ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ
በአገራችን ኢትዮጵያአ ወጣቶች በአንድ ልብ የተሳተፉበት ያልተሳካ የአብዮት ታሪክ አናውቅም። የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነዉ በርካታ የተመሰቃቀሉ ነገሮች አሉ።ፓለቲካዉ ተመሰቃቅሏል፡ ኤኮኖሚዉ ተመሰቃቅሏል ፡ ፀጥታና ደህንነታችንም እንዲሁ።ከፓለቲካዉ ፡ከኢኮኖሚዉና ከፀጥታው ሁኔታዎች መስተካከል ባላነሰ ደረጃ የአገራችንን የዳኝነት ገለልተኝነትና ነፃነት ማረጋገጥ ዐንዱ ዓቢይ ጉዳይ ሊላ ሲበደል እያዩ እኔን ካልነካኝ የራሱ ጉዳይ ምናገባኝ ማለትን መተዉ ይኖርብናል ።ምክንያቱም ያንድ ዜጋ መብት ዛሬ ሲገፈፍ ከእያንዳንዳችን መብትና ክብር ትንሽ እየተቆረሰ እየተጣለ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ።የኦሮሚያ ወጣቶች የስርአቱን ታጣቂ ሃይል በጦርና በጠመንጃ ይፋለሙት ይዘዋል። ከሻሸመኔ ወደ አዲስአበባ መንገድ ተዘግቶአል ነገሌ_አርሲ ባሌ ጎባ ። ልማደኛዋ ኮፈሌ ጦርሜዳ ሆናለች። ብረት ለበስ ጦር ኮፈሌና ሻሸመኔ ገብቷል። በጥቅሉ ወለጋና ሃረርጌ ፀጥታ የለም ይህ ተሰምቶን በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰዉን በደል ለማስቆም በጋራ መቆምን መልመድ ይገባናል።በሌሎች ላይ የሚደርሰዉን የመብት ጥሰት እኛንም ሳይቆነጥጠን ዝም ካልን የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ከእያንዳንዳችን ቤት ዘንድ መምጣቱ አይቀርም። ዝምታው ማብቃቱ ግልፅ ነበር። በሶማሌው በኦሮምያ በጋምቤላ በአማራው በደቡቡ በፈረቃ ግፍ ተፈጸመ እየተፈጸመም ይገኛል ገዳዮችን ፈርቶ ትብብርን ፈርቶ መሞት እንጂ መዳንም ነፃነትን ማስከበርም ባለ አገር መሆንም አይቻልም በተናጠል ጎጠኞች ፈጁን ኧረ ጎበዝ ንቃ!!! ምንጭ፣ ፍቅርተ ነጋሳ
No comments:
Post a Comment