ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌድራልዋናኦዲተርለተወካዮች ምክር ቤት የ2005 በጀት አመት ሪፖርትን ባቀረረበት ወቅት በ77 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ 8 መቶ 87 ሚሊዮን 45 ሺ 264 ብር ከ60 ሳንቲምያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን ይፋ አድርጓል።
የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ በአምስትመስሪያቤቶች ውስጥ በተደረገ የናሙና ጥናት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱም ተገልጿል።
አምና መከላከያን ጨምሮ በተደረገው ምርመራ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ጉድለት መገኘቱ ይታወቃል። አብዛኛው የገንዘብ ጉድለት የተገኘው ከመከላከያ ሚኒስቴር ነው። ይህ የገንዘብ ጉድለት በምን መንገድ እንደተፈታ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
No comments:
Post a Comment