Friday, December 20, 2013

ስትራቴጂ አልባ ተቃዋሚዎችን ማዳመጫቸውን ወያኔ እና ዲያስፖራው ደፍነውታል!!! by ========= ምንሊክ ሳልሳዊ =



ለላሸቀው የዲያስፖራው ፖለቲካ የፈጠረው ጫና ስለ ፖለቲካ እውቀት ያሌላቸው ሰዎች በደመነፍስ ፖለቲከኛ እየሆኑ መምጣት በሃገር ውስጥ ትግል የፖለቲካ ስትራቴጂ እና ታክቲክ እንዳይኖር አድርጓል::
                                   =========  ምንሊክ ሳልሳዊ ============
የወያኔውን ጁንታ አተኩረን በብዛት የምንተቸው የህዝብ አደራ ተቀብያለሁ ብሉ በተጭበረበረ ፖለቲካ ለግላዊ እና ቡድናዊ ጥቅሞች በመቆም አገን እና ህዝብን ወደ ገደል ከቶ በሙስና ተዘፍቆ ህዝብን በድህነት አለንጋ እየገረፈ መሆኑ በቅርበት እያየን ሲሆን ይህንን የትግል ስልት እንደ ህዝብ ስንከታተል የስትራቴጂ አልባ ተቃዋሚዎችን በሰበ አስባብ መንደፋደፍ ደሞ እየታዘብን ነው:: የተቃዋሚዎች ነገር ሰልችቶናል ስለዚህ የአስተሳሰብ ዘይቤያቸውን ቀይረው እና ከስሜታዊ እና ካለፈ ፖለቲካ ወተው በሰለጠነ መንገድ የወያኔን ጁንታ በሰላማዊ ይሁን በትጥቃዊ መንገድ እንዲያስወጉ ለመለመን ሳይሆን ራሳቸውን ደጋግመው እንዲፈትሹ ለማሳሰብ ነው::

ባለፈው ጹሁፎች ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የኢሕኣዴግ የስልጣን እድሜ የረዘመው በግንባሩ ጥንካሬ ሳይሆን በተቃዋሚዎች ልፍስፍስነት ነው::ይህን አባባል አባባልነቱ በደረቁ ተወስዶ በኔ ስታይል ቢጻፍም አረፍተ ነገሩ የተወሰደው ከወያኔው የ 40 አመት የስልጣን መቆያ እቅድ ንድፈ ሃሳብ የተወሰደ ነው :: ወያኔ እንደሚለን በንድፈ ሃሳቡ ተቃዋሚዎች አቅም የሌላቸው ልፍስፍሶች ስለሆኑ ለስልታን ብቁ ባለመሆናቸው እንደፈለግን በመፈንጨት እስከ 40 እና 50 አመት በስልጣን ላይ ለመቆየት የታቀደ ነው::ለዚህ ምንም መልስ ያሌላቸው ተቃዋሚዎች የመስዋትነት እና የስትራቴጂ ቁርጠኝነት ያሌላቸው ተንክሮ ሊወጣ የሚፈልግ አመራር  በማቀጨጭ እና ለገዢው ፓርቲ በገንዘብ በመደለል ትግላቸውን እያቀጨጩት ይገኛሉ::

ሃገሪቷ ህገ መንግስት ቢኖራትም በስርኣት አልበኞች እየተጣሰ ህግ በህግ እየተሻረ እና ባለስልጣናት እየሸረሸሩት አማራጭ የፖለቲካ አመለካከቶች እና አስተሳሰቦች እንዳይንሸራሸሩ እና እንዳይወዳደሩ በማድረግ በህግ የተረጋገጠውን የብዙሃን የፓርቲ ስርኣት እንዳይሰፍን እንቅፋት ቢሆኑም ይህ ደሞ የተቃዋሚዎች ድክመት ታይቶ የሚወሰድ እርምጃ ነው::ብቁ እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ አለመገኘቱ -የአገር ጉዳይ የአንድ ሰሞን ሆሆይታ እና ትኩሳት ተከትሎ ማውራቱ -ፖለቲካ የትርፍ ሰአት ስራ- መሆኑ ያልበሰሉ እና የፖለቲካ ስልታዊ እውቀት ያሌላቸው ቦዘኔዎች በፓርቲዎች ዙሪያ መሰባሰባቸው - በሚገባ የተደራጀ፣ አቅሙን እያጎለበተና ለሕዝቡ የተሻለ አማራጭ የሚያቀርብ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አለመኖር በኢትዮጵያ የሚፈለገውን ለውጥ አለማምጣቱ የታወቀ ጉዳይ ነው::ሰበብ የማያጡት ተቃዋሚዎች ይህንን ማድረግ ያልቻልነው ወያኔ እንዳንጠናከር እያዳከመን እያንገላታን እያሰረን ነው ቢሉም ይህንን አሰራር የወያኔው ጁንታ እንዲቀይር መስዋትነት ለመክፈል ምንም ያደረጉት ነገር የለም::

በእርግጥ የወያኔው ጁንታ በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጫና በማድረግ ድርጅቶቹ እንዲቀጭጩ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሚናውን እየተጫወተ ነው:: ሆኖም ግን ተቃዋሚዎች ከታጋይነት ይልቅ ባለፈ ታሪክ የመኮፈስ- እርስ በእርስ የመወቃቀስ- ያለፉትን ስርኣቶች የመናፈቅ-ህዝብን በታሪክ ስም ለመደለል መሞከር-ከመስዋትነት ይልቅ ለጥቅም መገዛት-መረጃ መሸጥ -ለስልጣን መጓጓት የመሳሰሉት ድክመቶች ያሉባቸው ሲሆን ስሜታዊ እና ያልበሰሉ ቦዘነዎችን ሰብስቦ ቲፎዞ በማድረግ መንጠራራትም ያልቀረፉት ችግራቸው ነው::የወያኔ ተጽእኖ እና ጫና እዳለ ድርሻው ሳይካድ መጀመሪያ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል::በውስጣቸው የሚታየውን ችግር ቢያድበሰብሱትም በአደባባይ እያየነው ያለ ጉዳይ ነው፡፡

ተቃዋሚዎች ራሳቸው ቆራጦች፣ ጠንካሮች፣ ቅኖችና ለመስዋዕትነት ዝግጁዎች ቢሆኑ ኖሮ ከዚህ በላይ የተጠናከሩ ይሆኑ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከባድ እና ሊቃለል እንኳን ያልቻለ የመንግስት ጫና ....ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውስጣቸው በተሰገሰጉ የወያኔ ሰላዮች የታጠሩ ናቸው::ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአንድነት ችግር ....ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአደረጃጀት ችግር ...ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአመለካከት ችግር ...ተቃዋሚ ፓርቲዎች የውስጥ የዲሞክራሲ ችግር.....ተቃዋሚ ፓርቲዎች የደጋፊና የአባል ብዛት ችግር ....ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፋይናንስ አቅም ችግር ... ተቃዋሚ ፓርቲዎች የፖለቲካ መስመር፣ የስትራቴጂና የታክቲክ ችግር አለባቸው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ችግሮችን የሚፈቱበት መንገድ ራሱ ችግር አለበት፡፡

ተቃዋሚዎች ከዚህ በላይ ለተተቀሱት ነገሮች አትኩሮት መስተት እና ማስተካከል አለባቸው ስሜታዊነት እና የሆያሆዬ ፖለቲካ መቆም ያለበት ጉዳይ ነው::በውስጣቸው ያለውን አንድነት ማጠናከር እና የስርኣቱን ተላላኪዎች ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል:: የአደረጃጀት መዋቅራቸውን ማስተካከል በበሰሉ እና ወደፊትን ግብ በሚያደርጉ ጠንካራ እና ብቁ ፖለቲከኞች መታጠር አለባቸው:: አመለካከታቸውን ካረጀ እና ከታሪክ ምርኩዝነት አውጥተው በሰለጠነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ራሳቸውን ማስተሳሰር እና አማራጭ ሃሳቦችን በማሸራሸር ጠንካራ ብሄራዊነት መፍጠርና ለላሸቀው የዲያስፖራው ፖለቲካ ፊት አለመስጠት ስለ ፖለቲካ እውቀት ያሌላቸው ሰዎች በደመነፍስ ፖለቲከኛ እየሆኑ መምጣት የፖለቲካ ስትራቴጂ እና ታክቲክ እንዳይኖር አድርጓል:: ስለዚህ እነዚህ ጉዳዮች በጥራት እና በአጽንኦት አትኩሮት ከተሰጠባቸው ትግሉ ሊያብብ ይችላል:: ከዚህ ውጪ አሁን ባሉበት ሁኔታ ተቃዋሚዎች ከቀጠሉ የወያኔን እድሜ ከማስረም ዉጪ ምንም ፋ

No comments: