Friday, June 12, 2015

አይ ኦ ኤም 200 ኢትዮጵያውያንን ከየመን አስወጣ

Amharic

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 200 ኢትዮጵያውያንን የጫኑ 2 ጀልባዎች ከ24 ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ በሁዋላ ጅቡቲ በሰላም ደርሰዋል።ኢትዮጵያውያኑ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወደ አዲስ አበባ ይጓጓዛሉ።
በየመን አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። በአገሮቱ ከሚኖሩት ከ80 ሺ በላይ ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩት ከ2 ሺ አይበልጡም።
በየመን ያለውን ጦርነት ለማስቀም ውይይቶች እየተደረጉ ቢሆንም እስካሁን የረባ ውጤት አላስገኙም።

No comments: