ዳኛቸው ቢያድግልኝ
በመላው አለም የተደረጉ የነጻነት ትግሎች በሙሉ በጉልበት በአፈናና በግድያ ጭሩሱኑ ሲገቱ አይተን አናውቅም። የትግሉን
ጊዜ የማራዘም ወይም የጥፋት ደረጃውን የማሳደግ ሀይል ሊኖራቸው መቻሉ ብቻ እርግጥ ነው። ኢትዮጵያ በሸፍጠኞች እጅ
ወድቃ ወደ ጥፋት በሚነዷት ደናቁርት ታግታ ያለችበት የታሪክ አጋጣሚ ላይ ሆነን በዚያው መጠን ደግሞ የአደጋውን ልክ
መረዳት አቅቶአቸው እርስበርስ በሚጠላለፉ የፖለቲካ ድርጅቶች መደናበር ሳብያ ከውድቀት ወደ ጥፋት በመጓዝ ላይ ነን
ወይም ነበርን። ሕዝቡን ከፍርሃት ወደ ተስፋ መቁረጥና ሰማያዊ ሀይል ብቻ ነፃ እንደሚያወጣው እንዲያስብ መገደድ
እንዲችል እየተገፋ እንደነበርም እናውቃለን።
እንዲህ አይነት ተስፋ መቁረጥና አቅመቢስ ስሜት መሰማትም አዲስ ነገር አይደለም። ሁሉም በአንድና ተመሳሳይ አቅጣጫ
መጓዝ እስኪጀምርና ውህደት ፈጥሮ አንድና የማይነጣጠል ሀይል እስኪሆን መሆን ያለበት ትርምስ ሁሉ የግድ ይሆናል።
መራር ቡና ውስጥ አንኳር ስኳር ስለገባ ብቻ አያጣፍጠውም አንኳሩ ተበትኖ ተፈረካክሶና ሟምቶ አንዱ ከሌላው
በማይለይበት ደረጃ ከቡናው ጋር ውህደት ሲፈጥር ግን ከፍተኛ የጣዕም ልዩነት ይፈጥራል።
ሕዝባዊ ትግልም እንደዚያው ነው። ተበታትኖ የየግል ችግሩን መሪ ጉዳዩ እድርጎ በየአቅጣጫው ይተምና የችግሮቹ ምንጭ
አንድ መሆኑን ሲያውቀው ወደዚያው አንድና ብቸኛ የችግር መንስዔ ያተኩራል፣ እናም ተባብሮ አንድ ሆኖ ድልን
ይቀዳጃል። ኦሮሞው በአንድ ወገን፣ አፋሩ በሌላ፣ ኦጋዴን በዚህ ሀዲያ በዚያ ትግሬው በሰሜን ሶሜሌው በምስራቅ
ተበታትኖ አንድ ማፍያ ቡድንን ይታገላል። የትግል መርሁ ግን አንድና ተመሳሳይ ነው ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ!
