(በጌታቸው ፏፏቴ)
ህወሃት ከእውነተኛው መንገድ ወጥተን የተሳሳተ መረጃ እንድንቀበልና ተንበርክከን የዝንተ ዓለም ተገዥዎች እንድንሆን ከጠላት አገሮች
ጋር በመወገን የሚሞግተን ለምንድን ነው?
የሲኖዶሱ ቀኖና ተጥሷል ፤መንግሥት በኅይማኖት ጣልቃ ገብቷል ፤ሕገመንግሥቱን ደፍሯል በሚል የኅይማኖት አባቶች ፤ክርስቲያን
የሆነው ምእመናን ደጋግመው ለሁለት አሥርተ ዓመታት ጮሁ፤ የኅይማኖት መሪ ፓትሪያርክን አስፈራርቶ ከመንበራቸው በማውረድ
የመንግሥት ፖለቲካ ሥልጣን አስጠባቂ የካድሬ ፓትሪያርክ በድፍረት ሾማችኋል በሚል በተደጋጋሚ ተወገዙ ውሸት ነው ብለው
ሊሞግቱን ሞከሩ። በመሆኑም ሥርዓተ እምነቱና የክርስትና ኅይማኖቻችን ተሸርሽሮ የእግዚአብሔርን ቃል ጠብቆ የሚቆምና ውግዝተ
ማሪዮስ የሚል የኅይማኖት አባት እንዳይኖረን በንቃት ተሰርቶበታል አሁንም «የትግራይ ወንበዴዎች እጃቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ኅይማኖት እንዲያነሱ እንጠይቃለን። የማያነሱ ከሆነ እንደ ሰማዕቱ ጴጥሮስ የሞትን ጽዋ ሳንፈራ ለሃይማኖታችን ስንል
እንጋፈጠዋለን። ከዚህ የባሰ ሊመጣ የሚችል ነገር የለምና። ይህ ድርጊት በእስልምና ኅይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ በባህሪው ከፍቶና
ሆነ ተብሎ መንግሥታዊ ሃይማኖት ለማድረግ እየተሞከረ ነው። ውጤቱ የከፋ እንደሚሆንና የህዝብ እልቂት እንዲነሳ የተጫረ እሳት ሲሆን
የስላሙ ሕ/ሰብ ግን ሕጋዊነት ለብሶ የእምነት ነፃነታቸው እጃቸው እንዲመለስ እየታገሉ ይገኛሉ። ይህንም በተደጋጋሚ ለዚህ ጎሰኛ ቡድን
ተነግሮት አልሰማ ብሎ እየሞገተን ነው።
ፍርድ ተጓደለ ድኻ ተበደለ ብሎ ፍትሕ የሚሰጥ ዳኝነትና መልካም አስተዳደር የለም ሥርዓቱ ዘግጧል ብለን ነገርናቸው እየነገርናቸውም
ሊሰሙ አልቻሉም።እስከ አሁንም የጫካ አስተሳሰቡን ያልቀየረ ከአንድም ጎሳ አልፎ በሰፈር የተደራጁ አስተሳሰበ ግትሮች የኢትዮጵያን
ህዝብ ማስተዳደር የሚያስችል ጥንካሬና ብቃቱ የሌላቸው መሆኑን ራስቸውም ተቀብለውት እያለ እንዲያውም ልማታዊ መንግሥት የሚል
ስያሜ ሰጥተውት ይገኛል።ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንድ ስንዝር ማለፍ አይቻልም የህወሃት ካድሬ የአስተዳደር ትምህርት ቢወስድ ስለዳኝነት
ቢሰለጥን ከዚህ በላይ ለውጥ ማምጣት አይችልም። እድገቱን ጨርሷልና ከዚህ በኋላ የሚጠብቀው ሥልጣን በሰላም ማስረከብ ፤
የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅና በቡድንም ሆነ በግል በሕግ ለሚቀርቡ የሕግ ጥሰት ክሶች አምኖ መቀበልና የሚፈረደውን ፍርድ
በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ወይም ይህን ድንበሩን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥን የመከላከያ ኃይል የስለላ ድርጅትና ቤተሰቡን እያንገላታ
የሚገኘውን ፖሊስ በተለመደው መንገድ አሰልፎ ከህዝብ ጋር መግጠምና በህዝብ ዱላ ተወግሮ ወደ መቃብር መውረድ ነው።
በኢትዮጵያ ስም በየአገሩ የተከፈቱ የኤምባሲና የቆንስላ ጽ/ቤቶችን ሞልተው የሚገኙት «የትግራይ ወንበዴዎች» የጎሳ አባላት ሲሆኑ
መደበኛውና ዋናው ተግባራቸው የካድሬ ሥራ መስራት ነው፦ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ተቋማትን መሰለል መሀል ገብቶ መከፋፈል፤
በእስላሙም ሆነ በክርስቲያኑ እንዲሁም በሲቪክ ማህበራት እየሰሩት የሚገኘው ይህ ሲሆን በኩየት፤ የመን፤ ሊቢያና ሳውዲ ዓረቢያ
እንደተመከለትነው ከሀገር ያስወጧቸውን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ከዓረብ ፊውዳሎችና ፖሊስ ጋር በመረባረብ አንገታቸው በገጀራ በአደባባይ
እንዲቀላ፤ ሴቶች እንዲደፈሩ በመተባበር የተፈፀመ ተግባራቸውን እንጅ ጽሕፈት ቤቱ በማን ስምና ለምን ዓላማ እንደሆነ ቢያውቁ ኖሮማ
እንካን በአደባባይ መገደል ለእስራትም የሚያበቃ ችግር አልፈጠሩም።ከዚህ አንፃር ስናየው ኢትዮጵያዊነቱን የተጠየፈ የመንግስት ኦፊሻል
ምን የሚሉት ነው? በጎረቤት አገርም ሆነ ራቅ ባሉት አገሮች እነዚህ የደደቢት ደደቦች«የትግራይ ወንበዴዎች» በኢትዮጵያ ስም
የተፈረመው ዓለም አቀፋዊ ውሎች ደንቦችና ሥርዓቶች ተጥሰዋል፦ኬኒያ ፤ ደቡብ ሱዳን ፤ ጅቡቲ ፤ ሱዳን ፤ ዩጋንዳ የህወሃት አፋኝ ቡድን
የሚያደርጋቸውን ሕገወጥ ድርጊቶች ካስተዋል በቂ ማስረጃ ናቸው። በትክክልም ጣልቃ-ገብነት ይላሉ ይህ ነው። የተማረ የሰው ኃይል
እንዲኖር የሚያደርግ ሥርዓተ ትምህርት ሆነ ተብሎ ተቀይሯል ። እንደጎሳው ሁሉ ሥርአተ ትምህርቱም ከአንዱ ክልል ሌላ ከሌላው ክልል
ሌላ የተለያየ የምህርት አሰጣጥ ነው ያለው በዚህ ላይ በትምህርት ጥራት ደረጃ ሲታይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመረቁ ሥራ
እንዲያገኙ የሚያደርግ አለመሆኑን መናገር ይቻላል። እነዚህ ደረቆች ግን ግግም ብለው የሚሞግቱን በውጭ እርዳታ ትምህርት ቤት
መከፈቱንና በየ ዓመቱ ተመርቆ የሚወጣውን የሰው ኃይል ብዛት በማስላት ነው። በነገራችን ላይ ከታችኛው እርከን እስከ ላይኛው ድረስ
ያለው የዘመናዊ ባለሥልጣቱ ልጆች የሚማሩት ውጭ አገርና በከፍተኛ የገንዘብ ኃይል ነው። «ሌላው አርሶ አደሩ ምረጠን ስንለው
ይመርጠናል ፤ተነስ ስንለው ይነሳል ፤ተኛ ስንለው ይተኛል፤ ተሰለፍ ስንለው ይሰለፋል። የተባለው መደብ አርሶ አደሩ የመሬት ጥያቄ
ያነሳው ትናንት አይደለም ከ1966 አ/ም በፊት ነበር አሁንም የመሬት ጥያቄ አልተመለሰም። በገሌ ጊዜ በእንትና ቅብጥርሴ ጊዜ የመሬት
ጥያቄ ተመልሷል የሚሉ መጀመሪያ ራሳቸውን ቢፈትሹ መልካም ነው። እንግዲህ ይህን መደብ(አርሶ አደሩን) እታች ያለውን ሰፊውን
አምራች ኃይል በቀበሌ ታጣቂ ፤ በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ፤ በአጋዚ ሠራዊት በፖሊስና ደህንነት(ስለላ ኃይል) በህወሃት መከላከያ ሠራዊት
ጠፍንገው እንደያዙትና መላወሻ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ ነበር በረከት እንዲያ እየተሳለቀ ስለ ገበሬው ወይም አርሶ አደሩ ሊነግረን
የከጀለው በረከት የአርሶ አደሩን አቅም ጥንካሬ ከኢህአፓ እስከ ኢህዴን ባደረጋቸው ትግሎች ጠንቅቆ ያውቀዋል አሁን በብረት በተገነባግንብ ስለሚኖር ሺህ ጦር በፊቱ ሽህ ጦር ከኋላው ስለሚያጅበው ግድ የለም ይመጻደቅ። እውነታውን አጥቶትም አይደለም። ጌታዋን
ያመነች በግ ላቷን ----እንደሚባለው እድሜ ለህወሃት ይበል እንደሱማ ሥራ በዙ ብዙ ነገር ነበረበት። ጊዜ ያፋርደናል በዚህ ጉዳይ ለዛሬ
እዚህ ላይ ላብቃ።
መሳይ መኮንን የምወደው የኢሳት ጋዜጠኛ ነው። የህወሃትን ቱባ ቱባ ባለ ሥልጣናት ጭንቅላታቸው ግን ባዶ ቀፎ የሆኑትን እየደወለ
በጥያቄ ሲወጥራቸውና ሲደናገጡ የሚሉትን ስሠማ በጣም ያስደነቅኛል መሳይ የሌለው የባለሥልጣን ስልክ ያለ አይመስለኝም።በዚህ
ምክንያት የሱ ፕሮግራም በሚቀርብበት ቀን አንዷም ወሬ አታመልጠኝም። ማክሰኞ ሚያዚያ 1ቀን 2014 ዓ/ም በአሜሪካ የዘመን
አቆጣጠር ከአንድ የአርማጭሆ ተወላጅ ጋር ያደረገውን የራዲዮ ቃለ-ምልልስ ሰሰማ በዚህ ህወሃት በሚንሰፈሰፍበት የኢትዮ-ሱዳን
መካከል በሚገኘው በጎንደር ክፍለ ሀገር የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ አንድ መልዕክት ማስተላለፍ ያለብኝ መሆኑን በመገንዘብ ብዕሬን
ከወረቀቴ ጋር ማገናኘት ጀመርኩ። ጉዳዩ ወደ ኋላ 26 ዓመት መለሰኝ « ሁመራን ስንቃኛት» በሚል የካሣ ሸሪፎ አሁን( የብሔር
ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ) በሆንው የቀድሞ የኢህዴን ታጋይ የሁመራ ጉብኝት መነሻ የታተመ ጋዜጣ ካርቱም ሱዳን እያለሁ
አንብቤ ነበር።ያኔ በህወሃትና ኢህዴን የነበረውን መገፋፋት አውቅ ስለነበር ሁመራን ከያዙ ጀግነዋል ማለት ነው ብየ ነበር። በኋላ ግን ነገሩ
የተገላቢጦሽ ሆኖ ተገኘ። ወልቃይት፤ጠገዴ፤ጠለምት ወደ ትግራይ ተካለለ ። የኢህዴን ታጋይ የነበሩ እነዚህ አካባቢዎች ለምን ወደ
ትግራይ ይካለላሉ ብለው ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ተገድለው ውሃ እንዲወስዳቸው መደረጉን እኔም ከኔ በፊትም ይህን ጉዳይ ይፋ
ማድረጋችን ይታወሳል ሌሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ ዙሪያ ላነሱት ጥያቄና የሕወሃትን የበላይነት ተቀብለን አንታገልም ያሉትን
የኢህዴን ታጋዮች ህወሃት አስወግዷቸው በሚል ቀጭን ትዕዛዝ መሠረት ጉዳይ አስፈጻሚው የኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በተለይም
ታምራት ላይኔ፤አዲሱ ለገሰ፤ ተፈራ ዋልዋ፤ሕላዊ ዮሴፍ፤ታደሰ ካሣ፤በረከት ስምኦን፤ካሣ ሸሪፎ ደርግ ከመውደቁ በፊትና ደርግ ከወደቀ
በኋላ«ዝም ብለህ ብትገዛ ይሻልሃል» አይነት አጥብቀው የሚከራከሩትን ደብዛቸውን ማጥፋታቸው ግልጽ ነው ።ነገሩ በዚህ አላበቃም ወደ
አርማጭሆ ቀጠለ። ከሱዳን ተመላሽ ወገን በሚል በአብደራፊና አብርሃጅራ የትግራይ ተወላጆችን ማስፈር ተጀመረ። ይህም እስከ ቋራ
ወረዳ የሚደርስና ጎንደር ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን በር የሚዘጋ ሴራ ነው።ጉዳዩን ወደተግባር ለመተርጎም ወሳኞቹና አስፈፃሚዎቹ ፦
ውሳኔው ከህወሃት ይተላለፋል የአማራው ክልል ባለሥልጣናት ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋሉ።ያየነው ጥሬ ሀቅም ይኸኑ ነው።
«እንደ ልማድ አድርገነው ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል።» የሚለውን የዘመኑ የፖለቲካ አነጋገር እየተቀበልን ስናስተጋባ መክረማችንን
ሰከን ብለን በተረጋጋ መንፈስ ማሰብ ከቻልን በፍጹም «ውሸት እውነት ሊሆን አይችልም» ለኔ በግሌ ይህን አይነቱ የአነጋገር ፈሊጥ
ተቀብሎ ማስተናገድ ከራስ ሕሊና ጋር የመጣላትን ያህል አድርጌ ነው የምቆጥረው። ዋሾው ማን ነው? ለምን ይዋሻል? ውሸታሙ ሰው
ወይም ድርጅት በመዋሸቱ የሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው? መልሱ ምን አልባት ሆዳምነት ይሆናል ወይም የተንበርካኪነት በሽታ። ፈርቶ
ወይም ለሆድ በማደር የሚፈፀም ድርጊት ደግሞ የሕሊና ሰቀቀን ሕይወቱን እየረበሸው ለጊዜው ሆዱን ሞልቶ ሊያድር ይችል ይሆናል
ወይም በወረራና ዝርፊያ ከሚሰበሰበው የህዝብ ሀብት ትንሽ የቤት መስሪያና በባንክ የሚያኖራት ሳንቲም ያገኙ ይሆናል ። ከሕዝብ
የተዘረፈ ሀብት (ፀጋ) የዚያ ሰው ወይም የነዚያ ሰዎች ሊሆን አይችልም። ጤና የሚያሳጣ ሀብት ደግሞ እንደ ጤዛ ሲነጋ ፀሐይ ሲሞቅ
የሚረግፍ ነው።ምክንያቱም ጊዜ ተለዋዋጭ ነውና መሬት አልበቃህ ብሏቸው የነበሩ የደርግ ሹማምንትን የመጨረሻ ሁኔታ
ተመልክተናልና። «ቃልህ ከሚጠፋ የወለድከው ልጅ ይጥፋ ይባል የለም እንዴ!» ውሸታምን ማስተናገድ እንዲያው ለአፍ ማሟሻ ወይም
ከድብርት ለመላቀቅ ለአንዳፍታ እገሌ እንዲህ ብሎ ቱሪናፋውን ለቀቀ ከማለት በስተቀር ውሸታምነት ከሕብረተሰቡ የሚነጥል ለራሱ
ለዋሾው ልጆችም የሞራል መውደቅን የሚያስከትል አደጋ ያለው የውስጥ ክፋትና ራስን አለማመን የሚያስከትለው ህመም ነው።
በማንኛውም አገር ምርጫ ሲካሄድ ለምርጫ በእጩነት የቀረበው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያችን ወንበር እስከሚይዝ ድረስ እሱ ቢመረጥ
በዚያች እሱ በተመረጠባት አገር ወይም ክፍለ ሀገር ህዝብን የሚጠቅም ብዙ ነገር እንደሚሠራ ቃል ይገባል። የገባውን ቃል ግን ስድስት
ወር እንኳን መጠበቅ አይችልም። የኋላ ኋላ ደግሞ ከዚያ ከመረጠው ህዝብ መሸሸት (መደበቅ) ይጀምራል። ከዚህ ዓይነቱ አደጋ የዳኑ
በጣት የሚቆጠሩ ብቻ ናቸው። እስቲ የትኛው ድርጅት ነው ያልዋሸው? የትኛው የፖለቲካ መሪ ነው ያልዋሸው? የትኛው ፕረዘዳንት ነው
ያልዋሸው?በእውነት እንነጋገር ከተባለ ሀቁን ሁላችንም አናጣውም። የዛሬው አነሳሴ የህወሃትን ውሸትና ያስከተለውን አደጋ በመመከትና
ባለመመከት የታዘብኩትን የህወሃትን መገለባበጥና ጧት የተናገሩትን ማታ መድገም አለመቻል እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ወኔና ባህሪ
አለመኖር ለመመስከር ነው።
ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በማለት የተደራጀው (ህወሃት) ምን አይነት ድርጅት እንደሆነ ከየት ተነስቶ የት እንደ ደረሰ ብልሹ ታሪኩ
ሚዲያ ማጣበቡን ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ለዛሬ ደርግ ይጠቀምበት የነበረውን የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ልዋስና «የትግራይ
ወንበዴዎች» በማለት የሀገራዊና መንፈሳዊ ሞራል ያልፈጠረለትን ድርጅት በሚመለከት እንደሚከተለው ለመግለጽ እሞክራለሁ።
መንፈሳዊ ሞራል የምለው ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለው እሱን የሚመስሉትን ፍጡራን በጭካኔ የሚያሳድድ ፤ የሚያስር ፤ የሚገድል ፤
የሚያስርብ እግዚአብሔርን የማያምን …ወዘተ ለማለት ነው። ለዚህ ህወሃት ( የትግራይ ወንበዴ) ቡድን ጥሩ ምሳሌ ነው።ሐገራዊ ሞራልየሌለው በኔ እይታ ድንበሩን የማያስከብር ፤ ሰንደቅ ዓላማውን መለያ አርማውን የማይቀበል ፤ የሀገሩን ታሪክ የሚያቆሽሽ፤ ዜጎቹን ነጣጥሎ
የሚመለከትና አስተሳሰበ ጠባብ ፤ የማየትም ሆነ የማሰብ አድማሱ የተቀለበሰ ፤ ሕሊናው ለባእድ ተገዥነት ያደረ ፤ ራሱን ከሕግ በላይ
ያደረገና ሕግን የረገጠ ፤ በነብስ ግድያ የተሠማራና ደም ያሰከረው ፤ ለንዋይ ባለው ሱሱነት ምክንያት የሀገሩን ዜጎች በማፈናቀል የሕዝብን
መሬት የሚሸጥ ፤ የሕዝብን አመኔታና ይሁንታ ሳይኖረው በወታደራዊ ኃይል አስገድዶ እየገዛ ለመኖር የሚያስብ ስንኩል አስተሳሰብ ያለው
፤ የሴቶችን የሕፃናትንና የአዝውንቶች ከሕ/ሰቡ ውስጥ ልዩ እንክብካቤ እንደሚሹ የማይገባው ማሕይም (ደንቆሮዎች) የተሰበሰቡበት
ተቋም ሀገራዊ የሞራል ብቃት የለውም። ብዙ መጥቀስ ይቻላል ።ህወሃት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዚህ ማሳያ ጥሩ ምሳሌና ሞዴል ይሆናል።
ክፍል አንድ፦ ህወሃት ያወጣውን ማኒፌስቶ እንደተመለከትነው ከአፋር ጀምሮ የኤርትራን አንዳንድ አካባቢዎች ወደ ትግራይ በማድረግ
ከአማራው ክልል ሰሜን ወሎንና ሰሜን ምዕራብ ጎንደርን የትግራይ ክልል በማድረግ ቦርደር ያላት «ታላቋ ትግራይ ትግርኝት ሪፐብሊክን»
መመስረትና አዲስ የአፍሪካ አገር ማስመዝገብ ነበር።በዚህ መሠረት ትግራይ ውስጥ የነበረው የደርግ ሠራዊት ጨርሶ እስኪወጣ ድረስ
የህወሃት ሠራዊት በትጋት የተዋጋበት ወቅት ነበር።ወደ መሀል አገር ጉዞው ሲቀጥል ግን በተለይም ከደብረታቦሩ የጉና ጦርነት በኋላ
የህወሃት ሠራዊት የተዋጋነው ትግራይን ነፃ ለማውጣት ነው ። ትግራይ አሁን ነፃ ወጥታለች ስለዚህ ከዚህ በኋላ አንቀጥልም የሚል
ድምዳሜ ይዞ አመራሩን አስጨንቆት ነበር።እዚህ ላይ የሚያመለክተው ህወሃት ራሱ የሚመራውን ኃይል ሰራዊቱን እየዋሸው መምጣቱን
ነው።በኋላ ግን የህወሃት አመራር የሰራዊት ወላጆችን በመማጸን የሰራዊቱ አባላትን ወደ መሀል አገር ለመግባት የሚደረገውን ጦርነት
እንዲቀጥል ተደርጎ ጉዞው ቀጠለ።ከፋና ኦፕሬሽን በኋላ ዘመቻ ዋለልኝ፤ዘመቻ ቴዎድሮስ፤ዘመቻ ቢሉስማ ውልቂጥማ እየተባለ ተገፋ።
ደርግ ወደቀ የህወሃት ሰራዊት አገሪቱን ተቆጣጠረ። የህወሃት አመራር ቡድን ያላሰበውና ያልተዘጋጀበት ሀገርን የመግዛት ሥልጣን እጁ ላይ
ገባ። በለስ ሲቀና እንዲህ ነው። ደርግ የገጠመው እድል አይነት። የህወሃት ሰራዊት በህግ የተቀመጠውን የሰራዊት ደንብ በመጣስ
ሰራዊትም አስተዳዳሪና መሬት አከፋፋይም መሆን ጀመረ። እኔ በቅርብ በማውቀው አካባቢ ሆነ ተብሎ ሰራዊቱ ያለ ሥራው እየገባ ከባድ
ስህተት ይፈጽም ነበር።ይህም የሚያሳየው አስቀድሞ መሬቱን በህወሃት ደጋፊዎችና ከህወሃት በሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ በይዞታ የማቆየት
ዓላማ እንደነበረ ያመላክታል።ጠቅለል ባለ መንገድ ህወሃት መላ ሀገሪቱን ተቆጣጥሮ ሀብት መዝረፍና የኋላ ኋላ ደግሞ መላ ኢትዮጵያን
ለመግዛት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ህዝብን እርስ በርሱ አናክሶ ኢትዮጵያን አጥፍቶ ታላቋን ትግራይ ትግርኝት ሪፐብሊክ መስርቶ
መገንጠል ወይም ሕዝቡን ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ በማድረግ አምባገነናዊ የሥልጣን እድሜውን ማራዘም ነው(የህወሃቱ ፊታውራሪ ስብሃት
ነጋ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻልን ኢትዮጵያን …..እናደርጋታልን እንጅ ሥልጣን ለአማራ አናስረክብም አይደለም እንዴ?ያለው መቼ ነው
ስብሃት የአማራ ገዥ የሚባል መደብ የነበረው እነማን ነብሩ ቢባል መልስ የለውም የተለመደ ውሸቱን ይነፋ እንደሆነ እንጅ። አንዴ ላይ
ሌላ ጊዜ ታች እየረገጥን የዚህን ወንበዴ ዘራፊና ነብሰ ገዳይ ድርጅት እድሜ ማራዘማችን ስህተቱ የእኛ እንደ ሆነ አምነን ይህን የሕይወት
መቅሰፍት የሆነ ሥርዓት ማስወገድ ካልቻልን ቀጣዩ አደጋ የከፋ እንደሚሆንና ኢትዮጵያዊ ዜጋ በኢትዮጵያ የማይኖርበት ሁኔታ
እንደሚፈጠር ከወዲሁ መገመት አያስቸግርም።እያወቅንም ሆነ ሳናውቅ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ኪሳራ እንዲደርስ አድርገናል።ህወሃት
የሀገር ጥፋት ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ አንዲት ስንዝር ወደ ኋላ አላለም።እኛ የምንፈጥረውን ክፍተት በጣም አድርጎ
ይጠቀምበታል።ትግሉ ህወሃትን ከዚህ ባደረሱት ላይ(ኢህዴን/ ብአዴን) ላይ ፤በህወሃት ሰራዊትና በደህንነቱ(በስለላ ድርጅቱ) ላይ
ማነጣጠር ይገባዋል። ፖሊስ የራሱን መታነቂያ ገመድ በእጁ እንደ ያዘ እብድ ስለምመለከተው አቧራው ሲጨስና ሰማይ ሲቀላ የመጥኔ
ያለህ ማለቱ የግድ ነው።ከላይ የጠቀስኳቸው ተቋሞች ግን የሥርአቱን አከርካሪ ወጥረው በመያዛቸው ዘመቻው በነሱ ላይ ማነጣጠር የግድ
ይለዋል።
ክፍል ሁለት ፦ ማንኛውም ሀገሩንና ሕዝቡን እንደ ሚወድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሃት ዜጎችን ወህኒ ቤት ማጎሩን በእስር ቤት ግፍ የተሞላበት
ስቃይ ማድረስን፤መግደል፤እንዲሰደዱ ምክንያት መፍጠር፤ የሀገር ሀብት የሆነውን መሬት ለፈለጉት እየቆረሱ መስጠትን በተመለከት
የሚሰማኝን ጽፌያለሁ ወደፊትም እቀጥልበታለሁ።በተለይ ግን ለሱዳን እሰጠዋለሁ ያለውን የጎንደር ክ/ሀገር መሬት በሚመለከት ጉዳይ
ዙሪያ ከራሴ ጋር እንድሟገት የሚያደርጉትን ሀሳቦቼን ላካፍላችሁ እወዳለሁ። «አለቃው አጎንብሶ የሚሄድ ጭፍራም አጎንብሶ ይሄዳል»
እንዲሉ የህወሃት መሪዎችና አባላቱም ሥስት ፤አልጠግብ ባይነት ክፉኛ የሚያጠቃቸው ለመሆኑ ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም በተወሰነ
ደረጃ የሚከተሉትን ለመጥቀስ እወዳለሁ። እንደምታውቁት የሰሜን ምዕራብ ጎንደር ፤ ጎጃም እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ምእራባዊ
ክፍል ውሃ ገብና ለም ነው። በአጋጣሚ ሁኔታ ጎንደር ከትግራይ ጋር አካላይ በመሆኑ የዚያን አካባቢ መሬት ለመውሰድ ያልተላከ ሰላይ
የለም። ማስረጃ አንድ። በህወሃት ቤት ጥሩ መብላት ፤ ጥሩ መልበስ ፤ በጥሩ ቤት መኖር ጥሩ የንግድ ድርጅት መኖር እንቅልፍ የማያስተኛ
ችግር ነው።ማስረጃ ሁለት።ህወሃት በገጠሩ አካባቢ ለ17 ዓመት ያህል ሁሉንም ገጠር መርሿል። ደህና ጥሮ ግሮ ሀብት ያፈራ አርሶ አደር
ብዙ የሚያመርትና በርከት ያሉ የቀንድና የጋማ ከብቶች ያለውን አርሶ አደር ሀብታም ብሎ በመፈረጅ ሀብቱ የሚዘረፍበት መንገድ በማሴር
የጠገዴ ፤ ወልቃይት ፤ ጠለምት ፤ አርማጭሆ ፤ አዳኝ አገር ጫቆ ፤ የመተማ ፤ ሽንፋና ቋራ አርሶ አደር ሰርቶ በመብላቱና ለፍቶ በመክበሩ
ሀብቱ እንዲዘረፍ ተደርጓል አሁንም እየተደረገ ነው። የነዚህ አካባቢ አርሶ አደሮች ሌላውን በማፈናቀል ወይም በመግዛት ያገኙት መሬት
ሳይሆን ተፈጥሮ ያደላቸው ነው። የዚህ አካባቢ ህ/ሰብ ርስትና ጉልት በሚል የመሬት ስሪት አይተዳደርም።በማጤ ቀደም አስቀድሞ
የፈለመውን መሬት መንጥሮና አለስልሶ ዘር ዘርቶ ሀብት ማፍራት በህወሃት ቤት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው። የእህቴ ልጅ ከመቶ ሃያ በላይየቀንድ ከብት (ላምና በሬ ሲኖራት) ፍየል ደግሞ ቢያንስ ከ60 እስከ 70 ነበራት እኔ ወደዚህ አገር ሳልመጣ ሽፍታ አብልተሃል ተብሎ
ባለቤቷ $10.000 ብር እንደቀጡት አስታውሳለሁ። በሌላ ወገን ደግሞ ዱር ቤቴ ያሉ ይህን ሰው የመንግሥት ሹመኛ አብልተሃል ብለው
አስገድደው ገንዘብ እንዳስከፈሉት አውቃለሁ።ማስረጃ ሦሥት። ከዚህ ስንነሳ ህወሃት እንዲያ ምራቁ እስኪዝረከረክ ድረስ የሚቋምጥለትን
መሬት ካራሱ አልፎ እንዴት ለሱዳን እንዲሰጥ ወሰነ? የሚለውን ስንመለከት አንድ የተሰወረ ደባ ከበስተጀርባው እንዳለ ያመላክታል።
ከላይ እንደጠቀስኩት« የህወሃቱ ፊታውራሪ» ስብሃት ነጋ እንዲሁም ሌሎች የሱ ጉጅሌዎች ደጋግመው እንዳረዱን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ
ሃይማኖትና አማራውን እንዳይነሳ አድርገን ቀብረነዋል ፤ ከአሁን በኋላ አማራው ወደ ሥልጣን እንዳይመጣ አድርገነዋል ፤ ኢትዮጵያን
መምራት ባንችል---------------እናደርጋለን እንጅ ሥልጣንን ለአማራ አናስረክብም የሚለው ውስጣኔው---ሕዝቡን በተተለመው መንገድ
አባልተን የሚገነጠለውንም እንደ ኤርትራ አስገንጥለን ወደ ትግራይ ሄደን «የመለስን ራእይ» ተግባራዊ እናደርጋለን ከዚያም በሱዳን እጅ
በአደራ የተቀመጠው የአማራው እጣ የሆነው የጎንደርን መሬት ከዚህ በፊት ከተወሰደው በመጨመር ትግራይን ኒዮርክ አስመስሎ ለመኖር
የታሰበ ከመሆን ሊያልፍ አይችልም። ሱዳን
ይገባኛል አላለችም ወይም ለህወሃት ውለታ ስለዋለች የመሬት ድርጎ ህወሃት አይሰጥም ማለቴ አይደለም። ሱዳን ራሷ ያላትን ደቡብ
ሱዳንን አጥታለች ፤ ለቻድ የተሰጠ መሬት አለ ፤ ግብጽ በበኩሏ ከሱዳን መሬት ወስዳለች። እዚህ ላይ የምናየው የአያ በሬ ሆይ! ነገር መሆኑ
ነው። ይህችን ነጥቤን ለመቋጨት መሬቱ ቀደም ሲል ለሱዳን ሊሰጥ ስለሆነ ነዋሪዎችን ልቀቁ መባሉ እንዳለ ሆኖ አሁን ደግሞ
ለኢንቨስተሮች ሊሰጥ ነው በማለት በአንድ ራስ ሁለት ምላስ አይነት ያን ያደኸዩትን መከረኛ አርሶ አደር አካባቢውን ለቆ መድረሻ
እንዲያጣ እየገፉት ይገኛሉ። ኢንቨስተሮች የክልሉ ነዋሪዎች ከሆኑ የአካባቢውን አርሶ አደር የሚያፈናቅል ምንም ምክንያት አይኖርም።
ምሥጢሩ ሌላ ከሆነና ለሱዳን ሰጥተናል የሚለው ከቀጠለ ግን እስራቱና ሞቱ ደርቷል አሁንም ይቀጥላል እንጅ ያን አካባቢ አቧራው
ሳይጨስ ሰማይ ሳይቀላና ጨርሰን ሳናልቅ የሚታሰብ አይሆንም ። ሱዳን ይህን ጠንቅቃ ታውቃለች ህወሃቶችም ይጠፋቸዋል ብየ
አላስብም። ዋንው ዓላማና ቁልፉ ጉዳይ ደም የማፋሰሱ ጥማት ላይ ያለን በሽታ ነው የሚያመለክተው።
ሌላው ክፍል ሦሥትና የመጨረሻ ድምዳሜየ ፦ አሁን ትግራይ ላይ ያለው ሁኔታ ድሮ በታሰበው መንገድ አለመገኘቱ ፤ከአንድም ሁለት
የሚሆኑ የህወሃት ተቃዋሚ ኃይሎች እዛው ትግራይ ውስጥ መፈጠራቸውና ህወሃት በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለው አፈናና ግፍ ፤
የኑሮ ውድነት ያስከተለው ብሶት የትግራይን ህዝብ በህወሃት ላይ እንዲነሳና እንዲያምጽ በማድረጉ የህወሃት እድልም ሆነ የመለስ ራእይ
የጨለመ እንዲሆን አድርጎታል። ህወሃት የትግራይን ህዝብ ልጆች አስጨርሶ ከድል በኋላ በዙሪያው ያሰለፋቸው በቁጥር አናሳ ነባሮችና
አዲስ የድል አጥቢያ እበላ ባዮችን ስለሆነ ይህ የህወሃት አሳፋሪ ድርጊት የትግራይን ህዝብ ያሳዘነ በመሆኑ ህወሃት ከትግራይ ሕዝብ
ተነጥሏል ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የ1976ቱ ማኔፌስቶና የመለስ ራእይ ፤ የታላቋ ትግራይ ትግርኝት ቅዥት
ውሃ የማያነሳ ሆኖ እናገኘዋለን። አሁን መለስ የለም። ስብሃትም በድሮው ስለቱ ሊቆርጥ የሚችልበት ሁኔታ አጠራጣሪ ነው።ምላሱ
መቆለፍ ጀምሯል ሞትም በሩን እያንኳኳበት ነው። ሳሞራና ስዩም የየራሳቸው ችግር( የጤና መታወክ) ገጥሟቸዋል። አባይ ፀሐየ ህወሃት
ከሁለት ሲከፈል የሄደበትን መንገድ ቀይሶ ይቅርታ ከጠየቀ ወዲህ ክብደት የሚሰጠው ሰው አይደለም። በዚህ ላይ በረከትም ሰላም
ይሰጠዋልና የሚናገረውን ይቀበለዋል ብየ አልገምትም። አርከበና ሌሎች ባሳለፉት ጊዜ ባለሀብት ስለሆኑ ኪራይ መሰብሰብና ወደ ንግዱ
ገብተው ትንሽም ብትሆን ቀሪ ጊዜያቸውን ተዝናንተው መኖርን ይመርጣሉ እንጅ እንመክታለን ብለው የሚበረቱ አይመስለኝም። ህወሃትን
ነብስ እንዲዘራ የተሾሙትና ሌላው ካድሬው የህዝብን ቁጣ የሚመክት ፖለቲካዊ አቅም ይኖራቸዋል ብየ አልገምትም። በሌላ በኩል ደግሞ
የሦስተኛው አብዮት መባቻ ምልክት እየታየ ስለሆነ ይህን ቀፋፊ ሥርዓት እንደ ምሰሶ ገትሮ የያዘው የስለላ መዋቅሩና የመከላከያ ሠራዊቱ
ስለሆነ የሕዝብ ልጅ ነኝ ብሎ የሚያምን በኢትዮጵያዊነቱ የማያፍርና የሚኮራ ምርጫው ምን እንደሆነ ይስተዋል አይባልም። ከሥርዓቱ
ጋር አብሬ ነው የምቀበር የሚለው ደግሞ ምርጫው የራሱ ነውና በሰፈረው ቢሰፈር ማንም አይፀፀትም። እንግዲህ ልማታዊ መንግሥት
ተብየው በየቀኑና በየሳምንቱ በየወሩ የሚጭራቸው ህዝብ አስጨራሽ ተንኮሎችና የግጠሙኝ ግፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ውድቅ ሆኖ ህዝቡ
የደረሰበትን በደል በሰላማዊ መንገድ እስከ አሁን ገፍቶ በመምጣት እዚህ ድረስ መጥቷል። ጽዋው ሲሞላ ግን የሚመልሰው የለምና የዘመኑ
ገዥዎቻችን አዲስ ታሪክ እንሰራለን ብላችሁ የሄዳችሁበት መንገድ የሰይጣን መንገድ ስለሆነ መጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር ታረቁ ከዚያ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ራስ እንድትወርዱ ጊዜው ደርሷልና ነገር ሳይበላሽ ብታመልጡ ይሻላል በማለት የዛሬ ጦማሬን በምክር እዘጋለሁ። sourse http://www.ethiomedia.com/broadway/tplf_and_ethiopianness.pdf
ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም በክብር ትኑር!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
ከኢትዮጵያ ሕዝብ ራስ እንድትወርዱ ጊዜው ደርሷልና ነገር ሳይበላሽ ብታመልጡ ይሻላል በማለት የዛሬ ጦማ
No comments:
Post a Comment