ህብረት አንድነት የሰውልጆች የሚያስቡትንና የሚያልሙት ሊተግብሩት ያቀዱትን ራዕይ ወደተግባር የሚለውጡበት
እና የሚያሳኩበት ትልቅ ሀይለ ቃል ነው በቡዙ ፖለቲከኞች ፀሀፍቶች ሀያሲዎች የፖለቲካ ተንታኞች ሰፋባለ መልኩ ሙሁራዊ
አገላለፅ ሲፅፉ እናነባለን ሲናገሩ እንሰማለን በተለይም ደግሞ በአገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች በአንድ ላይ ሊሰሩ ተስማሙ
ወይም ደግሞ በአንድ ላይ ሊሰሩ የጋራ ዕቅድ አወጡ የሚሉ ቃላትን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንሰማለን ለምንድነው በቃላት ደርጃ
የሚነገርውን አንድነት ለምን ወደተግባር ተለውጦ ትርጉም ያለው ለህዝብ የሚጠቅም የተግባር ስራ ተሰርቶ የሚታሰበው
የስርዓት ለውጥ ተለውጦ ማየት ያቃተን፧ ምናልባት በኔ እይታ አንድነት ከአንደበታችን የሚወጣ የቃል አጠራር ትርጉም
እንጂ ከውስጥ ከልባችን የሚወጣ የ አንድነት የፍቅር፣የመተሳሰብ ፣የመደማመጥ የተግባር ሂደት አይደለም ።
የተለያዩ ጥያቄዎችን በመደማመጥና በመነጋገር ግልፅ በሆነ መልኩ ባለመነጋገር የሀሳብና ያመለካከት ልዩነቶችን
አለማቻቻል ነው ወይም መልካም የሆነውን የበለጠውን ሀሳብ ተቀብሎ ወደጥፋት የሚወስደውን የጋራ የሆነውን ጎጂውን
ሀሳብ ትቶ መልካም የሆነውን የጋራ እሴት ላይ ትኩረት አለመስጠት ነው።
ለዚህ ጽሁፍ መንደርደሪያ ሀሳብ የሆነኝ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳውና እንደሚገነዘበው በተለያዩ የኦሮሞ ክልል የህዝባዊ የተቃውሞ በተለይም የአዲስ አበባን የማስፋፋት የማስተር ፕላን በሚል ደሀውን አርሶ አደሩን ነዋሪውን ከመኖሪያው ቀዬው የማፈናቀል የተንኮል እስትራተጂ ነው በዚህም የተነሳ መብታቸውን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ ትቀዋሟቸውን ለማሰማት የወጡትን ሴት፣ ህፃን፣ አዛውንት ፣ወጣት ሰይመርጥ የህወሓት ወያኔ አጋዚን ወታደር የበርካታ ህዝብ ህይወት በማጥፋት በምግደል በማሰር በመግረፍ በማሰቃየት በገዛ ህዝብ ላይ ሊወሰድ ቀርቶ ሊታሰብ የማይገባውን ጨካኝ እርምጃ ወስደዋል የነፃነት ቀን ሲመጣ እያንዳንዱ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እሙን ነው።
በሌላ መልኩ ደግሞ በተለይም በኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ወይም ተወላጆች የሚነሳ ጥያቄ አለ እሱም ትግሉን ሊሎች አካሎች ወይም ማህበረሰቦች አልተቀላቀሉትም ወይም አልተባበሩንም የሚል ነገር በተላያይ ሆኔታዎች ሲገለፁ እናስትውላለን
ጥያቄው እውነታ ቢኖረውም የመፍተሄው ቁልፍ በኛው እጅ ነው እሱም ጥያቄውን ብሔር ተኮር ሳይሆን ትልቋን ሀገር ኢትዮጵያን ለብዝዎች የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል ምሳሌ የነፃነት ዓርማ ምልክት የሆነቸውን ሙስሊም ክርስታያን ሁሉም በፍቅር የሚኖርባት በመፀህፍ ቅዱስም በቅዱስ ቁራአን ትልቅ ሰፍራ የሚሰጣ ት እረፍትና ሰላም የሚገኝባትን የሰላም እና እንግዳተቀባይ የሆነችውን ሀገር ስም ኢትዮጵያን ሰሟን እየጠራን ሁሉንም ማሳተፍና ማንቀሳቀስ ስንጀምር ነው በተለይም ከቀድሞ አመለካከታችን ሙሉ በሙሉ ተቀይረን ወያኔ ፪፭ አመት ሲደክምበት ሲሰራበት የነበረውን ብቱቶ የሆነውን የዘር ፖለቲካ ከውስጣችን ማስወገድ አለብን ያኔ ለሁላችንም የምትሆን ምቹ ሀገር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንችላለን ያኔ ትግሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ይሆናል ስለዚህም ነው አንድነት ሀይል ነው የምንለው ከቃል የዘለለ የተግባር የሚሆነው። ሌላው በተለይም ለአንባገነኖች መንግስታት ትልቅ ትምህርት ሰጥቶ ያለፈው በቱኒዚያ በአንድ ሰው መሰዋትነት የተቀጣጠለው። የአርብ እስፕሪግ አድማሱን አስፍቶ የስሜን አፍሪካ ሀገሮችን ግብፅን ሙባርክን ሊቢያ ጋዳፊን ለውርደት ሲዳረጉ በአይናችን አይተናል ወያኔና ለህዝብ ሳይሆን ለሆዳቹ ያደራቹ ማናቹሁም የስርዓቱ ዳጋፊዎች አስተሳሰብ ቢኖራቹህ ከነሱ ብዙ መማር ትችሉ ነበር ግን የምታስቡት ለሀገር ለወገን ሳይሆን ለሆዳቹሁ ነው ወደ ግብፅ ስንመጣ ህዝቡ ለለውጥ ሲነሳ ምናልባት ምናስታውስ ከሆን የወታደራዊ ሀይሉ ከህዝቡ ጋር ወግኖ የግዛ ህዝቤን አልገልም ብሎ ከህዝቡ ጋር ነው የወገነው ይህነው ለህዝብ የቆመ መለዮ ለባሽ የሚያስበለው በተጨማሪም በተለይ በተሀሪር እስኬር በተደጋጋሚ በማደር ነፃነታችንን ካለገኘን በማለት በአንድነት ለአንድ ዓላማ በመቆም የአንባገነን ስርዓት ገርስሰው ያሶገዱት የወያኔ መከላከያም ሆነ የፖሊስ ሀይል በማንኛዉም ዘርፍ ያለው የወታደር ሀይል።
የህዝብ ደህንነትም ነገ የታሪክ ተወቃሽ ሰትሆኑ የህዝብ አጋርነታችሁን የምታሳዩበት ወቅት አሁን ነው ።
ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ።
No comments:
Post a Comment