esat radio
ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን
ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው።
እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ
ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው።
አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት በሚል አቶ አንዳርጋቸውን በቴሌቪዥን ማሳየቱን ገልጸው፤ ህዝቡ በዚህ ሳይዘናጋ ፣
ባርነትን ከራሱ ለማውረድ ከፈለገ የራሱን እርምጃ መውሰድ መጀመር አለበት ብለዋል።
ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየትና እንዴት እንደሚታገል ፍንጭ ነው ያጣው ካሉ በሁዋላ፣ ስራውን መጀመር አማራጭ የሌለው ነገር ሲሉ አክለዋል።
“አንድ ቀን ቀን ይወጣል ብለን” ስንጠብቅ ከርመናል ያሉት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ከእንግዲህ የምንጠብቀው ምንም ነገር የለም፣ ሁሉም ደምቷል ብለዋል።
“እኛም ሴቶች ብንሆን ለትግሉ ብዙ የምናግዘው ነገር ይኖራል” ያለችው አንዲት የራያ ቆቦ ነዋሪ፣ ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወደፊት መቀጠል እንዳለበት ገልጻለች።
በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫዎችን ማውጣት የቀጠሉ ሲሆን፣ የተቃውሞ ሰልፎችም በተለያዩ አካባቢዎች እየተደረጉ ነው።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ግንባር ወይም በእንግሊዝኛው አርዱፍ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቁጣውን ገልጿል።
የመን ህገወጥ በሆነ መንገድ አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ መስጠቷን በጽኑ ያወገዘው አርዱፍ፣ የመን በፈጸመቸው ህገወጥ ተግባር ተጠያቂ መሆን አለባት ብሎአል።
አቶ አንዳርጋቸውን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮችን በማሰር የነጻነት ትግሉ እንደማይቋረጥ የገለፀው አርዱፍ ፣ እንዲያውም ትግሉን የበለጠ እንድናጠናክር ያደርገናል ሲል አክሏል።
የአለማቀፍ ማህበረሰቡ፣ የእንግሊዝ መንግስትና የኢትዮጵያ ሃይሎች በሙሉ ለአቶ አንዳርጋቸው መለቀቅ አበክረው እንዲሰሩ አርዱፍ በመግለጫው ጠይቋል።
በብሪዝበን አውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ጋዜጠኛ ኤልሳ ይመኑ ከስፍራው ዘግባለች።
በፊንላንድየሚገኙኢትዮዽያውያንእናትውልደኢትዮዽያውያን ደግሞ ሄልሲንኪ በሚገኘው የ እንግሊዝ
ኤምባሲ በመገኘት ያዘጋጁትን ደብዳቤ አስረክበዋል። ኢትዮጵያውያኑ በደብዳቤው የየመን መንግስት የፈፀመውን ታሪካዊና ይቅርታ የማያሰጥ ተግባር በጽኑ አውግዘው
የየመን መንግሥት አለም አቀፍን ሕግ ጥሶ ለፈፀመው ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ መንገዶች እና ግዜያት ዋጋ እንደሚያስከፍለው አስታውቀዋል ።
የእንግሊዝ መንግስትም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዜጋው ስለሆኑ ፣ ሰብአዊ መብታቸው ስለተገፈፈ እንዲሁም የህወሓት አገዛዝ በቶርቸር እና ሰብአዊ መብት ረገጣ አለም አቀፍ
ድርጅቶች ባረጋገጡት መሠረት የታወቀ በመሆኑ ባስቸኳይ ተለቀው እንግሊዝ ሀገር ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የእንግሊዝ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ባፋጣኝ እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን አገዛዝ፣የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ግድያ የሚዲያ አፈና፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አለመከበር የእንግሊዝ መንግሥት ዝም
ብሎ ማየቱን ከቀጠለ ወይንም ጠንካራ አቋም የማይወስድ ከሆነ ለጊዜያዊ ጥቅም ብሎ ዘለቄታዊ
የሆነውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና የእንግሊዝ ብሔራዊ ጥቅም ስለሚጎዳ እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የውጭ ጉዳይ ፓሊስ እንደገና ባትክሮት እንድትመረምረው ጠይቀዋል ።
No comments:
Post a Comment