መጋቢት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኬንያው ዘ ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገሪቱ በህገወጥ መንገድ በመግባታቸው እያንዳንዳቸው 2 መቶ ሺ ሽልንግ እንዲከፍሉ የኢሲዮሎ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል።
ሁሉ ም ስደተኞች ባለፈው ሰኞ ሳምቡሩ በተባለው ስፍራ ላይ የተያዙ ሲሆን፣ ተከሳሾች ያለፈቃድ ወደ ኬንያ መግባት እንደማይቻል ባለማወቃቸው ምህረት እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። ይሁን እንጅ ፍርድ ቤቱ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ወይም ለ3
ወር እንዲታሰሩ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
በየአመቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በመካከሉ ባሉ አገሮች እየተያዙ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ከፍተኛ ቅጣት ይተላለፍባቸዋል። ይሁን እንጅ አገሪቱን እየጣሉ የሚጠፉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር አሁንም ከፍተኛ ነው። sourse esat radio
No comments:
Post a Comment