Wednesday, January 28, 2015

የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94ኛ የልደት በዓል ተከበረ


January 28, 2015
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
Ethiopian Hero Lt. General Jagama Kello
በጣሊያን ዳግም ወረራ ወቅት በ15ኛ አመታቸው ከፋሽስት ወራሪ ጦር ጋር በተለያዩ አውደ ግንባሮች ተፋልመው ከፍተኛ ጀብዱ የፈፀሙት እና ጣሊያን ከአገር ተሸንፎ ከወጣ በኋላም የአገር ዳር ድንበርን በማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነት የፈፀሙት የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94ኛ የልደት በዓል ዛሬ ጥር 20 ዓ.ም ተከበረ፡፡
በ1929 ዓ.ም ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ገና በወጣትነታቸው የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ጠላትን የተዋጉት ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በወቅቱ በተለያዩ የጦር ውሎዎች በጠላት ላይ ከፍተኛ ጀብዱን ተቀዳጅተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሶማሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የአገርን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡
ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ጥር 20/1913 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን በዛሬው ዕለት ቀበና አካባቢ በሚገኘው የልጃቸው የትምወርቅ ጃጋማ ቤት የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት 94ኛ አመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም የሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ 94ኛ የልደት በዓል ላይ ተገኝተው አክብረዋል፡፡
ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን ከነበሩት ሌ/ጀኔራሎች መካከል በህይወት የሚገኙት ብቸኛው ጀኔራል ሲሆኑ አንድ ወንድና አምስት ሴት ልጆች፣ አምስት የልጅ ልጆችና አራት የልጅ ልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡sourse ecdef

No comments: