መድረክ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የተፈጸሙበትን በደሎች ዘርዝሮ አቀረበ
የካቲት ፪(ሁለት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የሆነው መድረክ እንደገለጸው በደቡብ እና በኦሮምያ ክልሎች ለምርጫ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ አባሎቹ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል።
በደቡብ ክልል በቡርጂወረዳበላድሼቀበሌ የመድረክአባላትናደጋፊዎችሆናችሁዋል በሚል 10 አርሶ አደሮች መሬታቸውን ተነጥቀዋል። አቶማርሳካሳ፣አቶአይላአዶ፣ አቶአድማሱጩቻ ፣ አቶታምሩተስፋየ ፣ አቶሺኮጋሞ ፣ አቶመርከቤመጮላ፡አቶደጀኔዘውዴ ፣ አቶጨብቄጠቆ ፣ አቶተክሉታደሰ እንዲሁም አቶበዙዱቤ የእርሻመሬታቸውንከመንጠቃቸውምበላይእያንዳንዳቸው 200 ብርእንዲቀጡከተደረገ በሁዋላ፣ የተወሰደባቸው መሬት የኢህአዴግ ካድሬዎች ለሆኑት ለአቶ ዳዊትጫካ፣ አቶሶዬጩርቄ ፣ አቶመኮንንህርቦ፣ አቶደሳለኝማሬ እንዲሁም አቶቦጋሌቦኮለተባሉትተከፋፍሎ መሰጠቱን ገልጿል።
በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶመርከቤመጮላ ፣ አቶጨብቄጠቆ እና አቶታደሰጣሶየተባሉትአርሶአደሮች ደግሞ የመድረክአባላትናደጋፊዎችናችሁተብለውለከብቶቻቸውየገንዲበሽታመድኃኒትእንዳይሰጣቸውተከልክለዋል። አቶታደሰጣሶየተባለአርሶአደርከኦሞማይክሮፋይናንስብድርእንዳያገኝበቀበሌውሊቀመንበርበአቶጂሎአንዶመከልከላቸውንም መድረክ ገልጿል።
ጠንካራየመድረክአባልየሆኑት የአቶለማባሆናህጻናት ልጆች ደግሞክትባትእንዳያገኙመሰረትበለጠ በተባለ የጤናኤክሰቴንሽንባለሙያመከልከላቸውን መድረክ አስታውቋል። የግለሰቡ የተወሰነየእርሻመሬትለትምህርትቤትሥራይፈለጋል በሚል መወሰዱን፣ ለቤትመሥሪያያዘጋጁትንፍልጥሌሊት እንዳቃጠሉባቸው፣ ለወራጅናለቋሚያዘጋጁዋቸውን እንጨቶች አቶአለሙአዲሱየተባሉየቀበሌታጣቂእንደወሰዱባቸው መድረክ ገልጿል። 18 ኩንታልበቆሎአቶሉጬጠቃሎየተባለአንድየቀበሌውነዋሪበመኪናአስጭኖየወሰደባቸው ሲሆን፣ ለቀበሌውአመራሮችቢያመለክቱም ከተቃዋሚአባልጋርድርድርየለንምበሚልሰሚአጥተው ቀርተዋል።
በኦሮሚያክልል ደግሞ በኢሉባቦርዞንበገቺቦረቻናበበደሌምርጫክልሎችእንዲሁምበወለጋዞንበሆሮጉዱሩጅማገነትምርጫከልልየመድረክዕጩዎችንላለመመዝገብቢሮዘግቶበመውጣትናየትምህርትማስረጃከላመጣችሁበማለትሲያጉላሉመቆየታቸውን፣ በምዕራብሸዋዞንበጀልዱምርጫክልልደግሞከነጭራሹምየመድረክ ዕጩዎችንአንመዘግብምማለታቸውን መድረክ ገልጿል።
በቡሌሆራወረዳምርጫክልልበመልካሶዳቀበሌቁጥር 1 ምርጫጠቢያ ፣ 57 ነዋሪዎችየተቃዋሚደጋፊስለሆናችሁአንመዘግባችሁምተብለውስለተከለከሉጉዳዩለሚመለከታቸውአካላትአቤቱታቸውንበማቅረብላይይገኛሉ፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች የሰማያዊ አባላት በእጩነት እንዳይመዘገቡ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የቀድሞ አንድነት የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቀለው አቶ ስንታየሁ ቸኮል የትውልድ ቦታው በሆነው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ በእጩነት እንዳይመዘገብ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች እንቅፋት እንደፈጠሩበት ጋዜጣው ዘግቧል።
ከዚህም በተጨማሪ በሞጣ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በባሌ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በተቀመጠው ጊዜ እንዳይመዘገቡ እንቅፋት እየተፈጠረባቸው ነው ሲል ጋዜጣው አትቷል፡፡
በሌላ በኩል የጋራ ምክር ቤት አባል የሆኑ ፓርቲዎችን እጩዎች በስልክም ሳይቀር እየጠሩ እንደሚመዘግቡ፣ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ምዝገባ ጣቢያ ድረስ ሄደው ለመመዝገብ ሲያመለክቱ እንቅፋት ሲፈጥሩባቸው የብአዴን እጩዎች በአንድ ሰው ተወካይነት እንደሚመዘግቡ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። sourse esate radio
No comments:
Post a Comment