አንድነት ሰማያዊ መድረክና ሌላም ስያሜ ሰይሞ አንድና ተመሳሳይ ጨቋኝን ይታገላል። ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር እያለ
ነፍጥ ይዞ ሀገሩን አፍኖ የያዘውን ግንባር ይገጥማል። ይህም ወገን ቢሆን የትግል መርሁ አንድና ተመሳሳይ ነው ፍትህ፣
ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ! ይህ የተበታተነና ያልተቀናጀ ትግል በተናጠል ለመጠቃትና ወደፊት አላራምድ እንዳለ
ለመረዳት ሲያስችል ወደ አንድ ጎራ መሰባሰብ የግድ ይሆናል። ይህ መሰባሰብና ሀገራዊ ቁጣ ደግሞ ገዢውን
ስለሚያስጨንቀው ይበልጥ ወደ ቁጣና ቆራጥነት የሚገፋፋ ዳር ያለውን መሀል የሚያስገባ ተጨማሪ እርምጃዎችን
እንዲያደርግ ይገፋፋዋል። ይህም ቁጣውን እያባበሰ ትግሉንም ፈር እያስያዘ አምባገነኖቹ የሚኮሩበትን ተቋማት
መሰነጣጠቅና መፈረካከስ ይጀምራል። እንዲህ ነው የአምባገነን ስርዐት ሁሉ ተገፍቶ የሚንኮታኮተው።
የሰሞኑ የአንዳርጋቸው ጽጌ መታገትም አንድ ምሳሌ ነው። እንኳን የግንቦት ሰባት አባላትንና ደጋፊዎችን ይቅርና የግንቦት
ሰባት ተቃዋሚዎችን ሁሉ ወደ አንድ ጥግ ያመጣ ጉዳይ እንደሆነ ስንመለከት ተነጣጥሎ በተራ ከመጋዝ አንድ ሆኖ የግፍ
አገዛዝን ማውገዝና መገርሰስም አስፈላጊ መሆኑን በውድም በግድም እያመንበት መምጣታችንን ያመለክታል። ዘወትር
በሀገራችን እንደሆነውና ወደፊትም እንደሚሆነው ሁሉ በወዳጅና ዘመድ መካከል ያለን ችግር በይደር አሳልፎ ዋንኛውን
የሀገር ጠላት መፋለም የጊዜው ጥሪ ሆኖ ተገኝቷል። ያለአስተባባሪና መካሪ ወደ አንድ ጎራ የመሰባሰባችን ዋናው ምክንያትም
ይኸው ብሄራዊ ውርደታችን ነው። የተዋረደው ኢትዮጵያዊነት እንጂ አንድ ጎሳ ወይም የፖለቲካ ድርጅት አይደለምና ጉዳዩ
የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኑ አያጠራጥርም።
ከጎረቤት ሀገሮች አንስቶ እስከ አረብ ሀገራት የዘለቀው መጋዝ፣ መታሰር፣ መሸጥ መለወጥና ሌሎችም አሸማቃቂ ሰቆቃዎች
ሊፈጠሩ የቻሉት ኢትዮጵያ ግዴ የማይላቸው ሰዎች በስልጣን ላይ መቀመጣቸውና ትናንሽ ፍርፋሪ የሚወድቅላቸውም
የዚሁ ስርዓት ጉልበት ሰጪ በመሆናቸው ነው። ወጣቶች ቁጭ ብሎ ሞትን ከመጠበቅ እየሄዱ ማለቅ በሚል ያልተፃፈ
መፈክር ተስማምተው አገራቸውን ጥለው በየአቅጣጫው የሚሰደዱት በሀገራቸው የተስፋ ጭላንጭል በማጣታቸው ነው።
በዚችው ሀገር ከበለፀጉ ሀገሮች የሚያስንቅ የምቾትና የተድላ ህይወት የሚኖሩ ሳይሰሩ የከበሩ የማፍያዎቹ ወዳጅ ዘመዶችን
እያዩ በነሱ ጥጋብና ደስታ የሀገር እድገትን የሚሰፍሩ ተላሎችም ከሰለባነት አልዳኑምና ወደ ሕዝቡ ጎራ እየተቀላቀሉ ነው
ነው የሌሎች መምጣትም አይቀሬ ነው።
እነሆ የሚያስተባብረንና በጋራ የሚያነሳሳንን ምክንያት አገኘን። መዘናጋታችንም ይብቃ! ማንዴላ በኦፕራ አንድ ጥያቄ
ቀርቦለት ነበር “ለመሆኑ ይህ ላንተ የተሰጠ መለኮታዊ የመሰለ ክብርንና በዚያ ደረጃ ከእስርቤት ውጪ ለመኖር መቻልን
እንዴት ታየዋለህ?” የሚል ይመስለኛል። ምላሹ በጣም የሚያስደስት ነበር ታላቅነቱንም የሚያመለክት። እኔ ከዚህ በሁዋላ
No comments:
Post a Comment