Wednesday, February 24, 2016

“የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው” | ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር



የሕብር ራድዮ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ ኦዳ ጣሴን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ጥያቄዎችን በማንሳት አወያይቷቸዋል:: ቃለምልልሱ ቢደመጥ አያስቆጭም::
“ሕዝቡ እየተንቀሳቀሰ ነው.. መንግስት ቢወርድ ሃገሪቱን የመምራት ብቃት አላችሁ ወይ?”
“የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የማንንም ሕዝብ የሚነካ አይደለም… የኦሮሞ ሕዝብ የሌላውን ሕዝብም ትግል ይደግፋል”
“የኦሮሞ ሕዝብ ግንባር እና የኦሮሞ ሕዝብ ካለምንም ገደብ የሁሉም ብሔር ብሄረሰብ መብት እንዲከበር ነው የሚታገለው”
“ሕዝቡ ሞኝ አይደለም… ወያኔ ከወረደ ሃገሪቱ ትበጠበጣለች የሚለው አይሰራም; ትግላችን ከወያኔ እንጂ ከሌላው ሕዝብ ጋር አይደለም”
“ይህ እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት ያሰብነበት ጉዳይ ነው.. ወያኔ እንዲህ ያለውን ሴራ እንደሚሸርብ:: የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊምም ክርስቲያንም ነው:: መስጊድም ሆነ ክርስቲያን የማቃጠል ፍላጎት የለውም”
“ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ጉባኤ እናደርጋለን ለጊዜው ግን ትግሉን ማፋፋም ላይ ነው ትኩረታችን”
“የአዲስ አበባ እጣ ምንድን ነው የሚሆነው?”

Monday, February 22, 2016

ተቃዎሞ አድራጊዎች ላይ የሚፈጸመmው ግድያ እና እስር ለተከታታይ አራተኛ ወር ቀጥሏል (Human Right Watch)

ተቃዎሞ አድራጊዎች ላይ የሚፈጸመmው ግድያ እና እስር ለተከታታይ አራተኛ ወር ቀጥሏል (Human Right Watch)

February 22, s


FEBRUARY 21, 2016

Saturday, February 20, 2016

ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ

 

በአገራችን ኢትዮጵያአ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነዉ በርካታ የተመሰቃቀሉ ነገሮች አሉ።ፓለቲካዉ ተመሰቃቅሏል፡ ኤኮኖሚዉ ተመሰቃቅሏል ፡ ፀጥታና ደህንነታችንም እንዲሁ።ከፓለቲካዉ ፡ከኢኮኖሚዉና ከፀጥታው ሁኔታዎች መስተካከል ባላነሰ ደረጃ የአገራችንን የዳኝነት ገለልተኝነትና  ነፃነት ማረጋገጥ ዐንዱ ዓቢይ ጉዳይ ሊላ ሲበደል እያዩ እኔን ካልነካኝ የራሱ ጉዳይ ምናገባኝ ማለትን መተዉ ይኖርብናል ።ምክንያቱም ያንድ ዜጋ መብት ዛሬ ሲገፈፍ ከእያንዳንዳችን መብትና ክብር ትንሽ እየተቆረሰ እየተጣለ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ።የኦሮሚያ ወጣቶች የስርአቱን ታጣቂ ሃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስአበባ መንገድ ተዘግቶአል ነገሌ_አርሲ‬ ባሌ ጎባ ። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦርሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሃረርጌ ፀጥታ የለም  ይህ ተሰምቶን በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰዉን በደል ለማስቆም በጋራ መቆምን መልመድ ይገባናል።በሌሎች ላይ የሚደርሰዉን የመብት ጥሰት እኛንም ሳይቆነጥጠን ዝም ካልን የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከእያንዳንዳችን ቤት ዘንድ መምጣቱ አይቀርም።  ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። በሶማሌው በኦሮምያ በጋምቤላ በአማራው በደቡቡ በፈረቃ ግፍ ተፈጸመ እየተፈጸመም ይገኛል ገዳዮችን ፈርቶ ትብብርን ፈርቶ መሞት እንጂ መዳንም ነፃነትን ማስከበርም ባለ አገር መሆንም አይቻልም በተናጠል ጎጠኞች ፈጁን ኧረ ጎበዝ ንቃ!!!                                                                                                                                   ምንጭ፣ ፍቅርተ ነጋሳ 

Friday, February 19, 2016

እኔንም ታዘብኩት (ሀገሬ)

እኔንም ታዘብኩት (ሀገሬ)

