OCTOBER 13, 2015 LEAVE A COMMENT
በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) አብዲ ባለፉት አራት አመታት በማረሚያ ቤት እየተማረች እንደነበርና አምስተኛ ክፍልም መድረሷ ተገልፆአል፡፡
ይሁንና በዚህ አመት እንዳትማር የተከለከለች ሲሆን የተከለከለችበትን ምክንያት ስትጠይቅም ‹‹አንቺ መማር አይገባሽም!›› እንደተባለች የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አሊማ አብዲ መሃመድ የ23 አመት ወጣት ስትሆን በመደበኛ ጊዜ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ ክፍለ ሀገር በሚኖሩት የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ ከ6፡00 እስከ 6፡30 ለሰላሳ ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡ source በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተ
No comments:
Post a Comment