Tuesday, May 26, 2015

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ይህን መግለጫ አውጥቷል።



ያኔ ኢሓዴግ በምርጫ ተሸንፎ እያለ አጭበርብሮ በሥልጣን ለመቀጠል በሚያደርገዉ መፍጨርጨር ለሚከተለዉ ማንኛዉም ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተጠያቂ ነዉ።
===========================================================
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ይህን መግለጫ አውጥቷል።
በ 2007 ብሄራዊ ሀገር አቀፍ ምርጫ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከምርጫው ቅስቀሳ ጊዜ ጀምሮ ያለው ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ አለመሆኑን ባወጡት ሪፖርት አረጋግጠዋል::ወያኔ በምርጫው ቅስቀሳ ሂደት ድብደባ፣ አፈና ፣እስራት ፣ግድያ እና እንግልት በግልጽ ፈጽሟል:: (በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ እና በአርሲ ኮፈሌ የተፈጸመው ግድያ ፤ በእነ በቀለ ገርባ ላይ በበደሌ፣ ጅማ እና በነቀምቴ የተፈጸመውን ድብደባ ልብ ይሏል)
ተቃዋሚዎች ወያኔ ኢሓዴግን በምርጫ ክርክር አዋረዷት:: ህዝቡ ለመድረክ የሰጠው ድጋፍ ስላስደነገጠው ሃይልን በመጠቀም ጫና ቢያደርግም አልተሳካላትም:: ተስፋ ስቆርጡ ለምርጫው ሁለት ቀናት ሲቀሩት ጠ/ሚኒስትሩ ፓርላማው በማይጠራበት ወቅት ስብሰባ በመጥራት ማስፈራሪያ እና ዛቻ በተቃዋሚዎች ላይ ሰንዝረዋል:: ይህም አስቀድሞ የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ በሃይል ምርጫውን ለማጭበርበር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር የሚያስይ ነበር :: የኢሕዴግ ካድሬዎች የምርጫው ዋዜማ ሌሊት ከአለቆቻቸው የተላለፈውን ትእዛዝ ለመፈጸም አስቀድመው ኮሮጆ በመሙላት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የፌዴራል ፖሊስ: ሚሊሺያዎች: ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና አድማ በታኝ ፖሊሶችን በማዝመት የምርጫ ቦርድ ተወካዮችን እና የተቃዋሚ (የመድረክ) የምርጫ ታዛቢዎችን መታወቂያቸውን በመቀማት እያስፈራሩ እየደበደቡ በርካቶችን (90%) ሙሉበሙሉ ማለት ይቻላል ከምርጫ ጣቢያ በሀይል አባረዋል።በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምርጫ ካርድ ተከልክለዋል። የመምረጥ መብታቸዉን ተነፍገዋል።
ስለሆነም: ፀረ ሠላም እና ፀረ ዴሞክራሲ የዘረፋ ቡድን የፈጸመው ምርጫን ማጭበርበር ፣ የህዝብ ድምፅ መዝረፍ፣ ንጹሃን ዜጎችን መግደል እና የማሰር ድርጊት አጥብቀን እያወገዝን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ይህን መግለጫ አውጥቷል።
1. ኦፌኮ/ መድረክ በኦሮሚያ ክልል ምርጫዉን ሙሉ ለሙሉ አሸንፏል።
2. የተፈፀመው ድርጊት በማንኛውም አለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን:: በጽኑ እናወግዛለን::
3. ይህንን የህዝብ ድምፅ ዝርፊያ እና የምርጫ ማጭበርበር ተከትሎ ለሚነሳው የህዝብ ተቃውሞም ሆነ መንግሥት ለወሰደው እና ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው እራሱ ኢሓዴግ ነው።
4. የህዝቦች ህገመንግስታዊ መብቶች በተጣሰበት፣ በማፈንና በማስፈራራት ምርጫ አስፈፃሚዎች እና የምርጫ ታዛቢዎች ተባረው ምርጫ ተካሂዷል ለማለት አንችልም።
5. ህዝባችን የመረጠው ድርጅት ኦ.ፌ.ኮ /መድረክ/ የሚያደርገውን ቀጣይ የትግል ጥሪ ዝግጁ በመሆን እንዲጠብቁ እናሳስባለን ።
6. የወያኔን አፋኝ ስርአት እድሜ ለማሳጠር በትግል ላይ የምትገኙ ሃይሎች: ወያኔ ይህን ያህል ረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው በራሱ ድርጅታዊ ጥንካሬ ሳይሆን የተቃዋሚ ሃይሎች ትግሉን በተቀናጀ ሁኔታ ያለመምራት በመሆኑ በቀጣይ ለሚደረገው ትግል የፖለቲካውን ክፍተት በመዝጋት ትግሉን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር በመተባበር እና ልዩነቶችን በማጥበብ እንድንታገል ጥሪ እናቀርባለን።
ትግሉ ይቀጥላል !!!

No comments: