የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከ ማጣላት…
ዘንድሮ በኢትዮጵያ ተከበረ የተባለውን የብሄሮች ቀን ምን ያህሎቻችሁ እንደተከታተላቹህ አላቅም። ላላያችሁት ግንዛቤ ለመፍጠር ያህል… ዘንድሮ በአሉ የተከበረው ሱማሌ ክልል፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን በመንገር ወጋችንን እንጀምራለን። ይህ ዝግጅት እስከዛሬ በትግራይም፣ በአማራውም ክልል ተደርጓል… ሆኖም በአሉ ላይ ሁሉም የየብሄሩን ባህል ለማሳየት ሲጥር እንጂ፤ አንደኛው ብሄር ሌላውን ሲሰድብ ያየንበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚህ አመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ወይም የብሄረተኞች ቀን ሌላውን ኢትዮጵያዊ በመውቀስ ላይ የተመሰረተ ነበር።
“አማራው፣ ደገኛው፣ የመሃል አገር ሰው…” እያሉ ቀጠሉ አስተያየት
ሰጪዎቹ። በአሉን ምክንያት በማድረግ በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች ወቀሳቸውን ቀጠሉ፤ “የመሃል አገር ሰዎች ‘ሽርጣም ሱማሌ’ እያሉ ይጠሩን ነበር” አለ። እኛንም በሃሳብ ወደኋላ መለሰን። የመሃል አገር ሰው ይህንን ቃል አይጠቀምበትም ለማለት አይደለም። ነገር ግን “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን ቃል መስማት የጀመርነው፤ በኢትዮጵያ እና ሱማሌ ጦርነት ወቅት ነው። “ሽርጣም ሱማሌ” የሚለውን አባባል ሁሉም የመሃል አገር ሰው እንደማይጠቀምበት ሁሉ፤ በቴሌቭዥን መስኮት ላይ ብቅ ብለው ሌላውን ኢትዮጵያ የሰደቡት እና ያሰደቡትም መላውን የኢትዮጵያ ሱማሌ እንደማይወክሉ እናውቃልን። በመሆኑም ይህ ጽሁፍ በሁሉም የኢትዮጵያ ሱማሌዎች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን፤ የማያውቁትን ታሪክ ለማሳወቅ ያህል የተዘጋጀ መሆኑን ልብ ይበሉ።
(በዳዊት ከበደ ወየሳ)
No comments:
Post a Comment