ሀገሬ
ሰሞኑን በኃይሌ ገብረሥላሴ ላይ በስጨትጨት ብለው ከተናገሩት መሀል አንዱ ነኝ። በ”ይቻላል” አባባሉና ተግባሩ የምናውቀውና ጥሩ አርአያ ይሆናል የምንለው ጀግናችን አፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲን መመኘትን በ”ትለበሰው የላት ትከናነበው አማራት” ፈሊጥ አይነት ማስቀመጡ በእርግጥም አስከፍቶኛል። የሕዝባችን ሰብአዊ ክብርና የዜግነት መብት መጠበቅ በይደር የሚተው አይደለም። ከዘላለም ባርነት ያንድ ቀን ነጻነት ይባል የል! እንዴት ነው 25 አመት ሙሉ ከአንድ መንደር በመጡ ወያኔዎች መረገጥን ቻሉት የሚባለው? ኃይሌ የሚሳተፍባቸውን ውድድሮች በአሸናፊነት መወጣቱን እንደራሳችን ድል በመቁጠር ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ እንጨነቅ የነበርን፣ ሲያሸንፍ የምንቦርቅ፣ ሲሸነፍ ወይንም ውድድር ማቋረጥ ሲገደድ ከልብ የምናዝን በርካታ ነበርን። ተፎካካሪው ቀነኒሳም እንኳን ቀድሞ መግባት አላስችል ብሎት ወደኋላ መለስ እያለ በማየት ሲጠብቀው አልነበር? ታዲያ በዚህ ደረጃ የኛ ነው ያልነው አትሌት ዛሬ ስንት መስዋእትነት የሚከፈልበትን የዲሞክራሲ ህልም “ቅንጦት” እያለ ሲያጣጥል እንዴት አልዘን?
ኃይሌ ፖለቲካ ውስጥ መግባት መከጀሉን ሲጠቁመንም አመታት ቆጥረናል። ለቢቢሲው ጋዜጠኛ ሲመልስልትም “አሁን ተዉኝ ንግዱንም፣ እርሻውንም፣ ሆቴሉንም፣ ወርቅ ማእድኑንም ላትርፍባቸውና ከዛ በኋላ ፊቴን ወደ ፖለቲካ እመልሳለሁ” ያለ መሰለኝ። የዚህ ስሌት መሰረቱ አሁን ብፈልግም እነአቦይ ስብሀት አይሰጡኝም የሚል ፍርሀት ይሁን ወይንም አሁን በሀብት ማካበቱ ላይ ልትጋና ፖለቲካው ላይ ወደኋላ እደርስበታለሁ ማለቱ እርግጠኛ አይደለሁም። ፖለቲካውን የሚፈልገው ሕዝብን ለማገልገል ከሆነ የሀገራችን ሰው “እኔ የምሞተው ዛሬ ማታ እህል የሚደርሰው ለፍልሰታ” የሚለውን አይዘንጋ። አንዱ የፈረንጆቹ የምጣኔሀብት ባለሙያም “በረጅም ጊዜ ውስጥ ሁላችንም እንሞታለን” (In the long-run we are all dead) ብሏል አሉ። ሁለቱም አባባሎች ዛሬ መወሰድ ያለበትን እርመጃ ለነገ ተነጎዲያ እየተባለ ማጓተት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል የሚያሳስቡ ናቸው። ይህን ስል በጭራሽ ኃይሌ ዛሬውኑ ፖለቲካ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ይኑረው ለማለት አይደለም። ያውሳኔ የኃይሌና የቤተሰቦቹ ብቻ ነው። ደግሞም ፍላጎቱ በስልጣን ማገልገል ሳይሆን መገልገልና ዝና ማትረፍ ከሆነ አለምግባቱ ይመረጣል። ግን ዛሬ ዳቦን ብቻ እናስብ ዲሞክራሲ ቅንጦት ነውና እሱ ሆድ ከሞላ በኋላ ይደረስበታል አይነት አባባሉን አይድገመው ነው ምኞቴ። ምክንያቱም ይህ ሀሳብ እራስን ከትግል ከማሸሽ ባሻገር ሌላውንም ትጥቅ አስፈቺ ነው።
አሁንም ኃይሌን እየወቀስክ ይመስላል። ታዲያ እራስህን የምትታዘብበት ምክንያት ምንድን ነው ትሉኝ ይሆናል። እራሴን የታዘብኩት በሁለት ነገር ነው። መጀመሪያ ትኩረቴ “ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው” የሚለው አባባሉ ላይ ሆነና የተናገረውን ጥሩ ጥሩ ነገር ዘለልኩት። ለምሳሌ “መልካም አስተዳደር ቢኖረን አፍሪካ የት በደረሰች” ሲል የክፍለአለማችንና የሀገራችን የእድገት ማንቆ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው ማለት ነው። በተጨማሪም “አንድ ሰው ወይንም አንድ ወገን ህልጊዜ እኔ ብቻ መሪ ልሁን ማለቱ ትክክል አይደለም” ብሏል። የዚህም ፍሬ ሀሳብ ዘላለም እንምራ ከሚሉት ወያኔዎች ባሻገር የላቅ ብቃት ያለቸው መሪዎች አሉንና እነሱም እድል ይሰጣቸው ከማለት የተለየ አይደለም። ሀገርን ከእናት ጋር በማነጻጸር “እናትህ መጥፎ ባህሪይ ስላሳየችህ እናትነቷን አትክድም” ያለውም ልብ የሚነካ አባባል ነው። ይህም በግልጽ የሚጠቁመው ሀገራችን አሁን ባለችበት ሁኔታ ብዙ ችግር ያለባት ቢሆንም ከነቢሮክራሲው የመልካም አስተዳደር እጦት ሀገሬ እናቴ ናት ማለቱን ነው። ይህም የነቢዩ መኮንንን  “ሀገርህ ናት በቃ” ጽሁፍ አስታወሰኝ። https://www.youtube.com/watch?v=D0G5qs7wPvk
እናም ጨካኝ ወያኔዎች በሞሉበት ምድር ሀብቱን ለመዝረፍ ያሰፈሰፉ ጆፌ አሞራዎች በሞሉበት ምድር ላይ ሁኖ ኃይሌ ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው ስላለ ቅሬታዬን ያለማመንታት የገለጽኩት ሰው እንዴት ነው ለሃያአምስት አመታት ህዝባቸን አሳሩን ሲበላ ትንፍሽ የማይሉትን ከወያኔ በጣም ርቀው አሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ “ምሁራንን” ምነው ዝምታችሁ ምነው ወያኔን መደገፋችሁ ብዬ አለመጠየቄ ነው ሌላው እራሴን ታዘብኩት ያሰኘኝ።
