ኣምጣለች ጭንቀት ኖራለች መከራ
እጣዋ ሆነና ጭንቀቷ ኣያባራ
እምባዋ ኣያባራ
ታለቅሳለች ዛሬም ልጆቼን እያለች
ታሪክ ጽናትሽ ተሰምቶኝ
የምሆን ጭንቀት ያስጮሖኝ
የምርብሽ የማነባሽ
የምትርቤኝ የምርብሽ
ለዘንድሮ ያገሬ ሰው
የሆንከው የመኖር ጉልበት
ታሪኩን ንቆ ለከርሱ
ውስጡን ደብቆ ምላሱ
ደስ ብሎኛል እያለ
ባንተ ቅቤ እየታሸ
ውስጡን ንቆ እንደሸሸ
አይ ፍርሓት ጠቢቡ
እኔና አንተ እንሁን
አነጣጥሮ ኣንጣሪ ጋሻ ለወገኑ
የነፃነት ፈትል ደጋን ማባዘቻ።
ከሄኖክ የሺጥላ መጽሐፍ የተወሰደ ፍቅርተ ነጋሳ
No comments:
Post a Comment