Wednesday, November 26, 2014

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በተቀናጀ የከተማ ፕላን ላይ የመስተዳድሩን ሰራተኞች ሊያሰለጥን ነው


ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከላከው ቅጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ የከተማ እቅድ ዙሪያ በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ስልጠና ይዘጋጃል።
ፓርቲው የተለያዩ ቅጾችን ለሰራተኛው በመበተን ሰራተኛው እስካሁን ስለነበሩት ክንውኖችና ድክመቶች አስተያየቱን እንዲጽፍ ተጠይቋል። እጅግ አወዛጋቢ ሆኖ ተቃውሞ ያስነሳውንና በርካታ ሰዎች የሞቱበትን የአዲስ አበባ አዲስ ካርታ ለማስፈጸም መስተዳድሩ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።
የኦሮምያ ክልል መሬቶችን ወደ አዲስ አበባ  መስተዳድር ማስገባቱ ለበርካታ አርሶደሮች መፈናቀል ምክንያት ይሆናል በማለት ተቃውሞ ያስነሱ በኦሮምያ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች መገደላቸውና መታሰራቸው ይታወቃል። መስተዳድሩ በአቋሙ በመጽናት ውሳኔውን ለማስተግበር እንቅስቃሴ መጀመሩ  ሌላ ዙር ተቃውሞ ሊያስነሳ እንደሚችል ምንጮች ጠቅሰዋል።             esat radio

No comments: