ፈረንጅ የሚያደርገው ሁሉም ነገር ትክክል ነው ለማለት ሳይሆን ፈረንጅ ቀዳሚና አንገብጋቢ የሆነውን ጉዳይ ማስቀደም ያዘወትራል ለማለት ነው፡፡
ንዴት በማንም ላይ ይደርሳል፡፡ በዚህም ሳቢያ ሰው ንዴቱን ካልተቆጣጠረ የበለጠ ስህተት እንድጨምር ያደርጋል፡፡ በኔም ደርሶብኛል፡፡ ሰው ግን ከስህተቱ ይማራል፡፡ ዋናው ጥበብ ግን ንዴትን ተቆጣጥሮ የሚያስፈልገውን ነገር ግብ እንዲመታ ማድረግ መቻል ነው፡፡ አስፈላጊ ቦታ ላይም ሰው ተናዶ እልህ ቢይዘው እንደ ደካማነት መቆጠር የለበትም፡፡ የሚያናድድም፣ የሚያታግልም፣ እልህ የሚያስጨርስም ሰውም ሆነ ሁኔታ አለ፡፡ እንደ ቦታውና እንደ ሁኔታው ይለያያል፡፡ ዞሮ ዞሮ አንደኛውን ደረጃ የሚይዘው የሚያሸንፍ ብቻ ነው፡፡ የሚሸነፍ ግን እስከሚነሳ ድረስ ሁል-ጊዜ መሬት ላይ ነው፡፡ ይህንን ማስታወስ ሊጠቅም ይችላል፡፡ ሰው ደግሞ መሬት ላይ ሁል-ጊዜ መንከባለል የለበትም፡፡ ትግል ማለት በማንኛውም ገንቢያዊ እውቀት የግል ህይወትን ለማሻሻልም ሆነ ሃገርንና ወገንን ለመጥቀም መታገልንም ይጨምራል፡፡ ብዙ ሰወች መታገል ምን እንደሆነ በትክክል አይረዱትም፡፡
ለምሳሌ በቃ ውኃም ቀጭን ነው፤ ሰማይም እሩቅ ነው ብለው ዝም ይላሉ፡፡ በውኃ ቅጥነትና በሰማይ ርቀት ውስጥ ግን ብዙ መታወቅ ያለበት ነገር አለ፡፡ ውኃ ለምን እንደቀጠነና ሰማይም እንዴት እደራቀ ለማወቅ ብዙ ግድ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በቀላሉ ማድረግ የሚቻለውን ለማድረግ ማቃት የለበትም፡፡ ሰው ስህተቱ ሲነገረው ከመናደድ ይልቅ ትምህርት መውሰድ በተሻለ ነበር፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተፈታታኝ ጥያቄ ሲቀርብላቸው እልህ ይይዛቸውና ተናደው በግላቸው የተጠቁ ይመስላቸዋል፡፡ በተፈታታኝ ጥያቄ ከመናደድ ይልቅ ነጻነታቸውን ሲያጡ ተናደው በታገሉ ነበር፡፡ ግን መታገል ማለት ቡጢ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ለግል ጉዳይ በንዴትና በእልህ ከመጠመድ ይልቅ፤ መታገል ከመሬት ሆኖ አሸናፊውን ከማየት ያድናል፡፡
እስካሁን አስተያየቶች አልተሰጡም፡፡