Wednesday, November 6, 2013

የጥፋት መልእክተኞች የሆኑት የወያኔ ደህንነቶች ጉድ

ሔለን ንጉሴ/ከኦስሎ ኖርዌይ
እንደወትሮዬ ሁሉ ማምሻው ላይ ጆሮዬ ለመስማት የሚጓጓውን የኢሳት ሬዲዮ ዜና ለመስማት ሶፋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከፈትኩና የተለያዩ ዜናዎችን እያደመጥኩ ሳለ በድንገት መሃል ላይ ያልጠበኩትና በጣም አስደንጋጭ ልብን እንክት አድርጎ የሚሰብርና ዛሬስ ምን አለበት መሣሪያ ቢኖረኝ እና አንድ ወያኔ ገድዬ ቁጭቴን በተወጣሁ የሚል እልህና እንባ ተናነቀኝ ግን ምን ዋጋ አለው ማድረግ የቻልኩት አንድ ነገር ብቻ ነው ኩርምት ብዬ አንገቴን በእግሮቼ መሃል ደፍቼ ለረጅም ሰአታት ትካዜ፤ ንዴት፤ እልህ፤ ቁጭት፤ ብስጭት እና የጥቃት ስሜትን በማስተናገድ የልብ ምቴ ድም ድም….. ለረዥም ጊዜ አሰብኩ አወጣሁ አወረድኩ ሐገራችን ወዴት እያመራች ነው አምላኬ ሆይ አልኩ እስከመቼስ ነው በዚህ መልኩ የምንቀጥለው እያልኩ ምን አለፋችሁ ሙግት ከእግዚአብሄር ጋር ገጠምኩ።
የምሬን ነውነገሩ እንዲህ ነው የወያኔ የጥፋት መልእክተኞች /እራሳቸውን ደህንነት ብለው የሚጠሩ ጭራቆች/ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ የምክር ቤት አባል የሆኑትን አቶ አበበ አካሉን ከመንገድ ይዘው ወዳልታወቀ ጨለማ ቤት ውስጥ በመውሰድ አስገድዶ መጠጥ በመጋት እራሳቸውን እንዲስቱ በማድረግ ከፍተኛ ድብደባ ፈፀሙባቸው። ይህስ ባልከፋ ነበር ድብደባውና እንግልቱን ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ አቶ አበበ ተላምደውታል የዛሬው ግን ከወትሮው ለየት ያለና እስከዛሬ ከሰማናቸው በደሎች ሁሉ የከፋ በደል ከመሆኑ የተነሳ በአንደበት ለመግለፅ የሚዘገንን ባህላችን ያልሆነ በወንድ ልጅ ላይ ሊፈፀም የማይገባ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ተፈፅሞባቸው መንገድ ላይ መጣላቸውን ከአንደበታቸው ሰማሁ መቼም ሁላችንም ኢሳትን የምንከታተል ዜናውን እንደሰማን አምናለሁ።
ታዲያ እውን እነዚህ የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ኢትዮጵያውያን ናቸውን? ወይንስ ከጥልቁ የተላኩብን የሰይጣን መልዕክተኞች በሰው አምሳል በአካል የሚንቀሳቀሱ ጭራቆች ለክፋት ስራቸው ቃላት የማይገኝላቸው እርኩሶች ናቸው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ አይነት የከፋና የወረደ ሰውኛ ያልሆነ  የከፋ አስፀያፊ በደል በዜጎቿ ላይ ተፈፅሞ ሰምተን አናውቅም ወደፊትም እንዲህ አይነቱን እርካሽ በደል የሚፈፅም ይገኛል ብዬ አላምንም ከነዚህ ከወያኔ የጥፋት ልጆች በስተቀር። እኛም ከዚህ በላይ ምን እስከሚደርስብን ድረስ እንደምንጠብቅ አላውቅም በቁሙ ወንድ ልጅ ስብእናው ሲገፈፍ ሲዋረድ በመሀል ከተማ ኣዲስ አበባ ውስጥ ይሄ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም! ኧረ ያገሬ ሰው ንቃ ኧረ ያገሬ ወጣት ተነሣ ነግ በኔ ነውና እነኚህ የጥፋት መልእክተኞች ሐገራችንን ለማፈራረስና የተቃወሟቸውን ሁሉ ይህን ተመሳሳይና የከፋ ድርጊት በመፈፀም ያለ አንዳች ተቃዋሚ ብቻቸውን የመጡለትን ትውልድ የመግደልና የማኮላሸት አላማ እና የተጠናወታቸውን የክፋት ሴሰኝነት በሁላችንም ላይ ከመፈፀም ወደኋላ አይሉምና እንንቃ! እንቃ! እንንቃ! እራሳችንንም ሐገራችንንም ከወረራት ወረርሽኝ ነፃ ማውጣት የምንችለው ሆ ብለን በአንድ ላይ ስንነሳ ብቻ ነው።
የምንችል መሳሪያ ይዘን እንዝመት እንዋጋ ለሐገራችን ታሪክ ሰርተን እንለፍ ይህንን ደግሞ አንችልም የምንል ሁሉ ደግሞ ባለን ችሎታና ሞያ ቅስቀሳ በማድረግና ወጣቱን በማንቃት ትክክለኛ መረጃ እንዲደርስ በማድረግ እነኚህን አረመኔዎች ባገኝንበት ቦታ ሁሉ ማሳደድ መቻል አለብን።  በተለይ በዲያስፖራ የምንኖር ሁሉ ይህንን አረመኔ ጨካኝ ሴጣኒዝም የሆነ አገዛዝ ከሐገራችን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ውስጥ ከፍተኛውን ሚና መጫወት አለብን ይህ ትግል ትውልድ የማዳን ትግል፤ ታሪክ የማቆየት ትግል ነው የኢትዮጵያ ወጣቶች ዛሬ ወያኔ እንዴት አሽመድምዶ ሽባ አድርጎ እንዳስቀመጣቸው ሁላችንም እናውቃለን ዛሬ አቶ አበበ አካሉ ላይ የተፈፀመው ድርጊት በስንት ወጣት ወንድሞቻችን ላይ እንደተፈፀመ መገመት አያቅተንም ይህ አይነቱ በደል ባህላችን አይደለምና ውርደትና ነውርም ስለሆነ ባለመነገሩ ነው እንጂ ብዙዎች በጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ እርግጠኛ ለመሆን ብዙ መረጃዎች አሉ ነገሥ? በእኛ ወንድሞች እና ቤተሰቦች ላይ ላለመፈፀሙ ምን ዋስታና አለን? ስለዚህ ጥቃቱ የሁላችንም ነውና ትውልድ ሳይጨርሱ የሰይጣን መልእክተኞቹን በዚህ ይብቃቸው ብለን የማስቆም የዜግነት ግዴታ ሁላችንም አለብን ይህን ትግል መተኪያ የማይገኝለትን ውድ የሆነውን ህይወታቸውን ለሐገራቸው ክብር መስዋእት ለማድረግ ቆርጠው ጫካ ገብተው የጀመሩልን ወንድሞች እና እህቶቻችንን አሉ በደል በቃ የግፉ ፅዋ ሞልቷል የምንል ሁላችንም በገንዘብ ማገዝ አለብን የምንችለውን ያህል እንረዳለን ብለን ይህ ትግል አይቋጭም ከምንችለው በላይ የሚያምረንን ሁሉ ይቅርብኝ ይህ ግፍ ይብቃ፤ ይቁም ብለን እንርዳ ያለንን ሃይል ሁሉ ተጠቅመን እነዚህን ሐገራችንን እና ህዝባችንን ለውርደት የዳረጉ ጭራቆች ወደ መጡበት እንዳይመለሱ አድርገን ለመሸኘት መቁረጥ አለብን ከቆረጥን የያዝነው እውነት ነውና እናሸንፋለን ድል ሁልጊዜም ከተጨቆኑ ጋር ናትና ።
በአቶ አበበ ላይ የተፈፀመው ግፍ እጅግ ከምለው በላይ ልቤን በሐዘን ሰብሮታል እግዚአብሔር ለክፉዎች ብድራትን ይከፍላል ሁሌ እንደጨለመም አይቀርም ይነጋል ለአቶ አበበ በርቱ ከጎኖት ነን እግዚአብሔር ጤናቸውን እንዲሰጣቸው እየተመኘሁ ለወያኔ መልእክተኞች ደግሞ ትግሉ ይቀጥላል እናንተ ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጋርም እየተጣላችሁ ስለሆነ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ በሰፈሩት ቁና መሰፈሩ አይቀርምና ኢትዮጵያ ሐገራችን የቱንም ያህል ብትለፉ ብትደክሙ የአምላክ ቃል ኪዳን አላትና ለዘላለም
ትኖራለች።

የአንድነት አባልና የብሔራዊ/ም/ ቤት አባል የአቶ አበበ አካሉና የሰርካለም ፋሲል አሳዛኝ የበደል ታ

ሐገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክልን
 hel2

No comments: