Friday, April 22, 2016

ስደት፣ መከራ፣ እስራት፤ ለምን

ሰዎች  በተለያየ  መልኩ  ሀሳባቸውን  ሲገልጹ  በማሰተዋል  እና  በትኩረት  እንመለከታቸዋለን  የሁላችንም  ሀሳብ እንዳመለካከታችን  ብሎም  እንደአሰተሳሰባችን  እኛ  በገመትነው  ሁኔታ  ለመግለጽ  እና  ለማሰረዳት  እንሞክራለን  ነገሮችን በቅንነት  ወይም  በመልካም  ጎን  ማንፀባረቅ  ማሳየት  የምንችልበት  ሁኔታዎች  ማዳበር  በሰዎች  ህሊናውስጥ  እንዲሰርፁ  እኛ ምሳሌዎች  ሆነን  መቅረብ  አለብን

በመንፈሳዊ  ህይወትም  እንዲይላል  የእግዚአብሔር  መንፈስ  አንድ ነው  ፀጋ  ግን  የተለያየ  ነው  ይህም  ማለት  ለምሳሌ የመስበክ  ወይም  የማስተማር  ፣የመዘመር  ሌሎችም  የመሳሰሉት  እንደተሰጠው  ፀጋ  በመንፈሳዊ  ህይወት  ያገለግላል  ማለት ነው  ወደ  ፖለቲካው  ስንመጣ  የስነፁሁፍ  ችሎታ   ያለው  በመጻፍ ፣ ህዝብን  ለለውጥ  የሚያስተባብር  የሚቀሰቅስ የሚያደራጅ  በማደራጀት  ፣ በፋይናንስ  ወይም  የኢኮኖሚ  ድጋፍ  የሚያደርግ  በሀብቱ ፣ ከተለያዩ  ሚዲያዎች  ወይም የዜና ጣቢያዎች  የሚያገኛቸውን  ኢንፎርሜሽኖችን  የሚያሰራጭ  ሁሉም  እንደችሎታውና  እንደአቅሙ  እንደፍላጎቱ  የበኩሉን አስተዋጾ  ካደረገ  አንደኛው  ካንደኛው  የሚያንስበት  እና  የሚበልጥበት  ሁኔታ  የለም  ሁሉም  እንደመልካም  አስተሳሰቡ  ነው
ሁሌም   በመልካም   ስራቸው   የምንወዳቸው   የምናከብራቸው   የትግል   አርያነታቻውን   የምንከተላቸው  የሚያስተምሩን  በርካታ   ኢትዮጵያኖች  ሰፊውን   ግዜያቸውን   እውቀታቸውን፣  ህይወታቸውን ፣  ገንዘባቸውን ፣   በየእስርቤቱ   ያለአግባብ  የሚሰቃዩ   ስለህዝቦች   ነጻነት ሲሉ  መሰዋትነት  የሚከፍሉ  ብዙ  ኢትዮጵያኖች   አሉን  ዘወትር   የወያኔን  ዘረኛ  መንግስት በምንመልኩ  እናስወግድ  በሚለው  ላይ ነው  ትኩረታቸዉ   እንጅ ስለግለሰቦች  ወቀሳ ማቅረብ  አይደለም፣፣  በሌላምመልኩ ደግሞ   አንዳንድ  ግለሰቦ ች ከእኛ  ዉጭ  ኢትዮጵያዊነት ፣አዋቂ   ለአሳር  ነዉ፣  እን ዲያዉም   ከኛ  ዉጭ  ፉጬት  አፍ ሟሞጥሞጥ ነዉ፣  የሚሉ አካላት  አሉ፣፣   ምናልባት   ከዉስጥያለ   ኢትዮ ጵያዊነት፣ ወይም   ለወገን   ተቆርቋሪነት  ሊሆን ይችላል፣፣  ይህ  ስሜት   በሁላችንም   ወስጥያለ  ነገር   ቢሆ ንም  የሚንገልጽበት   መንገድ ሊለላይ ይችላል፣፣ አንዳንድ ሰዎ ች አቅማቸዉንና   እዉቀታቸዉ  በሚፈቅደዉ  ደረጃ የሚያደርጉትን  መልካም  ስራ  በሰዎች  ዘንድ  ለታይታ   ወይም  እዉቅና   ለማግኘት   ብቻ   ሳይሆን   በመጀመርያ   ደረጃ  እንደሰብዓዊ   ፍጡር   ማለትም   እንደ   ሰዉ   ከዛም   ቀጥሎ  እንደ ኢትዮጳያዊነት   ለሃገር እና  ለወገነ   ምን  ማድረግይገባኛል   ብለዉ   በሚኖርበትሃገር   ወይንም   አከባቢ  ያለዉን  የወያኔን የግፍ  አገዛዝ  በመቃዎምና  በማውገዝ   እንደሁም   የትግሉ   ተካፋይ   በመሆን፣   ኢትዮጵያ   የሁሉም   ብሄርና   ብሄረሰቦች ሃገር   መሃኑዋን   በተቃራኒወ  ደግሞ   የአንድ  ብሄርየበላይነት  የሚንጸባረቅበት  በሁሉም  መስክ  ማለትም  በኢኮ ኖሚ ፖሊቲካና   ወታደሪዊ  ሃይላት ሁሉንም  ተቆ  ጣትረዉ እንደያዙት፣፣

ለኢትዮጵያ      ያሰብነዉን   የነጻነት፣  የፍጥ ፣ የዲሞ ክራሲ እና   የእኩልነት  ሃገር  መገንባት  የሚንችለዉ፣፣  የተወሰኑ ሰዎች   መስዋእትነት   እየከፈሉ፣  የእነሱን ችግር   በማራገብ  ብቻ  የሚገኝ  ነጻነት  የለም፣፣  እያንዳንዱ  በያለበት  ቦታ በሃሳብ፣  በቁሳቁስ  ወይንም  በገንዘብ  ድጋፍ  የትግል  አጋርነቱን  መግለጽ  አለበት፣፣ሁልግዜ  ሰዎችን  ስንወቅስ  ስንኮንን  እንታያለን  በርግጥም  የሚወቀሰው  በአግባቡ  መወቀስ  አለበት  ሁላችንም  አመልካች ጣታችን  ወደ  ሰዎች  ስንቀስር  ሶስቱ  ጣታችን  ወደራሳችን  መሆኑን  አናስተውልም  ይህን  ለማለት  ያነሳሳኝ  አብይ  ነጥብ የራስን  ምሶሶ  የሚያክል  ጉድፍን  በአይናችን  ውስጥ  እያለ የወንድማችን  ወይም  የእህታችን  ስንጥር  የሚያክል  ጉድፍን መመልከት  እንወዳለን  እከሌ፨ሊት  ምንሰራ፨ች  ወይም  ምንድነው፨ናት  ከማለት  የልቅ  እኔ ምንሰራው  እኔ  ማነኝ  ብሎ  እራስን  መጠየቅ  አስተዋይነት   ነው።

Sunday, April 17, 2016

Ethiopia: Death toll from raid rises to 208, 108 children kidnapped


(Reuters) The death toll from a raid carried out by South Sudanese gunmen in western Ethiopia has risen to 208 people and the assailants kidnapped 108 children, an Ethiopian official said on Sunday.
An Anuak woman at work in Abobo, a village in Ethiopia’s Gambella region.
The attack took place on Friday in the Horn of Africa nation’s Gambela region which, alongside a neighboring province, hosts more than 284,000 South Sudanese refugees who fled conflict in their country.
By Sunday afternoon, the number had risen to “208 dead and 75 people wounded” from 140 a day earlier, government spokesman Getachew Reda told Reuters, adding the assailants had also abducted 108 children and taken 2,000 head of livestock.
“Ethiopian Defense Forces are taking measures. They are closing in on the attackers,” he said.
Getachew did not give further details, but officials in Gambela said on Saturday Ethiopian troops had crossed the border in pursuit of the attackers.
Cross-border cattle raids have occurred in the same area in the past, often involving Murle tribesmen from South Sudan’s Jonglei and Upper Nile regions – areas awash with weapons that share borders with Ethiopia.
Previous attacks, however, were smaller in scale.
The gunmen are not believed to have links with South Sudanese government troops or rebel forces who fought the government in Juba in a civil war that ended with a peace deal signed last year.
South Sudanese officials were not immediately available for comment.
Under pressure from neighboring states, the United States, the United Nations and other powers, South Sudan’s feuding sides signed an initial peace deal in August and agreed to share out ministerial positions in January.                                            source http://ecadforum.com/

Friday, April 15, 2016

በኦሮምያ ዜጎች መገደላቸውን አላቆሙም


ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ የሆኑትን ቫይበር እና ዋት ስ አፕ የመሳሰሉትን በመዝጋት በኦሮምያ ክልል የሚፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፋ እንዳይሆኑ እያደረገ ነው በሚል ትችት እየቀረበበት በሚገኝበት በዚህ ጊዜ፣በክልሉ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት መቀጠሉን ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ በጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወረዳ ሙጋድ ቀበሌ ውስጥ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን አጠናቆ ወላጆቹ ቤት ይኖር የነበረው ግርማ ገልጁ ኪጋ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎአል፡፡ ወጣቱ ቀደም ብሎ በደህንነቶች ሲፈለግ እንደነበር የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም አንድ ታርጋ በሌላት ነጭ መኪና የተጫኑ የደህንነት አባላት ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ ወጣት ግርማን አስቁመው በጩቤ ከወጉት በሁዋላ፣ እንደገና ከወደቀበት ተነስቶ ለማምለጥ ሲሞክር በጥይት ደብድበውታል፡፡የጥይት ሩምታውን የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ ወደ ቦታው ሲሄዱ፣ ደህንነቶች ጥይት በመተኮስ ህዝቡ እንዳይቀርብ ያደረጉ ሲሆን፣ ወዲያውኑ ሙዋቹን ይዘው ወደ ክብረመንግስት ወይም አዶላ ሆስፒታል በመውሰድ ጥለውታል፡፡
ወላጆቹ አስከሬኑን ሆስፒታል ሄደው የወሰዱ ሲሆን፣ የቀብር ስነስርአቱም ትናንት በመጋዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሶዱ በሚባል ቦታ ላይ ተፈጽሞአል፡፡
ነዋሪዎች እንደሚሉት ደህንቶች ከምሽቱ 12 ሰአት በሁዋላ በእየቤቱ ሳይቀር እየገቡ ህዝቡን በማስፈራራት ላይ ናቸው፡፡ሌሊቱን እንደሚዳቁዋ እየባነን ነው የምናሳልፈው የሚሉት ነዋሪዎች፣ ከምሽቱ 12 ሰአት በሁዋላ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡
በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚታሰሩ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
መንግስት ተቃውሞውን በሃይል ለማቆጣጠር ሙከራ ቢያርግም በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም አልፎ አልፎ ተቃውሞዎች ይካሄዳሉ፡፡
በክልሉ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ እስ 300 የሚደርሱ ሰዎች በመንግስ የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸው በተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወቃል፡፡                      source http://amharic.ethsat.com/

Thursday, April 14, 2016

እነ አቶ ዓለማዬሁ መኮንን በድጋሜ ተቀጠሩ


ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከመጋቢት 20፣ 2008 ዓም ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ አንድነት የዞኑ ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ፖሊስ የጠየቀባቸውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጨርሰው ሚያዚያ 05 2008 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው ለሚያዝያ13/08) ተቀጥረዋል ፡፡
በችሎት ላይ የተገኙት የኦህዲኅ አባላትና የታሳሪዎች ቤተሰቦች እንደገለጹት ፖሊስ መረጃ የማሰባሰብና የምርመራ ሥራውን አላጠናከኩም በሚል የ14 ቀን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ‹‹ ጥያቄው አግባብ ያለመሆኑን፣ባልተሰበሰበ መረጃና ባልተደረገ ምርመራ ተጠርጣሪዎችን ማሰርም ሆነ እዚህ ድረስ ማምጣት ከህግ አሰራርም ሆነ ከሰብዐዊ መብት አኳያ አግባብ አለመሆኑን ›› በመጥቀስ ፖሊሶችን ከገሰጸ በኋላ ፣ ‹‹መዘንጋት የሌለበት እነዚህ ሰዎች በጠባብ ቦታ ነው ያሉት ፣ እኛ ደግሞ በሰፊው፣ ስለዚህ የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ምን የተለየና ተጨማሪ ነገር ለማድረግ ነው ?›› ሲል ጠይቋል፡፡ ፖሊስ በሰጠው መልስ- የሰው ማስረጃዎችና ተጨማሪ መረጃዎች እያሰባሰብን ያለነው ከዞኑ- ጂንካ በመሆኑ ከቦታው ርቀትና ከዞኑ ፖሊስ ጋር ስለምንሰራ ነው ብሎአል፡፡ አቶ ዓለማዬሁ በበኩላቸው ‹‹ ከጅምሩ የታሰርነውና ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ወደሌለበት ያመጡን ያለአግባብ ነው፣ አሁን እየተጠየቀ ያለው የጊዜ ቀጠሮም ምንም በሌለበት እንዲሁ ለማንገላታት ነውና ፖሊስ አለኝ የሚለውን ማስረጃና የምርመራ ውጤት ያቅርብ ፣ ይህ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በነጻ ያሰናብተን ዘንድ እንጠይቃለን››ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ካደመጠ በኋላ ‹‹ የአንድ ሳምንት ጊዜ ይበቃችኋል›› በሚል ለመጪው ሃሙስ ሚያዝያ 13, 2008 ዓ.ም. ፖሊስ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቦ፣ ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርብ ሲል ቀጠሮ ሰጥቷል ፡፡ በተጨማሪም በዛሬው ችሎት ታሳሪዎች ከመያዛቸው አስቀድሞ ቤታቸው ሲፈተሸ የነበሩ እማኞች በችሎት ያለመቅረባቸው ተረጋግጧል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢሳት እነ ዓለማዬሁ ከመታሰራቸው ጥቂት ቀናት በፊት በዞኑ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸመውን የመሬት ቅርምት፣ ይህም በዞኑ ልማት ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖና የመሬት ቅርምቱ ከ98 ከመቶ በላይ የተፈጸመው በህወኃት አባላትና ደጋፊዎች መሆኑንና በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ዓለማዬሁና የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ አስተያየት መስጠታቸውን መዘገቡ ይታወሳል ፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ የዞኑ መስተዳድር በዞኑ ነዋሪዎች የተቋቋመ ‹ነጻ› በሚባል የልማት ማህበር ጋር የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ለማዘጋጀት ህዝቡን በመቀስቀስ ላይ መሆኑን፣ ለዚሁ ባዛር መምህራንን ለማሳመን በየትምህርት ቤቱ …..በመሰብሰብ ያወያየ ሲሆን ፣ ከመምህራን የተለያዩ ጥያቄዎች መነሳታቸውንና ለዚህም በቂ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ሰፊ ውይይት ለማድረግ በመወሰን ስብሰባዎቹ ማብቃታቸውን መምህራን ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ት/ቤቶች በተደረጉ ስብሰባዎች ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል ፣ ከዚህ በፊት በተደረገው ባዛር የተሰበሰበው ገንዘብ አጠቃቀምና በገንዘቡ ለመስራት የተነደፉ ፕሮጀክቶች ክንውን /አፈጻጸም ሪፖርት ሳይቀርብ ስለሌላ ባዛር ማቀድ አግባብ ነውን ፣ ሌላ ዕቅድ ከማሰባችን በፊት ከዚህ በፊት በህዝብ ሃብት የተገዙ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች / ዶዘርና ግሬደር፣ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ/ ያለአገልግሎት የቆሙት ለምን እንደሆን በግልጽ ይታወቅ፤ ከዚህ በፊት በህዝብ ገንዘብ የተገነባው ስታዲዬም ከፍተኛ ገንዘብ ወጣበት ተብሎ በተነገረ በወራት ውስጥ መደርመሱ/መፍረሱ ይታወቃል፤ ይህ ሁኔታ እንዲጣራ ጥያቄ ቢቀርብም መልስ ባልተሰጠበት እንደምን ሌላ ባዛር ማዘጋጀት ታሰበ ፣ በተመሳሳይ በዕቅድ ተጀምሮ የተቋረጠው የጂንካ ቤቶ-ሜላ መንገድ የተቋረጠበት ምክንያት አሳማኝና ግልጽ ምክንያት ባልቀረበበት በባዛር ስም ከህዝብ ለምን ገንዘብ መሰብሰብ ተፈለገ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
አንድ መምህር -እውነት ዛሬ ላይ ለጂንካ ከተማ የሚያስፈልገው የምግብ እህል ነው ወይስ የሽንት ቤት መምጠጫ መኪና- ለመሆኑ ምን ተበልቶ ? የሚል ጥያቄ አንስተው በተሰብሳቢው ከፍተኛ ጭብጨባ ተችሮኣቸዋል፡፡
መምህራኑ ‹‹ ማናችንም የዞናችንን ልማት እንፈልጋለን፣ ከፍላጎት ባለፈም በአቅማችን መሳተፍና አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለብን እንረዳለን፤ ግን በልማት ስም ገንዘብ እየተሰበሰበ ተጠያቂነት በሌለበት ሁኔታ የሙስና ደላላና ተጠቃሚ ግለሰቦችና ባለሥልጣናት ኪስ ማደለቢያ ሊውል አንፈቅድም ›› ብለዋል፡፡
ይህንኑ ባዛር በሚመለከት የኦህዲኅ የዞን ጽ/ቤት ምክትል ተጠሪ መምህር እንዲሪስ መናን በሰጡት አስተያየት ‹‹ ተመሳሳይ ጥያቄዎች እርሳቸው በሚያስተምሩበት ት/ቤትም በተደረገ ስብሰባ ላይ መነሳታቸውን አረጋግጠው፣ እንደ ህዝብና የዞኑ ነዋሪ ልማቱን የምደግፍ ነኝ፣ በመምህራን የተነሱት ጥያቄዎች በቂና አሳማኝ መልስ ማግኘት እንዳለባቸው አምናለሁ›› ከዚህ ባለፈ እንደ ፖለቲከኛ ‹‹ ይህ የአካባቢ ልማት ጉዳይ በቅርብ ጊዜ በዞናችን በኢንቨስትመንት ስም በህወኃት አባላትና ደጋፊዎች የተፈጸመው የመሬት ቅርምት ከተጋለጠና የህዝብ ውይይት አጀንዳ ከሆነ በኋላ እንዴት መጣ ፣ ለሽፋን የታሰበ ፖሮፖጋንዳ ይሆን ? በዚህ ጉዳይ የታሰሩ የእነ አቶ ዓለማዬሁ ጉዳይስ በዚህ ወቅት በዝምታ የሚታለፍ ነውን ? ከዚህ የልማት ኃሳብና ዕቅድ በፊት በዞናችን የሚታዩ ማህበራዊ ምስቅልቅሎች / የዜጎች መፈናቀል፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መሻከር – የቦዲና የኮንሶ ግጭት /፣ የሃመር ወጣቶች ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ተከትሎ ከመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ጋር የተገባው ቅራኔ ያስከተለው የህይወት መጥፋት፣ አካል መጉደል፣ የንብረት ውድመት፣የወጣቶች ከቀዬኣቸው መሰደድ፣….በአጠቃላይ ከዞኑ ነዋሪዎች የሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና በህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸው ፣ የህዝብ ብሶት ያሰሙ መሪያችን፣ አባልና የከተማው ነዋሪ በሃሰት ውንጀላ ከቤተሰብና ከዞናቸው ህዝብ ተነጥለው በእስር እየማቀቁ ባሉበት ይህን ለምን ? ብለው ሳይጠይቁ ‹ነጻ› ነን በሚል ስለልማት ቢሰብኩ በህዝብ ተቀባይነት ማግኘት አይታሰብም፡፡ ብለዋል፡፡
የኦህዲኅ ሊቀመንበር በሰጡት አስተያየት ደግሞ “ብዙ ከበሮ ተደልቆለት ከወራት በላይ ዕድሜ ከሌለው ድንጋይ ድርዳሮ በፊት የዜጎች መብትና የሰው ሃብት ልማቱ፣ የባለሥልጣናት ተጠያቂነት መቅደም አለበት፣ ለረጅም ጊዜ በተደጋጋሚ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች መመለስ፤ ሙስናው መገደብ…. አለበት፣ ስለቀጣዩ ብዙ ከማለታችን በፊት ካለፈው ምን ተምረናል ለሚለው ግልጽና በቂ መልስ ማግኘት፣ ፍላጎታችንና የልማት ጥያቄዎቻችን በአግባቡ ቅደም ተከተል ሊቀመጥላቸው ይገባል›› ብለው እንደሚያምኑና እነዚህ በሆኑበትና በተሟሉበት ‹‹ ህዝብ በአንድ ልብ፣በአጭር ጊዜ ተዓምር የመስራት አቅም እንዳለው በጽኑ አምናለሁ›› ብለው መናገራቸውን ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል፡፡                                                                                       source http://amharic.ethsat.com/ 

Friday, April 8, 2016

እሪይ በይ ሀገሬ

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለች ግን ከዓለም በጣም ደሃ ተብለው ከሚመደቡት ውስጥ የመጨረሻው ጠርዝ ላይ የሰፈረች፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠረው በርሃብና ቸነፈር ለረጅም ዓመታት የሚሰቃይና የውጭ አገር እርዳታ እጅ ጠብቆ የሚያድር ሕዝብ የሚኖርባት አገር ናት።ከድህነቱ በተጨማሪም ባለመረጋጋት፣የሕዝብ መብት የተረገጠባትና አምባገንን የሚፈነጭባት ከመሆኑ አንጻር የመጀመሪያውን ቦታ ይዛ ትገኛለች።በየእለቱ የመረጋጋትና የሰላም ኑሮ እየጨለመ የመጣባት፣ስጋት የሰፈነባት፣ ሕዝቡ በጎሳ ተከፋፍሎ በጠላትነት እንዲጋጭና እንዲተያይ የሚያደርግ ጎሰኛ ቡድን ስልጣኑን ይዞ ያሻውን የሚያደርግባት አገር ነች። ይህም ብቻ አይደለም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሰርቶ አዳሪው በተለይም ከተሜው አንድ ጊዜ በቀን እህል ቀምሶ ለማደር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።የገበያ ዋጋ ሰው ገዝቶ ከሚችልበት አቅም በላይ እየሆነ የበይ ተመልካችና ለጥቂቶች ገነት ለብዙሃኑ ሲኦል የሆነች አገር ሆናለች።
አገሪቱ በእድገት እየመጠቀች ነው ተብሎ ቢለፈፍም የሕዝቡ ኑሮ ያው በገሌ ነው።ብስቁል ፊቱና የሰውነት ቅርጹ፣ከአለባበሱ ጋር ሲታይ በሃያአንደኛው ክፍለዘመን ውስጥ የሚኖር አይመስልም።
በከተማና በገጠር የውሃና የሃይል ምንጭ አለመሟላት፣የመገናኛ መስመር በብቃት አለመዘርጋት፣ መሪዎች ተለዋወጡባት እንጂ በአገሪቱ አጠቃላይ ገጽ ላይ ለውጥ እንዳልመጣ በጉልህ ይታያል። አደገኛ የመኪና መንገድ ካለባቸው አገሮች መካከል በአንደኛ ደረጃ የተመደበች አገር በመሆኗ በአደጋ የሚሞተውና አካለ ጎደሎ የሚሆነው ቁጥሩ ከፍተኛ ነው። ወጣቱ ስራ አጥ በመሆኑ ለመኖር ሲል ወደ ውጭ ለመሰደድና በአደገኛ ተግባር ላይ ለመሰማራት የሚሻው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። በመንግሥት የመልካም አስተዳደር አለመኖር “ተከተል አለቃህን” ሆኖ በሕዝቡ ላይ የመልካም ምግባር ድህነትን አስፍኗል።መሪዎቹ ቢለዋወጡም በአገሪቱ ላይ መሰረታዊ የስርዓት ለውጥ አልመጣም።
አሁን ስለራሱ እንጂ ስለአገርና ወገኑ ቀርቶ ስለቤተሰቡ የሚያስበውና የሚጨነቀው እየተመናመነ መጥቷል።ብሔራዊ ስሜት ፣የአገር ፍቅር፣ቀናነትና፣መቻቻል ያለፈበት ተረት ሆኖ በቦታው አጭበርባሪነት፣ዘረፋ፣ውሸት፣ጎሰኝነት የዘመኑ እውቀት እየሆነ መጥቷል።
በመንግሥትና በደጋፊዎቹ የሚታየው የኑሮ ለውጥ ለአገሪቱና ለሕዝቡ ኑሮ መመዘኛ ሊሆን አይችልም።በስርዓቱ ባለቤቶች ከሚፈጸመው ጸረ ሕዝብ ወንጀሎች ጎልቶ የሚታየው የአገሪቱን ቅርስና ንብረት በተለይም ለእርሻና ለቤት መስሪያ የሚሆኑትን የገጠርና የከተማ መሬቶች ከሕዝቡ እየቀማ የንግድ ሸቀጥ በማድረግ የሚካሄደው ዘረፋ ነው። ሕዝብ ለዓመታት በውርስና በግዢ የኖረበትን ቦታ እየቀሙ በማይችለው የዋጋ ተመን መልሶ እንዲገዛ ካልቻለም ለቆ እንዲሄድና ቤት አልባ እንዲሆን በማስገደድ ቦታው ለሚችል እየተሸጠ ገንዘብ በመሰብሰብ የሚካሄደው የማፍያ ስራ በየእለቱ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።የቀን ገቢው በአማካኝ አንድ የአሜሪካ ዶላር በሆነው ሕብረተሰብ የኤኮኖሚ አቅም በሚሊየን ዶላር የሚገመት ቦታና ቤት ገዝቶ ለመኖር ማን ይችላል፧ ተብሎ ቢጠየቅ ፣መልሱ በስልጣን ላይ ያሉትና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የውጭ አገር ከበርቴ ዜጎች ብቻ ለመሆናቸው አሰላለፋቸውን ና የባለቤትነት ሰነዶቹን ማየቱ ብቻ ይበቃል።
ተወላጁ ከመሬቱ እየተነቀለ በገዛ አገሩ ስደተኛ ሲሆን፣ሕጻናት የመንገድ ላይ ተዳዳሪ ሲሆኑ፣ቦታቸውን የሚወርሱት መክፈል የሚችሉት የውጭ አገር ከበርቴዎች ፣አረቦች፣ቱርኮች፣ሕንዶች፣…ወዘተ ናቸው።ለዚህም ነው ላለፉት ሶስት ወራት የተካሄደው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ሊነሳ የቻለው።እንቅስቃሴው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ብሶት የወለደው እንጂ የአንድ ነጠላ ማህበረሰብ ጉዳት ብቻ ያነሳሳው አይደለም።
አገሪቱ በእድገት ላይ ነች ቢባልም በገሃድ የሚታየው እድገት ሕዝቡን ሰንጎ የያዘው የኑሮ ውድነቱ ብቻ ነው።ለቤት ኪራይ፣ለምግብ፣ለሕክምና ፣ለትምህርት፣ለመጓጓዣ፣ለልብስና ንጽህና …ወዘተ የሚጠየቀው ክፍያ ሕዝቡ ከሚያገኘው ገቢ ጋር የሰማይና የመሬት ያህል ይራራቃል፣እጅግ በጣም አድጓል።ከሌሎቹም አገራት የኑሮ ውድነት ጋር ሲነጻጸር ያስደነግጣል።
ሁኔታውን ተመሳሳይ እድገት ካላቸው ያፍሪካ አገሮች ጋር ለማወዳደር ቢሞከር ሌላውን ትተን በመሬት ዋጋ ያለው ልዩነት አያድርስ ነው።ለዛውም በሌሎቹ መንግሥት የመሬቱ ባለቤት ባልሆነባቸው አገሮች፣በሊዝ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ የባለቤት ይዞታ መብትና እውቅና በሰፈነባቸው አገሮች ጋር ያለውን የዋጋ ተመን ብናስተያየው ሰሚ የለም እንጂ ኡኡ ያሰኛል። የመሬት ባንክ የሚል ፈሊጥ በኢትዮጵያ ካልሆነ በቀር በሌላው አገር አይታወቅም።የባንኩ ባለቤት ደግሞ ሕዝብ ሳይሆን የስልጣኑ ባለቤቶች ናቸው
በመሬት ዙሪያ በኢትዮጵያ ያለው ።በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ዳሞትራ እንደምትባለው ባለብዙ አፍ የሸረሪት ዘር በየአቅጣጫው ዘረፋ የሚያከናውንበት ጠንካራ መረብ ዘርግቷል።ይህን የብዝበዛ መረብ ለመበጣጠስና ሕዝቡን ከዚህ የተደራጀ የማፊያ ስርዓት ለመውጣት የተደራጀ ትግል ማካሄድ ያስፈልጋል፤ ሕዝቡም ተባብሮ የተጣለበትን የዋጋ ተመን አልከፍልም ማለት ይገባዋል።በተግባር የሚታየው ግን በተናጠል የባለስልጣኖቹን ፍላጎት እየተቀበለ ማደር ሆኗል፣በጎሳ ተኮር ትግል በተናጠል ለእልቂት መጋለጥ፣መጮህና መርገም መልስ አይሆንም። መንግሥት የዘረጋውን አንድ ለአምስት የስለላ ሰንሰለት ሕዝቡ በግልባጩ አምስት ለአንድ አድርጎ ሊቆጣጠረውና ሊበጣጥሰው ይገባል።ቁርጠኝነት ከብዛት ጋር ሲቀናጅ የሚቋቋመው ሃይል አይኖርም። በውጭ አገር የሚኖረውም ኢትዮጵያዊ ለቁራሽ መሬት ሲል ከአውሬ ስርዓት ጋር እየተባበረ የሕዝቡን ስቃይ ባያበዛው መልካም ነው።የዃላዃላ ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ መሆን አይቀርም።

Wednesday, April 6, 2016

Beatings, torture against detainees at Tolai Military Camp, protest in Oromia continues


Security forces are beating and torturing the nearly three thousand people detained at the Tolai Military Camp. The detainees were incarcerated in mass in the ongoing anti-government protest in the Oromia region for political and economic rights that is well into its fifth month.
Quoting his sources, Berhanu Lenjiso, a social scientist who closely follow the protest in the Oromia region, told ESAT that there were 2,800 people detained at the Tolai Military Camp and the detainees were being beaten and tortured by the Oromia police and prison guards. He said, according to his sources, the TPLF officers were the ones directing the beating and torture behind the scene.
He said the majority of the detainees were from the Oromia regional state, but there were also prisoners from South Ethiopia, Gambella and Benishangul regional states.
Some members of the police who were forced to perpetrate the torture against the detainees have begun challenging the instructions coming from the TPLF officers.
Meanwhile, the protest in the Oromia region resumed on Monday in Sululta town, few miles from the capital Addis Ababa. Seven students have been arrested following the protest, according to OMN.
In another development, a fire has reportedly broke out at the Haromaya University today. Students told ESAT that the fire engulfed four buildings, which were student dormitories. Students’ belongings were damaged by the fire but the sources could not tell if there were injuries to the students.
The University has been the center of the protest by the people in the Oromia region against years of marginalization by the tyrannical minority government. The University was partially open despite ongoing protests in the region.                                                                                                                                                                                             sourcehttp://ethsat.com/ 

Sunday, April 3, 2016

A forum of political parties say regime arrested 2,627 people in the Oromia region in the last three weeks


ESAT News (April 2, 2016)
The Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, also known as Medrek, said in a statement on Friday that the regime arrested 2,627 people in the Oromia region in the last three weeks alone.
The statement said the figure only refers to the number of people arrested after the Prime Minister apologized in a televised speech for the killing and injuries the TPLF special forces perpetrated against peaceful protesters in the Oromia region.
Medrek said the Premier’s apology was not a sincere and it was just a PR stunt made to impress Western donors.
The arrests were mainly in West Arsi, 1200 and West Hararge 1000, as well as in Wollega and West Shewa among others.
Medrek called for the release of all prisoners and demanded the perpetrators of the killings to be brought to justice. Opposition political parties estimate at least 500 protesters were killed in the four months of protest in the Oromia region. The recent arrests would bring the total to at least 8000.                                                 source  http://ethsat.com/