እነኃይሌ ሲያሸንፉ እንደምንደሰተው ኢትዮጵያዊ ምሁር በሙያው እውቅናና ሽልማት ሲያገኝ እንፈነድቃለን። ዶክተር እከሌና ዶክተር እከሊት ታላቅ ሳይንቲስት ተባሉ፣ እነእከሌ ለአለም አቀፍ ድርጅት በመሪነት ተሾሙ፣ እከሊት ታላቅ ሰአሊ ተባለች፣ እከሌ ታላቅ ሼፍ ተባለ፣ እከሊት ታላቅ ሞዴል ተባለች እረ ስንቱ አንቱ በተባለ ቁጥር ፈንጥዘናል። ይሀው ዛሬም መሰረት ደፋርና ገንዘቤ ዲባባ የሩጫ ባለድል ሆኑ መባሉንና የካናዳው አቤል ተስፋዬ ግራሚ ሽልማት አገኘ የሚለውን ዜና በየአምዱ እያነበብን እየተደስትን ነው። የወገን ድል የኛም ድል ነው በሚል ስሜት።
ሕዝባችን ለነጻነትና እኩልነት የሚያደርገውን ትግል በተመለከት ደካማ አስተያየት የምንሰማው አንዱ ጸሀፊ እንዳለው “ታዋቂነት አዋቂነት ከሚመስላቸው” ብቻ አይደለም። በሙያቸው አንቱ የተባሉ በኢትዮጵያ የከበሩና የተከበሩ የቢሮዋቸው ግድግዳና መደርደሪያ በዲግሪና በተለያዩ ሽልማቶች የተጨናነቀባቸው “አዋቂዎች” ናቸው ዛሬ የወገንን መከራና ሰቆቃ “በፖለቲካና ኮረንቲ በሩቅ” አይነት ተልካሻ ምክንያት በዝምታ የሚያልፉት። በቅርብ አንዱ አርቲስትም ቃለ ምልልስ ላይ “ፖለቲካንና ሙያን ማደባለቅ ፍጹም ስህተት ነው” ሲል ሰምቼው ነበር። ሙያ የሚተገበረው ህብረተሰቡ ውስጥ ነው። ህብረተሰብ ላይ በጎና ክፉ ተፅእኖ የሚያደርገውን በሙሉ አይመለከተኝም እያሉ ሸቃጭ እንጂ እንዴት ባለሙያ እንደሚኮን አይገባኝም።
ታዲያ እኛ ስኬታችሁ ስኬታችን ነው የምንላቸው በተለይም ደሀው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍሎ አስተምሮ ለከፍተኛ ማእረግ ካበቃቸው ምሁራን መሀከል በጣት የሚቆጠሩት ብቻ የህዝቤ ህመም የኔም ህመም ነው ማለታቸው ለምንድን ነው? እነሱ ሲሳካላቸው እኛ በደስታ እንዘፍንላቸዋለን፣ አክብረን መቀመጫችንንም እንለቅላቸዋለን፣ ወደድ ያለ ውስኪም ይዘን “እንኳን ደስ አለን!” ለማለት ከቤታቸው ጎራ እንላለን። እኛ ስናለቅስ እነሱ የታሉ ነው የኔ ጥያቄ። ክፍል ውስጥ ስለነጻነት አስፈላጊነት ስለህግ የበላይነት ስለመልካም አስተዳደር ግድ ማለት ፈላስፋ እያጣቀሱ በስሜት ያስተምራሉ። ነገርግን ህዝባቸው ከግፍ ሰንሰለት እንዲፈታ ቅንጣት ታክል አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ አይታዩም። ሌላው ለመብቱ ለነጻነቱ መታገል መብቱ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ግዴታውም ጭምር እንደሆነ ክፍል ውስጥ ይሰበካል ወደራስ ዘንድ ሲመጣ ግን “ጎመን በጤና” ይመረጣል። አጋዚን የሀገራችን ሕዝብ “የቤት አንበሳ የውጪ እሬሳ” እንደሚለው መሆኑ ነው።
እነኚህ ምሁሮችም ወይ ሀገርቤት ለመጦሪያ የቀለሷት ቤት እንዳትወሰድባቸውና ኢትዮጵያ ተዝናንተው መምጣት ወያኔ እንዳያግዳቸው በመፍራት ዝምታን መርጠዋል። ከዚህ የከፉም አሉ። በርካታ አመታት ትምህርትቤት አሳልፈው የዕውቀት ጠርዝ ላይ ደርሰናል የሚሉ ግን “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል” አለች ከምትባለው እንስሳ ባነሰ አስተሳሰብ ወገናቸውን ለሚያሰቃየው ወያኔ ገንዘብ ለማሰባሰብ ቶምቦላ የሚያሻሽጡ ማፈሪያ ዶክተሮች አሉን አሉ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ፡፡ ወያኔም እንዲህ በኮንዶሚኒየምና መዋእለንዋይ እንቁልጭለጭ “ማኖ” እያስነካ ትልልቁን ዳቦ ሊጥ ያደርገዋል።
ዶክተር ብርሀኑ በቅርብ አሜሪካ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያውያን ልሂቆች ከተደበቁበት ወጥተው የሀገሬና የህዝቤ ጉዳይ ያገባኛል ብለው መነሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሌላው ሞቶ ነጻ ባወጣት ምድር ላይ ከበርቴ ሁኖና አንቱ ተብሎ መኖርን ማለም ብልህነት ሳይሆን ሌላውን ገድሎ መኖር የሚከጅል ደም መጣጭ መዥገርና ፓራሳይት መሆን ነው። እርግጥ ነው በታሪካችን ለሀገር የቆሰለውና የሞተው ተረስቶ ከሀዲ ባንዳ የተሾመበት ጊዜ ብዙ ነው። ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያችን ውስጥ ለአንድነቷ ሲዋጉ የነበሩት ለማኝ ሁነው ሀገሪቱን ለማፍረስ ያሴሩ ባንዳ የባንዳ ልጆች ተሹመው ይፈነጩባታል። ለዚህም ነው “ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የሚለው አባባል ዛሬም ወቅታዊ የሆነው። ነገርግን ህሊና ላለው ሰው ከሀዲ ባንዳ ተብሎ ሆድን ከመሙላት ሀቀኛ ጀግና ተብሎ በገንዘብ ችግር መኖር ይመረጣል። ለዚህም ኩሩው የሚሊሺያ አሊ በርኬ ታሪክ ታላቅ ምስክር ነው። ለጊዜያዊ ጥቅም ሲል ክብሩንና ሀገሩን ያዋረድ ሆዳም መባልን እንፍራ እንጥላ።
(It takes to Tango) ታንጎ ለመደነስ ሁለት ሰው ያስፈልጋል እንደሚባለው ምሁሮቻችንን የኛ እንድንላቸው እንሱም እኛን የኛ ይበሉን። እንድናከብራቸው እንድንወዳቸው እንድናወድሳቸው የኛን ችግር እንደ ባዕድ ከርቀት ሁነው ስራችሁ ያውጣችሁ ማለቱን ትተው መፍትሄ ፍለጋው ላይ አብረው ይስሩ።

Friday, February 12, 2016

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተከላከሉ ተባ ተከሳሾች 200 የሰው መከላከያ ምስክሮች አሉን ብለዋል


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን አቋርጠው ኤርትራ የሚገኘውን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ከአዲስ አበባ ተነስተው ሲጓዙ ማይካድራ የሚባል የድንበር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሶ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል፡፡
ዛሬ የካቲት 4/2008 ዓ.ም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾቹ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ወ/ሪት እየሩሳሌም ተስፋው፣ አቶ ፍቅረማርያም አስማማው እና አቶ ደሴ ካህሳይ አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በሰነድና በአንድ የሰው ምስክር ማስረጃዎች አስረድቷል በሚል ተከሳሾች መከላከል ይገባቸዋል ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
ተከሳሾች 14ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀየርላቸው አቤቱታ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ ይህ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ችሎቱ ብይኑን እንዳያሰማ ቢጠይቁም፣ ችሎቱ ‹‹አቤቱታው ቶሎ ብይን እንዲሰጣችሁ የሚጠይቅ ነው፣ በመሆኑም ብይኑ ተሰርቷል›› ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ተከሳሾች ብይኑ አይሰማብን የሚለውን ጥያቄ ባለመቀበል ችሎቱ ብይኑን በንባብ አሰምቷል፡፡
እነ ብርሃኑ ተከላከሉ መባላቸውን ተከትሎ መከላከያ ማስረጃዎች ያቀርቡ ከሆነ በሚል ፍርድ ቤቱ ጠይቆ፣ ተከሳሾች 200 የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች በጋራ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም መከላከያ ማስረጃዎችን ለማድመጥ ለመጋቢት 21/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች እያዘጋጁት የነበሩት የተከሳሽነት ቃል ጽሁፍ በማረሚያ ቤት ፖሊሶች እንደተወሰደባቸው ለፍርድ ቤቱ በመግለጽ ከዚህም በኋላ ተመሳሳይ ለችሎት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ማዘጋጀት እንዲችሉ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ችሎት የቀረቡት እነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ 14ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀየርላቸው አቤቱታቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ብይን ለማሰማት ለየካቲት 10/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
source በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር  

Tuesday, February 9, 2016

ሁለተኛው ምዕራፍ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ ማጎሪያ)

 እጅግ ኋላቀር ከሆኑ ትናንሽ የገጠር ወረዳዎች አንስቶ እስከ ታላላቅ ከተሞች ድረስ በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የመጀመሪያውን ምዕራፍ ከሞላ-ጎደል በአሸናፊነት ተወጥቷል፡፡ በድሉ በመጠኑም የምንኩራራው (አንገታችንን ቀና የምናደርገው) የወደቁ ሠማዕታት የከፈሉትን ዋጋ ሳንዘነጋ ነው፡፡ በዚህ አውድ ፖለቲካዊ ድል ብዬ የምዘክረው የ “ማስተር-ፕላኑ” ዕቅድ መሠረዙን ብቻ አይደለም፡፡ በውሳኔው ስር የሰደደው የወያኔ ግትር ባሕሪም (የአስተዳደር ዘይቤ) ለቡርቦራ መጋለጡን ጭምር በመገምገም ነው፡፡ ክስተቱም የ1966ቱን አብዮት ዋዜማ ያስታውሰኛል፡፡ በወቅቱ የአፄው መንግሥት የተቃውሞ ንቅናቄ በፈጠረበት ጫና አጣብቂኝ ውስጥ በመቀርቀሩ “ሴክተር ሪቪው” የተሰኘ አዲስ የትምህርት ፖሊሲውን ሲሰርዝ፤ በነዳጅ ዋጋ ላይ ሊጨምር ያሰበውንም ታሪፍ ለመተው ተገዷል፡፡ በዚህም የተበረታታው የለውጥ ኃይል ዘውዳዊውን ሥርዓት ለመገርሰስ ከወራት የበለጠ ጊዜ አላስፈለገውም ነበር፡፡ በኦሮሚያ ጎበዛዝት ክፉኛ የተፈተነው ወያኔም የቆመበት ጠርዝ በግርድፉ ሲታይ ከ66ቱ ዋዜማ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ይህ ግን እንደ አዛውንቱ ንጉሥ የመጨረሻ ቀናት ጡንቻው ሙሉ በሙሉ ዝሏል ማለት አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላ ማዛሉ፣ አልፎም ተርፎ የመቃብሩን ካንቻ ማጥበቁ የመጀመሪያውን ምዕራፍ ያህል አስቸጋሪ (ከባድ) አለመሆኑን መጠቆም እንጂ፡፡ የሁለተኛው መርሃ-ግብር ሕዝባዊ እምቢተኝነት “ማስተር ፕላኑ” መሠረዙን አመስግኖ ሲያበቃ (በብሉይ አብዮቱ ዋዜማም የንጉሡ አስተዳደር ያፀደቃቸውን ፖሊሲዎች ለመሻር የተገደደበትን ኩነት ተከትሎ “እግዜር ይስጥልኝ” በሚል ርዕስ ከግራ-ዘመም ቡድኖች የአንዱ አመራር አባል መጣጥፍ አዘጋጅቶ እንደነበረ ዛሬ ማስታወስ ባልቻልኩት ድርሳን ላይ ማንበቤን አልዘነጋውም፡፡) በዋናነት መነሳት ያለበት አጀንዳ ምንድን ነው? የሚለውን በአዲስ መስመር ጨርፈን እናያለን፡፡ ቀዳሚው እንዲህ ዓይነቱን የክልሉን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ህልውና ተፈታታኝ ዕቅድ ያለአንዳች ሕዝባዊ ውይይት ማብራሪያና ለመተግበር የሞከሩ፤ ሙከራውንም በዝምታ ያዩ ባለሥልጣናት ከሥልጣናቸው እንዲሻሩ ማድረጉ ላይ ቢያተኩር ቅቡል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህም ርዕሰ-መስተዳድሩ ሙክታር ከድር፣ ረዳቶቹና አማካሪዎቹ በቸልተኝነት የሚከሰሱ ሲሆን፤ ተከታዩ የፕላኑ ነዳፊዎችን ይመለከታል፡፡ በጋራ ደግሞ ሹማምንቱ ለጠፋው ሕይወት፣ ለደረሰው አካል ጉዳት፣ ለወደመው ንብረት…… ኃላፊነቱን ወስደው በወንጀል እንዲጠየቁ መቀስቀሱ እና ማሳመፁ የሁለተኛው ምዕራፍ ትግል ባንዲራ መሆን ይችላል፡፡ ይህንን ለማደላደልም ልሂቃን እና አክቲቪስቶች ከወዲሁ የመጀመሪያውን ተሞክሮ ገምግመው ጠንካራ ጎኑን በማዳበር፣ ድክመቱን አርመው መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አጀንዳው የታሰሩ የንቅናቄው ተሳታፊዎች ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ጭካኔ የተጠናወተውን ጅምላ ጭፍጨፋ ያዘዙ ባለሥልጣናትም ሆኑ የተገበሩት በሙሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ እንዲሁም መንግሥት ለሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፍል ማስገደድን ጭምር ማካተቱን ሁሉም በግልፅ በሚገባው መንገድ ማብራራቱና ማስረፁ አስፈላጊ ነው፡፡ በጥቅሉ ሊመለሱ የማይችሉ ጉዳዮችን እያነሱ የመታገያ ጥያቄዎች ማድረጉ ከሰላማዊ ትግል ስልቶች መካከል የሚመደብ መሆኑም መዘንጋት የለበትም፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም የተገኘውን ፖለቲካዊ ድል በተለይ ለተርታው አማፅያን አጉልቶና አፍታቶ ማስረዳቱ የመሪዎቹ ግዴታ ነው፡፡ ብዙሃኑ የዕቅዱ መሠረዝ የአገዛዙ ችሮታ ወይም በራሱ አገላለፅ ‹‹የሕዝብን ፍላጎት ማክበር›› ሊመስለው ይችላልና (ወሳኔውንም በዚህ መልኩ ወደ መሬት ለማውረድ የሥርዓቱ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ምን ያህል እንደለፉ ልብ ይሏል፡፡) ሌላው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች አስተዋፅኦ ወሳኝነትን ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ የዚህ ትኩስ ኃይል አበርክቶ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም የላቀ ነው፡፡ ምክንያቱም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቋንቋ ተናጋሪነታቸው በብሔር የተከፋፈሉ ከመሆናቸውም በዘለለ፣ አብዛኞቹ በዕጣ-ምደባ መሠረት ከትውልድና ከመኖሪያ መንደራቸው ርቀው በመምጣታቸው ምክንያት በሚማሩበት ከተማ ካለው ሕብረተሰብ ጋር ግንኙነታቸው የጠበቀ አይደለም፡፡ ስለዚህም ተቃውሞውን ከትምህርት ቤታቸው ቅፅር ግቢ ውጪ የማሻገር ዕድላቸው የመነመነ ነው፡፡ በግልባጩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እዛው በቀዬአቸውና በማሕበረሰባቸው ውስጥ ሆነው ስለሚማሩ ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመድ ጓደኞቻቸውን….. በአጠቃላይ አካባቢያቸውን በቀላሉ ከጎናቸው ማሠለፍ አያዳግታቸውም፡፡ ይህ ደግሞ የአመፁን አድማስ በሚፈለገው መጠን ያስፋፋዋል፡፡ እናም መላው አብዮታውያን፣ ተማሪዎቹ ከወዲሁ አስተባባሪዎቻቸውን መርጠው በሕቡዕ እንዲደራጁ ማብቃቱ ለነገ የሚሉት የቤት ሥራ አይደለም፡፡ (በያ ትውልድ ትግልም ከ1964ዓ/ም ጀምሮ ሕዝባዊ ቁጣ የተጋጋመውም ሆነ በከፊል የተመራው በየትምህርት ቤቱ በተመሠረቱ “የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሸንጎ” (High school councils) እንደነበር ዘመኑን የሚያወሱ በርካታ ትርክቶች አትተዋል፡፡) በመጨረሻም ኦሮሚኛ ተናጋሪ ያልሆነው ኢትዮጵያዊ ሚናስ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ሊተኮርበት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህን መሠሉን ተቃውሞ ተቆጣጥረው ከመሩት ታሪካዊ ተልዕኮውን ሲጨርስ ወደ አብዮታዊ ትግል ማደጉ ተፈጥሮአዊ (አይቀሬ) በመሆኑ ከፖሊሲ ማሻሻያ ያለፈ ውጤት ሊያስገኝ የሚችልበት አጋጣሚ የበዛ ነው (የኢኮኖሚው ድል በተስፋና በአመፅ ትዕምርትነትም (symbolic) ጭምር ማገልገሉ ሳይረሳ ማለት ነው፡፡) በአናቱም ንቅናቄው በኢትዮጵያችን ሰማይ ሥር (ያውም ሁሉን ረግጦ በሚገዛ ቡድን ላይ) እስከሆነ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ቢገደብ እንኳ መንፈሱና ውጤቱ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የማይዳስሰው የሕብረተሰብ ክፍል የለም፡፡ ስለዚህም የየብሔሩ ቅቡል ልሂቃን ባሻቸው ሥፍራ (“ሰባተኛው ሠማይ” ላይም ቢሆን) ተሰባስበው ቢያንስ በስልት ደረጃ የሚደጋገፍ የጋራ ግንባር (ኮሚቴ) በመፍጠር ተቃውሞውን በየክልላቸው ማዛመቱ ታሪክ የጣለባቸው ኃላፊነት ይመስለኛል፡፡ የሰሜን ጎንደሩን ስምየለሽ ክስተት እና የድንበር ጉዳይ አማርኛ ተናጋሪውን የማስተባበሪያ አጀንዳ በማድረግ መጠቀምንም እመክራለሁ (በእንዲህ ዓይነቱ በግላጭ በሚሰራጭ መጣጥፍ ዝርዝር ነገሮችን ማንሳት አገዛዙን ማንቃት ነውና ሃሳቤን እዚሁ ጋር እገታለሁ፡፡) ከዚህ ባለፈ ሁለተኛው ምዕራፍ እንዲያጠነጥንባቸው ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ይዘት ብቻ በመመዘን ጉዳዩ የኦሮሞ የግሉ ነው ብዬ ራስን በዝምታ መግራት (በተመልካችነት ማስቀመጥ) የማይታረም ስህተት ከማስከተሉም ሌላ ወርቃማውን ዕድል ሊያመክነው ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በጠቅላይነት ሳር-ቅጠሉን በመጠርነፍ የተካነው ኢህአዴግ ተጠናክሮ የሚወጣበትን ጉልበት በቀላሉ እንዲጎናፀፍ ያደርገዋል፡፡ ድል ለሠፊው ሕዝብ! ኢትዮሚድያ -                                                        Source     Ethiomedia.com February 9, 2016

Saturday, February 6, 2016

Ethiopia: 120 Years After The Battle Of Adwa A Documentary Remembers The History Of Italy In Ethiopia



This month will mark the 120th anniversary of The Battle of Adwa.The 120th anniversary of the Battle of Adwa
Ethiopia is widely known as the only country in Africa, besides maybe Liberia, not to be colonized by a European power. During the twentieth century, many African nations adopted Ethiopia’s flag colors of green, yellow, and red to proclaim to the world, we too are free as our Ethiopian brethren.
Ethiopia did not escape European colonization for a lack of attempts. To the contrary, Italy attempted an invasion twice. The Italians brought with them mustard gas, roads, guns, infrastructure, and atrocities. Under the leadership of Pope Pius XI, Vatican officials and clergy blessed the bombs that massacred scores of Ethiopian civilians. Here’s a clip of a priest doing just that. “Sanctus Sanctus Sanctus” (holy, holy, holy) he says as he holds the bomb.
The first Italo-Ethiopian War began during the Scramble for Africa with Italian forces encroaching into sovereign Ethiopian territory leading to skirmishes and battles that culminated in late February 1896 at The Battle of Adwa. The poorly equipped Ethiopians, led by Emperor Menelik II, decisively beat back the military might of Italy.
This legacy of defeat haunted Italy’s fascist leader Benito Mussolini’s sense of nationalistic jingoism and in 1935 he began an offensive to seize Italy’s “rightful place under the sun.” What he didn’t consider was Ethiopia’s long rainy season.
What is not widely known is the history of struggle that engulfed Ethiopia, the short but lasting impact of the Italian occupation from 1935-1941 and Ethiopia’s triumphant return to independence.
If Only I Were That Warrior, winner of the Premio ‘Imperdibili’ at the 2015 Festival dei Popoli, is a thoughtful documentary that grapples with these highly contested subjects, including Rodolfo Graziani, the fascist Italian general behind the death of tens of thousands of Ethiopians in the 1930s.
Known as “The Butcher” for his sustained brutality, Graziani famously spoke the words, “The Duce (Mussolini) will have Ethiopia, with or without the Ethiopians.” And he delivered on that proclamation by indiscriminately killing civilians, deploying chemical agents and leading a campaign of mass death in Ethiopia. Graziani never faced international law tribunals for his role in the occupation.
In 2012, the small conservative town of Affile, Italy, where Graziani was from, erected a monument to the fascist war criminal, sparking international protests. The documentary follows this long and complicated history, detailing the protests around the monument with interviews with Ethiopians and Italians in their home countries and in the diaspora. With rare archival footage from the Graziani Archive, the documentary offers a fascinating glimpse into the conflict.
If Only I Were That Warrior marks the feature-length documentary debut of Brooklyn-based filmmaker Valerio Ciriaci. Filmed in Ethiopia, Italy, and the United States, the project follows the stories of three people as they discuss the vestiges of the Italian occupation, a story that traverses generations and cultures.
Check out the trailer below and catch the documentary screening this month in the following locations across the U.S. and Italy.
If Only I Were That Warrior February 2016 Screenings
Feb. 5 2016 / Tivoli, Italy
Scuderie Estensi – 5pm
Sponsored by Comitato Affile Antifascista, Associazioni Etiopi in Italia, ANPI.
Feb. 11 2016 / New York
Casa Italiana Zerilli-Marimò, New York University – 6pm
Sponsored by Centro Primo Levi NY and Department of Italian Studies NYU. Q+A with director Valerio Ciriaci and producer Isaak Liptzin.
Feb. 20 2016 / Minneapolis / Italian Film Festival
St. Anthony Main Theater – 5pm
Sponsored by The Italian Cultural Center of Minneapolis and St. Paul
Feb. 20 2016 / Philadelphia / Africa World Documentary Film Festival
Molefi Kete Asante Institute – 5pm
Q+A with director Valerio Ciriaci and producer Isaak Liptzin.
Feb. 21 2016 / Washington DC
TBD – 2pm
Sponsored by The Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause. Q+A with director Valerio Ciriaci and producer Isaak Liptzin.
Feb. 24 2016 / Cuneo, Italy
Cinema Monviso – 9pm
Sponsored by Pro Natura Cuneo.
Feb. 27 2016 / Missoula / Big Sky Documentary Film Festival
Crystal Theater – 10pm
Q+A with director Valerio Ciriaci and producer Isaak Liptzi                                                      source   http://ecadforum.com/

Friday, February 5, 2016

ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጳ ሊሆን አይችልም አንድነት ሀይል ነው።


        ህብረት አንድነት የሰውልጆች  የሚያስቡትንና   የሚያልሙት ሊተግብሩት ያቀዱትን ራዕይ ወደተግባር የሚለውጡበት
እና የሚያሳኩበት ትልቅ ሀይለ ቃል ነው በቡዙ ፖለቲከኞች ፀሀፍቶች ሀያሲዎች የፖለቲካ ተንታኞች ሰፋባለ መልኩ ሙሁራዊ
አገላለፅ ሲፅፉ እናነባለን ሲናገሩ እንሰማለን በተለይም ደግሞ በአገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች በአንድ ላይ ሊሰሩ ተስማሙ
ወይም ደግሞ በአንድ ላይ ሊሰሩ የጋራ ዕቅድ አወጡ የሚሉ ቃላትን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንሰማለን ለምንድነው በቃላት ደርጃ
የሚነገርውን አንድነት ለምን ወደተግባር ተለውጦ ትርጉም ያለው ለህዝብ የሚጠቅም የተግባር ስራ ተሰርቶ የሚታሰበው
የስርዓት ለውጥ ተለውጦ ማየት ያቃተን፧ ምናልባት በኔ እይታ አንድነት ከአንደበታችን የሚወጣ የቃል አጠራር ትርጉም
እንጂ ከውስጥ ከልባችን የሚወጣ የ አንድነት የፍቅር፣የመተሳሰብ ፣የመደማመጥ የተግባር ሂደት አይደለም ።  
 የተለያዩ ጥያቄዎችን በመደማመጥና በመነጋገር ግልፅ በሆነ መልኩ ባለመነጋገር የሀሳብና ያመለካከት ልዩነቶችን
አለማቻቻል ነው ወይም መልካም የሆነውን የበለጠውን ሀሳብ ተቀብሎ ወደጥፋት የሚወስደውን የጋራ የሆነውን ጎጂውን
ሀሳብ ትቶ መልካም የሆነውን የጋራ እሴት ላይ ትኩረት አለመስጠት ነው።                                                                                                                                     
ለዚህ  ጽሁፍ  መንደርደሪያ  ሀሳብ  የሆነኝ  በአብዛኛው  ኢትዮጵያዊ  እንደሚረዳውና  እንደሚገነዘበው  በተለያዩ  የኦሮሞ  ክልል የህዝባዊ  የተቃውሞ  በተለይም  የአዲስ  አበባን  የማስፋፋት  የማስተር  ፕላን  በሚል  ደሀውን  አርሶ  አደሩን  ነዋሪውን  ከመኖሪያው  ቀዬው  የማፈናቀል  የተንኮል  እስትራተጂ   ነው በዚህም  የተነሳ  መብታቸውን  ለማስከበር  በሰላማዊ  መንገድ ትቀዋሟቸውን  ለማሰማት  የወጡትን  ሴት፣  ህፃን፣  አዛውንት ፣ወጣት  ሰይመርጥ  የህወሓት  ወያኔ  አጋዚን  ወታደር  የበርካታ  ህዝብ  ህይወት  በማጥፋት  በምግደል   በማሰር  በመግረፍ  በማሰቃየት  በገዛ  ህዝብ  ላይ  ሊወሰድ  ቀርቶ  ሊታሰብ  የማይገባውን ጨካኝ  እርምጃ  ወስደዋል  የነፃነት  ቀን  ሲመጣ  እያንዳንዱ  ከተጠያቂነት  እንደማያመልጥ  እሙን ነው።

በሌላ  መልኩ  ደግሞ  በተለይም  በኦሮሞ  ቋንቋ  ተናጋሪዎች  ወይም  ተወላጆች  የሚነሳ  ጥያቄ  አለ  እሱም ትግሉን  ሊሎች  አካሎች ወይም  ማህበረሰቦች  አልተቀላቀሉትም  ወይም  አልተባበሩንም  የሚል  ነገር  በተላያይ  ሆኔታዎች  ሲገለፁ  እናስትውላለን

ጥያቄው  እውነታ  ቢኖረውም  የመፍተሄው  ቁልፍ  በኛው  እጅ  ነው  እሱም  ጥያቄውን  ብሔር  ተኮር  ሳይሆን  ትልቋን  ሀገር ኢትዮጵያን  ለብዝዎች  የጥቁር  ህዝቦች  የነፃነት  ቀንዲል  ምሳሌ  የነፃነት  ዓርማ  ምልክት  የሆነቸውን  ሙስሊም  ክርስታያን  ሁሉም በፍቅር  የሚኖርባት  በመፀህፍ  ቅዱስም  በቅዱስ  ቁራአን  ትልቅ  ሰፍራ  የሚሰጣ ት እረፍትና  ሰላም  የሚገኝባትን  የሰላም  እና እንግዳተቀባይ  የሆነችውን  ሀገር  ስም  ኢትዮጵያን  ሰሟን  እየጠራን  ሁሉንም  ማሳተፍና  ማንቀሳቀስ  ስንጀምር  ነው  በተለይም ከቀድሞ  አመለካከታችን  ሙሉ  በሙሉ  ተቀይረን  ወያኔ  ፪፭ አመት  ሲደክምበት  ሲሰራበት  የነበረውን  ብቱቶ  የሆነውን  የዘር ፖለቲካ  ከውስጣችን  ማስወገድ  አለብን  ያኔ  ለሁላችንም  የምትሆን  ምቹ  ሀገር  ዲሞክራሲያዊ  ስርዓት  መገንባት  እንችላለን  ያኔ ትግሉ  የሁሉም  ኢትዮጵያዊ  ይሆናል  ስለዚህም  ነው  አንድነት  ሀይል  ነው  የምንለው  ከቃል  የዘለለ  የተግባር  የሚሆነው።                                                                                                                                                                  ሌላው  በተለይም  ለአንባገነኖች  መንግስታት  ትልቅ  ትምህርት  ሰጥቶ   ያለፈው  በቱኒዚያ  በአንድ  ሰው   መሰዋትነት    የተቀጣጠለው።  የአርብ  እስፕሪግ  አድማሱን  አስፍቶ  የስሜን  አፍሪካ  ሀገሮችን  ግብፅን  ሙባርክን  ሊቢያ  ጋዳፊን  ለውርደት  ሲዳረጉ በአይናችን አይተናል  ወያኔና  ለህዝብ  ሳይሆን  ለሆዳቹ  ያደራቹ  ማናቹሁም  የስርዓቱ  ዳጋፊዎች  አስተሳሰብ  ቢኖራቹህ   ከነሱ  ብዙ  መማር ትችሉ  ነበር  ግን  የምታስቡት  ለሀገር  ለወገን  ሳይሆን  ለሆዳቹሁ  ነው   ወደ  ግብፅ  ስንመጣ  ህዝቡ  ለለውጥ  ሲነሳ  ምናልባት ምናስታውስ  ከሆን  የወታደራዊ  ሀይሉ  ከህዝቡ  ጋር  ወግኖ  የግዛ  ህዝቤን  አልገልም  ብሎ  ከህዝቡ  ጋር  ነው  የወገነው  ይህነው ለህዝብ  የቆመ  መለዮ  ለባሽ  የሚያስበለው  በተጨማሪም  በተለይ  በተሀሪር  እስኬር  በተደጋጋሚ  በማደር  ነፃነታችንን  ካለገኘን በማለት  በአንድነት  ለአንድ  ዓላማ  በመቆም  የአንባገነን  ስርዓት  ገርስሰው  ያሶገዱት  የወያኔ  መከላከያም ሆነ  የፖሊስ  ሀይል በማንኛዉም  ዘርፍ ያለው  የወታደር  ሀይል።

የህዝብ  ደህንነትም  ነገ የታሪክ  ተወቃሽ  ሰትሆኑ  የህዝብ  አጋርነታችሁን  የምታሳዩበት  ወቅት  አሁን  ነው ።

                                         

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ።