Wednesday, July 31, 2013

Statement of peaceful demonstration of union of Oromo students in Germany













We, members of Union of Oromo students in Germany (UOSG), protest against human rights violation practices of criminal regime of Ethiopia known as Tigray People's Liberation Front or Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (TPLF/EPRDF). For example the Oromia Support Group in United Kingdom, a non-political organization to raise awareness of human rights violations in Ethiopia, has reported four thousand two hundred seventy nine (4,279) extra-judicial killings and 987 disappearances of civilians in Ethiopia from 1994 - 2010. 

--Full Report

fikrte

Injustice and non democratic practice is getting worse and worse in Ethiopia since TPLF is taking over the position of governance in Home land .With a mask cover of Ethnic federalism TPLF is destroying the people unity -working together, thinking mutual for the interest of one country, the love of one country as patriot, Ethnicity- this days in Ethiopia become a poison which kills slowly part by part, one Nation feels as differ enemies watching each other as an out comer, because of TPLF systematic attack we become to the target circle of TPLF’S plan.

People are getting arrested without accountability of Law, any one who is against the idea of TPLF or who have a different opinion will be harmed the way which is available, Their is no a free media freedom neither Journalist free practice in reporting News. so many journalists and reporters are getting arrested by proclaiming a terror-related charges, It is so sad here and then in Ethiopia to hear...See More

Hulum Ethiopiawi liyayewu yemigeba yezarewu Asgerami Teqawu BILL TUBE

ESAT Special The Former Ethiopian Air Force Association 20th An

ESAT Special The Former Ethiopian Air Force Association 20th An

Monday, July 29, 2013

Dr. Wondimu says Semhal Meles deposits $5 billion


የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። ይህን ያሉት እንግሊዝ አገር እሚገኙት ምሁር እና የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑት ዶክተር ወንድሙ መኮንን ናቸው። ዶክተር ወንድሙ የቼኩን ኮፒ አያይዘው ለእንግሊዝ ፓርላማ ሃውስ ኦፍ ኮመንስ አቅርበዋል። ሙሉውን እዚህ ያገኛሉ
July 26, 2013
Semehal Meles Zenawi, the daughter of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi, has deposited $5 billion in one of the banks in New York, said Dr. Wondimu Mekonnen, an academic and opposition figure, during a recent presentation at the House of Commons in the U.K. The date on the cheque that Wondimu distributed states the money was lodged on October, 2011.
Wondimu also showed and distributed a copy of the cheque of the money she lodged to the members of the House who attended his presentation.
Celebrity Net Worth site said Meles Zenawi got a net worth of $3 billion. What a shame! That is wrong guys. Absolutely wrong.  I have got a copy of a cheque signed by Semhal Meles Zenawi, the daughter of Meles Zenawi himself, depositing in one of the New York banks $5 billion. I have got and I will give you the copy. Don’t ask me how it came into our possession but that is a fact.
Wondimu further said ”I think, Celebrity Net Worth, got it entirely all wrong. If that was the case, how come, a check in the name of his elder daughter Semhal Meles Zenawi, for US5 billion was deposited into a bank in New York? We will leave the investigation to Department of Fraud and Money Laundering Investigation of the United States”.

ESAT Weekly News July 28 2013


Call for Peaceful Protest by all Oromos in Washington, D.C.

uly 24, 2013 | Washington, DC
To All Oromo nationals and friends of the Oromo in the Diaspora,protest_in_washThe Oromo Youth Self-Help Association (OYSA), in collaboration with other sisterly associations:  the Oromo Community Organization (OCO) of Washington D.C. area, and the Oromo Studies Association (OSA), has organized a peaceful protest to be held in Washington, D.C., in front of the White House and the US State Department, on Friday, August 02, 2013 to request the US administration put pressure on:
  • the Ethiopian regime to stop the mass killings & displacements of Oromos in Mayu Muluqqee, Qumbii, & Cilaqsan in East Hararge, Manasibu in West Wollega and Moyale in Boranaa of Oromia,
  • the Ethiopian regime to release Bekele Gerba, Olbana Lelisa and thousands of Oromo political prisoners,
  • the UNHCR, Egyptian, Yemen and Djibouti governments to protect Oromo refugees in Egypt, Yemen and Djibouti as well as respect the UN convention on political immigrants.
All Oromos and friends of the Oromos living in metropolitan areas of Washington D.C. (Maryland, Virginia), Pennsylvania, NY, Texas, Minneapolis, Seattle, Atlanta, etc are kindly asked to stand with us and advocate for our people who have been unjustly killed, displaced, incarcerated and silenced. This is also to protest against the inhumane treatment of Oromo immigrants in Egypt, Yemen and Djibouti. Together we can make a difference by speaking up for our people. We should say ‘Stop’ to the dictatorial regime in Ethiopia, and uplift the voice of our people to the world forum. It is evident that our people are suffering because of their identity, outlook and beliefs. Therefore, this is the time when you can take a practical action by standing with them and telling about their pains, which we all carry with us. Every shout and every protest will eventually make a difference!
Let’s act and march together, let’s stand side by side in large numbers and show to the world that we are serious about our people’s rights. Let’s show again and again to the US policy makers that we are indeed a strong force to reckon with and shall not be ignored.
On our previous protest of January 25, 2013 we proved that the Oromo youth is the real engine of Oromo power as we stood together with our seniors in extreme weather carrying placards, shouting slogans, and singing “Tokkummaa Tokkummaa”. Come and join us again! Don’t let any business or reason stop you! As we have done before, let’s make every effort to be there for our brethren on this day. This is a tiny sacrifice that we can pay for our nation Oromia!
Please also share this announcement to all in your domains; through social media such as facebook, twitter, email, via phone, paltalk, blogs, front-pages of websites, through radio/TV and personally in social gatherings.
United we stand, divided we fall!
Abebe Etana,
Chairman of the Oromo Youth Self-Help Association (OYSA)/WWDO, Washington, DC
Protest Date:    Friday, August 02, 2013
Protest Time:    9:00 AM – 1:00PM
Protest Place:   In front of The White House (Lafayette Park) 1600 Pennsylvania Avenue NW   
                          Washington, DC 20500 and then march to US State   
                          Department (Galvez Park), 2201 C Street NW, Washington, DC 20520
 Contact:            -   Oromo Youth Self-Help Association, Washington D.C.:
                                  Tel. 202-705-6585
                          -   Oromo Community Organization, Washington D.C.:
                                  Tel. 202-234-1151
=============================================================

Dear OSA members and friends,

The Oromo youth in general and the Oromo Youth Self-help Association (OYSA) in particular, were the key in our successful peaceful demonstration of January 25, 2013 in front of the US State Department in Washington DC. An estimated 60% of those on the rally were the youth. They made us proud.
Now, the Oromo youth have prepared another peaceful rally under their leadership and in collaboration with OSA and OCO, planned for August 2, 2013. This time the plan is to meet at the White House and march to the US State Department. The flyer for the event is coming up soon. I strongly urge OSA members for them to do their very best to participate on this rally. For those who come for OSA annual conference, I ask you to do your best to arrive in DC early on August 2 for you to be able to particpate on the rally. I understand that many of you may have purchsed air ticket already, but I am just asking you to do your very best to rearrange it.
Violence against the Oromo, which is a theme of one panel on our annual conference, is intensified in the Ethiopian empire as we speak. Just today, VOA Afan Oromo service (listenhere) reported that 21 Oromos, most of them Oromo university students, have been convicted of “carrying out the terrorist mission of OLF and endangering the unity of the country” after being in jail for over three years. [By the way OSA's annual conference preparation is also reported today by Namo Dandi in "dirree dimokrasii", you may listen to that as well].
If you may recall, one of the slogans we were chanting on our January 25 rally says “Release Student Dachasa Wirtu” and we were carrying his picture. Sadly, it is reported on today’s  VOA program that Dachasa Wirtu is one of those convicted of “serious crime” and is expected to receive a long prison term or possibly death. It is only today that his arrest has been reported on a major international media in the first place.
So, we can not keep silent. We have to speak for our brothers and sisters whose voices have been silenced. They have no body but us. Let’s stand with our boys and girls, our youth, and show that we are not a weak nation. Here is where we show our strength to our enemies and allies alike. It will be a shame for us to stay at home when our children are taking the lead to fight injustice which we passed on to them. In January, some people stayed home because of the bad weather which was understandably terribly cold that day in Washington DC. Now, we will not have any excuse.
Come, and join your children on August 2 at the White House! Fight tyranny! Don’t be silent, speak out!
United we prevail! Let’s do what we can do together. We can do this one!
Mosisa Aga, Ph.D.

Ethiopia — Rape, Torture, Jail



Image

Saudi Star’s 60-year, 10,000-ha lease came free of land rent. This cost incentive fueled the company’s planned acquisition of 500,000 ha of land in Gambella and other states to grow a projected one million tons of rice, as well as maize, teff, sugarcane and oilseed. Marred in conflict and human rights abuses after documented cases of arbitrary arrests, beatings, rape and torture, Saudi Star remains one of the most watched land deals. As locals tell of no prior consent about the land deal as well as of being forced off their land by the government, conflict has escalated and a shooting took place on the Saudi Star compound which left five Saudi Star employees dead in June 2012. In retaliation, the Ethiopian government has been indulging in arbitrary arrests, beatings, rape and torture. 

Image
Image

Image

Who is investing?

Indian firms, including Karuturi Globa and Ruchi Soya, among others, claim to have acquired over 600,000 ha of fertile land to grow edible oils, crops and cotton for export in Ethiopia, the fifth ‘hungriest’ nation in the world.

News coverage to date has emphasized the role of countries like China and Gulf States in the acceleration of land acquisitions in Africa. Our research showed that Indian firms are extremely active in countries like Ethiopia; it highlighted the major role of western firms, wealthy US and European individuals, and investment funds with ties to major banks such as Goldman Sachs and JP Morgan.

Image

Your land is my land

Those promoting land investments as the new development paradigm claim that their initiatives target unused and unproductive land while providing employment and growth opportunities to local populations. In Ethiopia, the current ‘villagization’ process, impacting nearly 1.5 million indigenous people, is taking place in the very same areas targeted for land investment by large-scale investors.
    Major African rivers — the Nile, Zambezi and Niger — are tapped by these land grabs. As an investor said, ‘Internally, we call our land fund — water fund’

Water and food — unlimited buffet

Foreign corporations are treating Africa’s water like an all-you-can-eat buffet. Many of the deals give developers free rein to take as much water as they want, dams and irrigation schemes are built, and groundwater is used with no analysis of the devastating impacts this will cause. As a result, local residents, especially women, have to travel much farther than before to find water, try to get into plantations to access their old water sources, or purchase it at inflated prices.

African rivers are lifelines for the people who depend on them for water and irrigation, but, now, major rivers are being drained so fast that they could be facing extinction. For example, the Niger river is decreasing by 10 per cent every decade and the problem is getting worse as more and more water-intensive agrofuel plantations emerge. In Ethiopia, the construction of a large dam on the Omo River and the irrigation of adjacent sugar plantations will result in Kenya’s Lake Turkana, the world’s largest desert lake, to drop by two metres in the first year, increasing salinity levels, adversely impacting fish stocks and invaluable grazing areas on the banks and condemning the lake to a not-so-slow death.

Image

The Oakland Institute research found little assurance that large-scale agricultural investments can improve food security, despite claims made by governments and investors. In many cases, local food farms are sold off in order to make room for export commodities, including biofuels and export crops.

Saturday, July 13, 2013

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!

July 13, 2013
Ginbot 7 weekly editorialወያኔ  በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም :: ለዚህም የሚሰጠው  ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል::  ዋና ከተማችን  አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት :: በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ  ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል ::
ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች  ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል። ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን  ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች  ዘርፎ  እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን  አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል :: በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል::
ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት  የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ   ሁኔታዎችን ለማመቻቸት   ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት  የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም  ለማሳመር መጣር ናቸው።:
የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ  ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት::
1) በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
2) በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሥራ በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
3) የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
4) በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
5) ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን”  የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
6) ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው  ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ  ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)
ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ስለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው::
የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው:: በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን  የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል::  አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴራ ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት  የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች  እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ  ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል? :
የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው:: ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው:: በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ  ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው::   ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል :: ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ  የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል  ማሰብ ብልህነት ነው::
ግንቦት  7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል::
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ዛሬ በደሴ ‹‹የሼኽ ነሩአዊ ሐረካት›› ድራማ ቀረጻ በመንግስት ተካሄደ (ድምፃችን ይሰማም)

July 11, 2013
መንግስት የቱን ሕዝብ ነው ሊያታልል የሚሞክረው?
ከመንግስት ከፍተኛ የሚዲያ ዘመቻ ጀርባ ያለው ድብቅ አላማ ምንድን ነው?
ከሳምንት በፊት የተገደሉትና ምንም አይነት የአስከሬን ምርመራ (Autopsy) ሳደረግባቸው በችኮላ እንዲቀበሩ የተደረጉትን የሼኽ ኑሩን ግድያ መንግስት ባሰበው መልኩ ፖለቲካው ጥቅም ሊያፍስበት በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ለማሳካት እንዲቻለውም የተለመደውን ስልት በመጠቀም በደሴና አካባቢው በሚገኙ ከተሞች የግዳጅ ሰልፍ በማስወጣት በሚዲያዎች የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ያደረገ ሲሆን፣ በመንግስት ብዙሀን መገናኛዎች በተለይም በኢቴቪና በአዲስ ዘመን ከፍተኛ የማራገብ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ መንግስት በተጨማሪም በሚኒስቴር መስሪያቤቶች እንዲሁም በፓርቲ ደረጃ ትናንት መግለጫ አውጥቷል፡፡ መንግስት በዚሁ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻው በመቀጠል ሼኽ ኑሩአዊ ሀረከት ድራማን በዜናና በሌላ የፕሮግራም ፎርማት ለማቅረብ የሚረዳውን ቀረጻ አካሄዷል፡፡ ይህ ድራማም ተቀናብሮ ዛሬ ምሽት ወይም ከሰሞኑ ለማታለያነት ለሕዝብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡Ethiopian Musilms
ይኽው ዛሬ በደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ ባድራ ጊቢ በተለምዶ አጠራሩ ረሺድ መስጊድ አካባቢ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የድራማ ቀረጻ በከፍተኛ ጥንቃቄ በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የድራማው ግብአት እንዲሆኑ እየተደረጉ ያሉትም የደሴ ከተማ ወጣቶች ናቸው፡፡ እንደምንጮች ዘገባ ሼኽ ኑሩ ከመገደላቸው በፊትና ከተገደሉም በኋላ የተያዙ የከተማው ሙስሊሞችን የዚሁ ወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለትም ይህንን ውንጀላ በድራማ መልኩ ሲቀርጹ ውለዋል፡፡ ቀረጻው በሚካሄድበት ቦታ ዛሬ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ የቆየ ከመሆኑም በላይ በአካባቢውም ማንም ዝር እንዳይል ተደርጓል፡፡
የካሜራ እና ፊልም ባለሞያዎች ከመንግስት ከፍተኛ ደህንነቶች በተሠጣቸው ስክሪፕት መሰረት ሷሊህ ሙሀመድ የተባለና ማክሰኞ ከሰዓት አካባቢ ተይዞ የነበረን ወጣት ዛሬ በማለዳው ወደ መኖሪያ ቤቱ ይዞ በመሄድ ቀረጻ አካሄደዋል፡፡ ለቀረጻው ግብአት እንዲመችና ሕዝብንም መሸወድ እንዲቻል መንግስት በወጣቱ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንዲቀመጡ በማድረግ ከወጣቱ መኖሪያ ቤት እንደተገኙ ተደርጎ ቀረጻ ተካሄዷል፡፡ በመቀጠልም ወጣቱ ሽጉጥ በእጁ እንዲይዝ በማስገደድ በቪዲዮ ቀርጻ የተካሄደበት ሲሆን፣ ሟችን ወጣቱ እንደገደላቸው አድርጎ ለማቅረብም ድራማው የሚያስፈልጉትን ዝግጅቶች መንግስት አከናውኗል፡፡ የወጣቱ ወላጅ እናትም የወንጀሉ ተባባሪ በሚል በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
የዛሬ የተካሄደውን የድራማ ቀረጻ ለማጀብ በርካታ የአካባቢው እና የክልል ባለስልጣናት እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን የነበረው ጥበቃም ከፍተኛ ነበር፡፡ መንግስት የሼኽ ኑሩን ግድያ ተንተርሶ እያካሄደው ያለው ዘመቻ ቀድሞ ከፍተኛ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን ፍንጭ ሰጪ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩን ሚዲያ ላይ ያራገበበት መንገድም አስገራሚ የሚባል ኖኗል፡፡ ላለፉት በርካታ አመታት በማህበረሰቡ ውስጥ አንቱታን ያተረፉ ከሌሎች እምነቶችም ሆነ ከሙስሊሙ ወገን አንጋፋ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከመጤፍ ሳይቆጠር በሼኽ ኑሩ ሞት ተስታኮ ተከታታይ እና ከቀበሌ እስከ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተቀናጀው ፕሮፖጋንዳ ከጀርባው ያለውን መልእክት በራሱ የሚናገር ነው፡፡ከጥቂት ሳምንታት በፊት ህይወታቸው ያለፈው ታላቁ አሊም ሀጂ ዘይኑ፣ ዶ/ር አብዱረሺድና ሌሎችም አሊሞች በመንግስት ሚዲያዎች ሞታቸውን አስመልክቶ ዘገባ እንዳልተሰራላቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በባህር ዳር በቅርቡ ከ15 በላይ ንጹሀን ዜጎች በፌዴራል ፖሊስ ተገድለው ተገቢው የሚዲያ ሽፋን እንዳልተሰጣቸውም ይታወሳል፡፡
መንግስት ግን ይህን የሼኽ ኑሩን ግድያ በማጎን ሙስሊሙን ህብረተሰብም የወንጀሉ ፈጻሚ አድርጎ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በክልል የሚካሄዱ የመብት ጥያቄዎችን ለማጨናገፍ የሰላማዊ ዜጎችን ንፁህ ደም በከንቱ ማፍሰሱ ሳይበቃ ድንበር ዘለል ፍረጃው እና ወከባው ከአሳሳ እስከ ደጋን፣ ከሃረር እስከ አዲስ አበባ የተተገበረ እና መላው ህዝባችንም የነገሩን ስር መሰረት በበቂ ማስረጃዎች ቀድሞውኑ ሲረዳው የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ መንግስት ባወጣቸው መግለጫዎች ሙስሊሙን የወንጀሉ ፈጻሚ አድርጎ እያቀረበ ቢሆንም፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ መሰል ወንጀሎችን ለመፈጸም ሀይማኖቱም ሆነ መርሁ የማይፈቅድለት መሆኑና ሁለት አመት በዘለቀው ትግላችንም መሰል ወንጀል ተፈጽሞ አለማወቁ ምስክርነት ይሰጣል፡፡ የትግላችን መሰረታዊ መርህ የሆነው ‹‹የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት አላማ የለንም›› መርህ እንኳን በዚህ ወቅት አይደለም መሪዎቻችንን በተነጠቅንበትና ከፍተኛ ወንጀል በተፈጸመባቸው ወቅትም ተጥሶ የማያውቅ መሆኑን ሁሉም ህብረተሰብ የሚያውቀው የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
የህዝባችን እና የትግላችን ሰላማዊነት የሚመነጨው ከምንከተለው መርህ መሆኑ ላለፉት 16 ወራት በተዘጋጁልን የትንኮሳ ወጥመዶች ውስጥ ላለመውደቅ ባደረግነው እልህ አስጨራሽ ትግል ፈተናዎችን በሚገባ በማለፍ አስመስክረናል፡፡ ሰላማዊው የደሴ ሙስሊምም እንደተቀሩት የሃገራችን ከተሞች በመቻቻል እና በመከባበር የሚኖር መሆኑ በአርዓያነት የሚነገር ነው፡፡ የደሴ ህዝብ እና መላው የሃገራችን ዜጎችም ከታሪካችን እና ከለመድነው ማህበራዊ መስተጋብር የወጣ ይህን መሰሉ ድርጊት ሲፈፀም አዳዲስ እጆች ሰርገው እንደገቡ ይረዳል፡፡ እነዚህ እጆች ደግሞ ሰላማዊ የመብት ጠያቂዎችን ለማፈን በተለያየ መጠን እና ግዜ ሲሰነዘሩ ሕዝቡ በበርካታ አጋጣሚዎች በአይኑ እየታዘበ በልቦናው አኑሯቸዋል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የዚህ አይነት ወንጀል የሚፈጽሙ አካሎች ቢኖሩ እንኳ ከማጋለጥ ወደ ኋላ እንደማይል የተረጋገጠና መሰል ወንጀሎችን እንደሚያወግዝ ደጋግሞ በአቋሙ አሳይቷል፡፡

ዶ/ር ሰይድ ሐሰን ኢሳትን አስመልክቶ ያደረጉት ንግግር

July 12, 2013

በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የኢሳት 3ኛ በዓልን አስደግፎ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ስብሰባ ላይ የቀረበ አጭር (ንድፍ/ግርድፍ) ነግግር

ከዶ/ር ሰይድ ሐሰን- Murray State University
ክቡራትና ክቡራን ወገኖች፤
በዚህ አጭር ንግግሬ 3 የተያያዙ ሐሳቦችን (ነጥቦችን) አንስቼ አቀርባለሁ።
ከዚህ በታች ያለው አጭር ንግግሬ ኢሳትን እንደ ነፃ ሚዲያ አድርጎ በማሰብ (assume) ነው። የእስካሁኑ የኢሳት የሥራ ጠባይም ይህንኑ ያመለክታል። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸውን፤ ካገር ውጭም፤ ካገር ውስጥም ያሉትን አስተናግዷል። የመንግሥት ባለሥልጣናትንም እየጋበዘ ለማነጋገር ሞክሯል። አንዳዶቹ- ለምሳሌ እንደነ አቶ በረከት ሲሞን ያሉት የኢሳት ጋዜጠኛ ሲደውልላቸው በጆሮው ላይ ቢዘጉበትም!
ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ የሆነ  የመገናኛ ዘዴ፤  ነፃ ሚዲያ/ፕረስ-  ለሀገርና ለሕዝብ ልማት በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይ ባሁኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን ነፃ ሚድያ እያስገኘ ያለው ጥቅም ብዙ ነው። የኢንፎርሜሽ ቴክሎጅን በሰፊው ተፎካካሪ ሀገሮችን ጥለው እንዲገሰግሱ እየረዳቸው ይገኛል። የሰውን  ባጠቃላይ ዓለምንም እየለወጠ ነው።Dr. Seid Hassan, Murray State University.
ለምሳሌ፤ ነፃና  ጠንካራ የመገናኛ ዘዴ፤ ነፃ ሚዲያ ተቋም፤ነጻ ፕረስ፤ የግል ቴሌቪዝንና ሬድዮ ጣቢያውች መኖር፤
ዲሞክራሲ እንዲስፋፋ (እንዲፋፋ) ይረዳል፤ እንዳውም፤ ዲሞክራሲ ያለ ነፃ ሚዳያ ሊኖር አይችልም። ሁለቱን ነጣጥሎ ማየትም አይቻልም!
ንግድ እንዲስፋፋ፤ የገባያ ፉክክር እንዲኖርና እንዲጠናከር ይረዳል። የገባያ ፉክክር ሲኖር ደግሞ ኢኮኖሚው ያድጋል፤ አገርም ትበለፅጋለች።
እውነት የበላይነት እንዲኖራት ይረዳል::
ቅርስንና ታሪክን ዘክሮና ዘግቦ ለውርስ የማስቀመጫ መሣሪያ ይሆናል።
ዜጎች ለችግሮቻቸው መፍትሄ ለመፈለግ እንዲወያዩ፤ እንዲከራከሩ፤ ይፈቅዳል/ይረዳል። በዚህም የተነሳ ዜጎች ብልህና ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲወስዱም ይረዳል።  ዜጎች ለሕብረተሰባቸውና ለሀገራቸው እድገት ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል።
ዜጎች በሀገራቸው ላይ የተፈጥሮ አደጋ፤ ተላላፊ በሽታ (ወረርሽኝ) ሲመጣ ባስቸኳይ ለሕብረተሰቡ መረጃዎችን ለማቅረብ፤ ሕብረተሰብም እንዲያውቃቸው ለማድረግ ይረዳል። ዜጎች እንድተባበሩም፤ የዜግነት ግዴታቸውን በፍጥነትና በጋራ እንዲወጡም  የመገናኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል።
የተጠፋፉ ዜጎችን፤ቤተሰቦችን፤ መተባበር የሚፈልጉ ሙያተኞችን ያገናኛል። በአካል መገናኘት ያልቻሉትን ሁሉ በቀላሉ ያገናኛል።
መንግሥት ሥራውን በትክክል እንዲሠራ ይረዳዋል; መንግሥት ለሕዝብ ተገዢ እንዲሆን ይረዳዋል። ዜጎች የመንግሥትን መጥፎም ሆነ መላካም ተግባሮች እንዲያዩ፤ እንዲገነዘቡና እንዲቆጣጠሩትም ይፈቅድላቸዋል፤ በአንፃሩም፤ አምባገነኖች ሕብረተሰቡን በተራ ውሼትና ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ሊያጠምቁና ሊበርዙ ሲፈልጉ መንገዱን ይዘጋባቸዋል። በዚህም የተነሳ ክፍተቶችንም ይሞላል።
ለነፃነት የሚደረገውን ትግል አቀጣጣይ መሳሪያ ሆኖ ያገልግላል። በጭንቅ ጊዜ (በጭንቅ ዘመን) የሕዝቡን አንድነት ሊያስተባብርና ለጋራ ትግሉ የመገናኛ  መድረክ ሆኖ ያገለግላል።
ፖለቲካዊና ህበረተሰባዊ ለውጦች እንዲመጡ/እንዲገኙ ይረዳል፤ አምባገነኖችን ከሥልጣን የማስወገጃ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የሕብረተሰቦችን፤ የዜጎችን ችሎታ ያዳብራል (ኢምፖወር ያደርጋል)።
ነፃ ሚዲያ ኢንፎርሜሽንን ስለሚያቀብል እውቀት እንዲስፋፋ ይረዳል። ባለፉት 20 ዓመታት እንደታየው፤ በርካታ ሀገሮች  አዲሱን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ፈጠራ) ተጠቅመው ሕዛባቸው በሥልጣኔና ዕውቀት እንዲገሰግስ አድርጓል። ደቡብ ኮሪያን ልምሳሌ መጠቀስ ይበቃል።
የግል ቴሌቪዝንና ሬድዮ ጣቢያውች መኖር አማራጭን ይሰጣል። ድምፃቸው ለተዘጋቸው ሀሳባቸውን የመግለጫ መንገድ፤ እንደ እንባ ጠባቂ ሆኖም ሆኖ ያገለግላል።
የመረጃ ማዕከሎችን በመፍጠር ትልቅ ሚናን ይጫውታል። መረጃና የመረጃ ተቋም የጋራ ሀብት ነው። መረጃ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው። መረጃ  ኃይል ነው። መረጃ እውቀት ነው። እውቀትም የጋራ ሀብት ነው!
ከላይ የጠቀስኳቸው  የነፃ ፕረስ፤ የነፃ ሚዳያና የመረጃ ተቋም መገኛ የሚያስገኛቸው ከፊል ጥቅሞች ናቸው። እነዚህ ጥቅሞች  አንድ የጋራ የሆነ ጠባይ አላቸው። ይኸውም፤ ጥቅማቸው በአብዛኛው ለግል ሳይሆን ለጋራና ለሕዝብ ነው። በእንግሊዝኛው የPublic Goods ጠባይ ካላቸው መጠቀሚያዎች ይጠቃልላል ማለቴ ነው።   ይህ የጋራ ጠባያቸው፤ ከጥቅማቸው ጋር ተያይዞም  ቢያንስ አንድ  ሁለት ችግሮችን ያስከትላል።
1ኛው ችግር፡ ጠንካራ ሚዲያን ለማቋቋምና ቀጣይ በሆነ መንገድ ለማስኬድ የሚያስወጣው የገንዘብና የጉልበት ወጪው በጣም ብዙ መሆኑ ነው።
ለምሳሌ፤ እንደ ኢሳት ያለውን ተቋም ለማቋቋምና ለማስቀጠል ባጭሩ፤
ሀሳብን በማፍለቅ፤መሰረቱን ለመጣል፤የአየር ሞገዱን ለመምረጥ፤ ለማስተካከልና ለመሳሰሉት፤ ለሚደረገው ውይይት የሚጠፋው ጊዜና ገንዘብ፤
ለመግሥት ታክስና የመሥሪያ ፈቃድን ለማስገኘትና ለማደስ የሚወጣው እንግልትና የገንዘብ ወጪ፤
የሳተላይት ጣቢያን ለመከራየት የሚወጣው ገንዘብ፤
ቦታዎችን ለመከራየት፤ ክፍያውንም በጊዜው ለመክፈል የሚደረገው ወጪ፤
አስፈላጊ የሆኑትን የቴክኖሎጂ የማስተላለፊያ መሣሪያዎችን (broadcast equipment – master control switcher፤ satellite receivers, tape decks, and a transmitter፤ ካሜራዎችን፤ ኮምፒዩተሮችን፤ ሶፍትዌሮችን፤ ወ.ዘ.ተ.) ለመግዛት፤ አሮጌውችን ባዳዲሶቹ ለመቀየር በየጊዜው የሚወጣው ገንዘብ፤.
ሙያተኛ (ፕሮፌሽናል) ጋዜጠኞችን ለመቅተር፤ ለማሰልጠን፤ የሰለጠኑትንም በአግባቡ  ቀጥሮና ከፍሎ ለማሰራት፤ ሳይቋረጥ የሚደረገው ወጪ፤
መረጃን ለማግኘት የሚደረገው ክፍያ፤ ጋዜጠኞች ከቦታ ቦታ ሲጓዙ የሚደረገው ወጪና ክፍያ፤
የተሰበሰቡትን መረጃውች ሰብሰቦና ቀርፆ ለማስቀመጥ የሚደረገው ወጪ፤
ለፕሮግራሚንግ (programming) ለመሳሰሉት የሚደረገው ወጪ፤ ወ. ዘ. ተ.

እንደነዚህና የመሳሰሉትን ለመሸፈን፤ ወጪው ከባድ ስለሆነ፤
ሀ.            አንዱ መንገድ፤ መንግስት ዜጎች ላይ ታክስ ጭኖ ወጪውን አጠቃሎ በመሸፈን ተቋሙን ማስቀጠል ነው። ይህ ክስተት በአፍሪካ፤ በኤሽያና በደቡብ አሜሪካ በስፋት ይታያል።
ለ.            ሁለተኛው መንገድ፤ የሚዲያ ተቋሙ ከመንግሥት ካዝና ድጓሜ እንዲደረግለት በማድረግ፤ የቀረውን እራሱ ተቋሙ በንግድ (ቢዝነስ) የገቢ ምንጩን እንዲፈልግ ማድረግ ነው። ምናልባት እንደነ ቢ.ቢ.ሲ.ን ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል።
ሐ.           ሦስተኛው፤ የግል ያልሆኑ፤ ለሕበረተሰብ አግልግሎት የተቋቋሙ የሬዲዮና የቴለቪዥን ጣቢያዎች (የሚዲያ ተቋማት)፤  ከመንግሥት ድጎማ እየተደረገላቸው፤ አንዳንድ የገዘብ ማስገኛ መንገዶችን እየፈላለጉ (ለምሳሌ ለኩባንያዎች ማስታወቂያን በማሰማትና በመለጠፍ) ወጪያቸውን ሽፋን ሲያደርጉ፤  በተጨማሪም በየጊዜው ኩባንያዎችንና ግለሰቦችን በመለመን፤ የማይናቅ ወጫቸውን ይሸፍናሉ። በአሜሪካ NPR : National Public Radio ን እና PBS: Public Broadcasting Serviceን  እንደምሳሌመጥቀስ  ይቻላል።
መረሳት የሌለበት ነገር፤ ኢሳትን ልዩ የሚድደርገው፤ሙሉ በሙሉ የእናንተ-ለእናንተ -ለሕዝባችን መሆኑ ነው። ከዚህ ዝቅ ብዬ እንደማሳየውም፤ ኢሳት በግለሰቦች መዋጮ የሚደገፍ መሆኑም የበለጠ ክበድት ይሰጠዋል።
እንግዲህ እኛ፤ አልታደልንምና በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ኢሳትን ሊረዳ ቀርቶ፤ ለማዳፈን በበርካታ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የሕዝብ ሀብት ያባክናል።  ህወሀት/ኢሕአደግ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጨለማ ውስጥ አጉሮ ለዘላለም ለመግዛት ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም። በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሀብትን እያፈሰሰ የኢሣትን ሞገድ በጥለፍ ለማጥፋት/ለማዳፈን ያላደረገው ነገር የለም።  ይህንን ሲያደርግም፤ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት፣ የፕሬስ ነፃነት የሚፈቅደውን የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 29ኝን (ሐሳብንና አመለካከትን የመያዝና የመግለጽ መብት) እንደተለመደው  በመጣስ ነው።
እንደዚህ ባልው ሁኔታ፤ ያለን አማራጭ የነጻ ሚዲያ ጥቅሙን በማሳየት እናንተ ኪሳችሁን እንድትዳብሱ “መለመን” የግድ  ነው። እንደዚህ ያለው ልመና አስፈላጊም ነው፤ የተለመደም ነው። አገር ወዳዶችና ተለማኞችም ሳይሰለቹ በቋሚነት መልኩ መለገስ እንዳለባቸው ማስታወስም የግድ ይላል። አሁን ከፊታችሁ የቆኩትም ለዚሁ ነው።
2ኛው ችግር፤ እንደ ኢሳት ያሉት የመገናኛ ዘዴዎች የሚያሰራጩት ዜና እና መረጃዎች፤ ዜናዎች፤ መዝናኛ ዎች … ግደታቸውን ለተወጡትም፤ ላልተወጡትም በጋራ ይደርሳሉ። የወር መዋጮቻቸውን ባለማድረገ ግደታቸውን ያልተወጡትም፤ ግዴታቸውን የተወጡም፤ የከፈሉም፤ ያልከፈሉም፤ ኢሳትን የሚወዱም፤ የማይወዱም፤ ኢሳትን ይሰማሉ፤ጥቅሙንም ይጋራሉ። ግደታችውን ያልተወጡትን መርጦ እንዳይሰሙ፤ ስርጭቱን እንዳይጋሩ፤ እንዳይጠቀሙ ማድረግ አቻልም። የነፃ ተጠቃሚዎችን (በእንግሊዝናው፤free riders ተብለው የሚዘረፉትን ማለቴ ነው ) ማግለል አይቻልም። ችግሩም በእንግሊዝኛው “Free-Rider Problem” ይባላል።  ይህ ችግር  በእንግሊዝኛው ከ“nonexcludability” criteria of a public good ችግር ጋር ይጠቃልለላል።
በዚህም የተነሳ፤ እያንዳንዱ ሰው፤ በግለሰብ ደረጃ፤ አንድ ጊዜ ተቋሙ ከተመሰረተ በኋላ፤ “ለዚህ ሀብትነቱ የጋራ ለሆነ፤ ጥቅሙ የጋራ ለሆነ፤ ጉዳዩ  የጋራ ለሆነ፤ የኔ ብቻ ላልሆነ…. ሌላው ይክፈለው እንጂ እኔ አልከፍልም፤ አላዋጣም” ሊል ይችላል! አልፎም፤  “ይህን የመሰለ “ግዳንግድ” ተቋም ከኔ ኪስ የምትፈልቀው መዋጮ ጋኑን ለመሙላት ለሚደረገው የውኃ ጋጋታ አንዲት ጠብታ ስለሆነች ማዋጣቴ ጉዳትንም፤ ጥቅምንም አያመጣም” የሚል ከንቱ አስተሳሰብን ያስከትላል። ይህ ጉዳይ በእንግሊዝኛው “Drop-In-The-Bucket Problem” ይባላል።  ከዚያም አልፎ “ኢሳትን ከማዳመጥ የሚከለክለኝ፤  ማናባቱ ነው! እምቢ፤ አሻፈርኝ፤ አልከፍልም” የሚል መጥፎ አስታሰብንም ሊያስከትል ይችላል!
እንደምታውቁት እንደዚህ ያለው ችግርና አስተሳሰብ “የፉክክር በር (ወይም ባለቤት የሌለው በር)  ሳይዘጋ ያድርና አደጋው ለሁላችንም  ይደርሳል!”  ከሚለው የአያቶቻችን ቁም-ነገራዊ  አስተሳሰብ ጋር ይያያዛል።
መልእክቴን ግልፅ ያደረግኩ ይመስለኛል፤ ኢሳትን እያንዳንዳችን በግል ተነሳሽነት ካልደገፍነው ኢሳት ሊኖር አይችልም! የኢትዮጵያ አይንና ጆሮ፤ የነጻነት ነፀብራቅ … እንዳይዳከም፤ እንዳይደፈን፤ መብራታችን ሆኖ እንዲቀጥል ከፈለግን፤ ቀጣይ በሆነ መንገድ መርዳት አለብን! ለሌላ የምንተወው ጉዳይ አይደለም!
በነገራችን ላይ ይህ ከላይ የነሳሁት ችግር በመገናኛ ዘዴ (ሚዲያ) ብቻ የተወነ አይደለም።
ጎበዝ፤ እኔን  የሚደንቀኝ፡-
ኢሳትን ለማቋቋም ለማስቀጠል በርካታ ገንዘብ እንደሚያስወጣ እያወቁ፤ ከላይ የጠቀስኩትን ችግርና ፈተና እያወቁ፤ በቀላሉ መውደቅን፤ መክሰርና እንደሚያስከትል እያወቁ ኢሳትን ያቋቋሙት ግልሰቦችና ቡድኖች  (እንደሰማሁት ከሆነም፤ አንዳንዶቹ የቤት ካርታዎቻቸውን ተያዥ በማድረግም ጭምር) እንዴት ደፍረው ይህንን ትልቅ ጉዞ፤ ይህንን ችሮታ፤ ጀመሩት? ነው።
በኔ አስተያየት፤ ኢሳትን የመሠረቱት/የጀመሩት (ይቅርታ፤ እኔ አንደኛው አልነበርኩም!) ሊከበሩ፤ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።
እነዚህ የዲሞክራት ሀይሎች በሕብረተሰቡ (በተለይ በዲያስፖራው) ላይ ያላቸውንም እምነት ያሳያል። የነፃ ሚድያ ጥቅሙንም ከማናችንም በላይ የተገነዘቡ ይመስለኛል! ለነጽነት፤ ለፍትሕ፤ ለዲሞክራሲ ያላቸውን ጥማት ያሳያል። የመንፈስ ጥንካሬያችውንም ያሳያል።  ተበታትኖ ከመጮህ ይልቅ ተቋምን ፈጥሮ የመታገልን ጥቅም የተገነዘቡ፤ ያወቁ ይመስለኛል! በዘላቂነት ውድ ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን ለማገልገል እንደተነሱም ያሳያል። እነዚህ ሥራዎቻቸውና እምነታቸው እኔን ማርኮኛል! ኢሳትን በማቋቋም እዚህ ድረስ በማድረሳቸው ትልቁን ሸክም አውርደውልንናል። ምስጋና ይገባቸዋል!
ከላይ የጠቀስኩትን ለማጠናከር ያህል፤ እስቲ ኢሳት በዚች አጭር የለጋ  እድሜው  ከሸፈናቸው ትላልቅ ጉዳዮችና ከተጫወተው ታሪካዊ ሚናዎች  አንዳንዶቹን  ልጥቀስ፤
የሙስሊሞች የድምፃችን ይሰማ፤ የመብታችን ይከበር ጥያቄን አስመልከቶ ያደረገው ሰፊ ሽፋንና የተጫወተው ሚና፤
ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል-ጉምዝ የተፈናቀሉትን የብዙ ዜጎች የእሮሮ ድምጾች፤ የህወሃትን የዘር የማጥራት (Ethnic Cleansing) ወንጀል  ሰፊ ሽፋን በመስጠትና በማጋለጥ የተጫወተው ሚና፤
በዋልድባ ገዳም መነኮሳት ላይ ህወሀት የደረሰውን በደል፤ እንግልትና መፈናቀል፤ የዘር ማጥራት ወንጀል፤ የመነኮሳቱን እሪታን በማስተጋባት በተካታታይ ያደረገው ሽፋን፤
በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በክረስትና ሀይማኖት ጉዳይ ውስጥ ያደርገውንና እያደረገ ያልውን ጣልቃ-ገብነት በማጋለጥ የተጫወተው ሚናና ሰፊ ሽፋን፤
ለመብታቸው መከበር በሚታገሉ ዜጎቻችን፤ ጋዜጠኞቻችን፤ ወ.ዘ.ተ. እደረሰ ያለውን  እስርና አፈና በማጋለጥ ያደረገው ሚና፤
የአቶ መለስ ሕልፈትን በሚመለከት ማንም ሳይቀድመው ያደረገው የዜና ዘገባና በህወሃት ላይ ያደረሰው ክስረትና ውርደት፤
መንግሥትን የከዱ ግለሰቦችን- ለምሳሌ፤ የኢት/ ቴሌኮሙኒኬሽን በሙስና መዘፈቅ፤አድሎአዊና የጎሰኝነት የተሞላበት አስተደደርን በሚሚለከት፤  በብረታብረትን የቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ተብየው ውስጥ፤ በኢትዮጵያ የጦርና መከላከያ መሥሪያ ቤት የሚደረገውን (እንደነ አቶ ተስፋየ አጽብሀ ያሉና ሌሎችን ማስታወስ ይበቃል)  እንግዶችን በእንግድነት በማቅረብ፤ በሰፊው እንደ፤ ደኩመንታሪ የሚሆን መረጃን በተከታታይ ማቅረቡ፤
ባጠቃላይ በሀገሪቱ ሰፍኖ ያለውን በደልና አድሎአዊ አስተዳደር ፤በተለይ የአንድ ጎሳ የባላይነት የሰፈነበት የሆነበትን ጉድ በተጨባጭና በመረጃ በተከታታይ ማቅረቡ፤በሚሊዮን የሚቆጠር አድምጭ እንዲሰማው ማድረጉ፤
የሶማሊው የክልል ፕሬዚደንት አቶ አብዲ ሞሃመድ ኦመር ከሶማሊ ጎሳ መሪዎች ጋር ያደረገውን ቅሌታዊ ውይይት፤ ከህወሃት ጋር ያደረገን መርዛዊ የፀረ አማራ ንግግርና  የፀረ-ኢትዮጵያዊ የሶማሊ ዜጋ በደልን፤ በሶማሊ አስተዳደር የሰፈነውን ሙስና  ወጣት አብዱላሂ ሁሴንን በእንግድነት በማቅረብ ያቀረበው ዘገባ/ቅሌት፤
ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የህበረተሰባዊ ተራድዖ መሬዎች፤ የሀሳባቸው መግለጫ መደረክ በመሆን የተጫወተውና እየተጫወተው ያለው ሚና፤
በሀገሪቱ ተንሰርፍቶ ያለውን ሙስና በማጋለጥና በመዘከር ያደረገውና የሚያደረገው አስተዋፅዖ፤
በኔ አስተያየት፤ ከላይ የጠቀስኳቸው የኢሳት ተግባሮች በዋጋ የሚተመኑ አይደሉም! እርሰዎም ያውቁታል፤ ኢሳትን እያዳመጡም አድንቀዋል! ሌሎች የከፈሉም ሰምተውታል፤ አድንቀዋልም! ለመሆኑ ድርሻዎን በትክክል ተውጥተዋል? ጥቅሙን ካወቁ፤ ከዚህ በላይ ያሰፈርኳቸው ችግሮችና ቁምነገሮች የገቡዎት ከሆነ ማለቴ ነው!
መደምደሚያ፤
እንግዲህ እኛ፤ አልታደልንምና በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ኢሳትን ሊረዳ ቀርቶ፤ ለማዳፈን በበርካታ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የሕዝብ ሀብት ያባክናል።  ህወሀት/ኢሕአደግ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጨለማ ውስጥ አጉሮ ለዘላለም ለመግዛት ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም። በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሀብትን እያፈሰሰ የኢሣትን ሞገድ በጥለፍ ለማጥፋት/ለማዳፈን ያላደረገው ነገር የለም።  ይህንን ሲያደርግም፤ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት፣ የፕሬስ ነፃነት የሚፈቅደውን የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 29ኝን (ሐሳብንና አመለካከትን የመያዝና የመግለጽ መብት) እንደተለመደው  በመጣስ ነው።
እንደዚህ ባልው ሁኔታ፤ ያለን አማራጭ የነጻ ሚዲያ ጥቅሙን በማሳየት እናንተ ኪሳችሁን እንድትዳብሱ “መለመን” የግድ  ነው። እንደዚህ ያለው ልመና አስፈላጊም ነው፤ የተለመደም ነው። አገር ወዳዶችና ተለማኞችም ሳይሰለቹ በቋሚነት መልኩ መለገስ እንዳለባቸው ማስታወስም የግድ ይላል። አሁን ከፊታችሁ የቆኩትም ለዚሁ ነው።
ወያኔ/ኢሕአደግ  እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን እንደጦር የሚፈራቸውም ያለምክንያት አይደለም፡፡ መላው ዓለም ለኢኮኖሚውና ለኅብረተሰባዊ ዕድገቱ እየተጠቀመበትና የኤኮኖሚ፤ የፖለቲካዊና የሕብረተሰባዊ እድገቱን በፈጠነ መልክ እያስኬደ ባለበት በዚህ የሥልጣኔ ግስጋሴ ዘመን፤ ወያኔ/ኢሕአደግ  የሬዲዮ፤ የሳተላይት ቲቪ ስርጭቶችን፤ የኢንተርኔት፤ የእስካፕና ሌላውን ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ መዝጋቱ፤ ለመዝጋት መጣሩ፤ መበሰሱ፤ ኅብረተሰቡ በጨለማ ውስጥ እንዲጓዝ ማደረጉ፤ የትምህርት ተቋሟት ጥራት መቀነሱ፤ በጣም የሚያስፍር ነው። በሥላጣን ላይ ያሉት ቡድኖችና ግለሰቦች የቱን ያህል፤ወደኋል የቀሩ መሆናችውን ያሳያል። እነዚህን የረከሱ ኋላ ቀሮች እንድንታገላቸው የሚያስችለን እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን፤ የመረጃ ማዕከላትን  በመመሥረትና በቋሚነት በመደገፍ ብቻ ነው።
በኔ አስተያየት ለመጀምሪያ ጊዜ የዲያስፖራው ሕብረተሰብ የሠራው ውጤታማ ሥራ ኢሳትን ማቋቋሙ ነው። ኢሳት በጨለማ ውስጥ እየማቀቀ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ  የነፃነት ችላጭል ሰጥቶታል። ወደፊትም ይህ የመገናኛ ዘዴ የበለጠ እንድንተባበር፤ ለነጻነታችን የምናደርገው ትግላችን  እንዲስምር፤ የሕዝባችን አንድነት እንዲጠነክር የሚረዳን፤ እንዳውም ህወሀት በቆፈረልንና እየቆፈረልን ባለው ጉድጓድ እንዳንገባ፤ እንዳንተላለቅ መገናኛና መወያያ፤ የመፍትሄ መፈለጊያ መደርካችን፤ መሳሪያችን ይሆናል ብዬ አጥብቄ አምናለሁ። የመልካም ዜጎች ትልቁ ሚና እና ትልቁ እርዳታ መሆን ያለበት እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን መፍጠርና ማስቀጠል ነው።
ኢሳት እንዲቀጥል፤ እንዲያድግ፤ ቋሚ ሆኖ እንዲያገለግለን  እያንዳንዳችን፤ ሁላችንም –  ማንም ሳይነግረን፤ ማንንም ሳንጠብቅ፤ ማንም ሳይለምነን፤ በባለቤትነት፤ በግል ተነሳሽነትና ሀላፊነት በተሞላው መንገድ፤ በቋሚነት ድርሻችንን መወጣት አለብን ብዬ አምናለሁ። እያንዳንዳችን ኢሳትን ለመጠበቅ ዘብ መቆምም አለብን።
ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።

“ወደ እናት ሀገራችሁ በመምጣት አዲስ አበባ ላይ በሚካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፉ!” ፤ እስክንድር ነጋ

July 11, 2013
በበትረ ያዕቆብ
በአምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሐሰት ዉንጀላ ለእስር የተዳረገዉ ታዋቂዉና ተወዳጁ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ዲያስፖራዉ በሀገር ዉስጥ እየተካሄደ ባለዉ ሠላማዊ ትግል ላይ በአካል ተገኝቶ እንዲሳተፍ መልዕክት አስተላለፈ፡፡
የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በአካል ለመጠየቅ ቃሊቲ ለተገኙ ጋዜጠኞች እና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሕዝባዊ ንቅናቄ የግብር ሃይል አባላት አደራ ሲል ባስተላለፈዉ መልዕክቱ ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ቀጣይ በሚካሄዱ የተቃዉሞ ሰልፎች ላይ (በተለይም አዲስ አበባ ከተማ ላይ በቅርቡ ሊካሄድ በታቀደዉ ትልቅ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ) በአካል በመገኘት ተሳታፊ መሆን ይገባቸዋል ብሏል፡፡
“ዲያስፖራዉ በአካል ተገኝቶ የሚያደርገዉ ተሳትፎ ትግሉን የበለጠ ያጠናክረዋል” ሲል ለጠያቂዎች የተናገረዉ እስክንድር ነጋ ፤ አያይዞም “ዲያስፖራዉ ማንኛዉንም መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ሊሆን ይገባል” ብሏል፡፡ በተጨማሪም በግብፅ አቢዎት የግብፅ ዲያስፖራዎች የነበራቸዉን ቀጥተኛ ተሳትፎና ጉልህ ሚና በዝርዝር በመጥቀስ “እኛ ኢትዮጵያዉያን ከእነርሱ ብዙ ልንማር ይገባል” በማለት ተናግሯል፡፡
እስክንድር ደጋግሞ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሊካሄድ የታቀደዉ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ዲያስፖራዉ ለሀገሩ ያለዉን ቀናኢነት እንዲሁም ለወገኑ ያለዉን ፍቅርና ወገንተኝነት በተግባር የሚያሳይበት ትልቅ አጋጣሚ ነዉ ያለ ሲሆን፡፡ ይህን በመረዳት “በዉጭ ሀገራት የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ከአሁኑ በዚህ ታሪካዊ ክስተት ላይ ለመሳተፍ ሊዘጋጁ ይገባል” ብሏል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ እንደ አገር በመቀጠልና ባለመቀጠል አጣብቂኝ ዉስጥ እንዳለች እና ዜጎችም በጭቆና ፍዳቸዉን እያዩ እንደሚገኝ የጠቆመዉ እስክንድር ነጋ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመቅረፍ የግድ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ያስፈልጋል ሲል ተናግሯል፡፡ አያይዞም “አሁን በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መሪነት “የሚሊዎኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የተጀመረዉ የትግል እንቅስቃሴ ይበል የሚያስብልና የሚያበረታታ ነዉ” ያለ ሲሆን፡፡ “ትግሉ በዚሁ ተጠናክሮ ከቀጠለ እንዲሁም የሁላችንም ተሳትፎ ከታከለበት ያለምንም ጥርጥር ወደ ነፃነት ጎዳና ያደርሰናል” ብሏል፡፡
“አትፍሩ! ለአንባገነኖች ዛቻ ቦታ አትስጡ!” በማለት የተናገረዉ እስክንድር ነጋ “ፍርሐት የጨቋኞች ዋንኛ የአፈና መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም በድፍረት ድል ሊያደርገዉ ይገባል ሲል አብራርቷል፡፡” አያይዞም “መቁሰል ፣ መታሰር እና መንገላታት ሊኖር ይችላል ሆኖም ግን ይህ የምንከፍለዉ መስዋትነት አገር አልባ ከመሆን ያድነናል ፤ የተሻለች አገር ለመገንባት እና ለቀጣዩ ትዉልድ ለማስተላለፍ ይረዳናል” ብሏል፡፡ በመጨረሻም “ወደ እናት ሀገራችሁ በመምጣት አዲስ አበባ ላይ በሚካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፉ፡፡” ሲል ከአደራ ጋር ለዲያስፖራዉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

Saturday, July 6, 2013