ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናት በመያዝ ከአብድራፊ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች
ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በአስተዳደር እና በጸጥታ ችግሮች ምክንያት መማረሩን ተወካዮቹ ተናግረዋል።
አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ህዝቡ በመብራት፣ ውሃ እና በመንገድ ችግር እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላ ተናጋሪ ደግሞ ህዝቡ በድብቅ ጠመንጃ እየተዳደረ መሆኑንና ወረዳው ህዝቡን ማስተዳዳር እንደተሳነው ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል የድብቅ ጠመንጃ ህጋዊ እንዲሆንና ህዝቡ በይፋ ይዞ እንዲንቀሳቀስ መፈቀዱን የተናገሩት ተወካዩ ፣ በምእራብ አርማጭሆ ፈቃድ በመከልከሉ ህዝቡ በድብቅ
ለያዘው መሳሪያ ፈቃድ እንዲሰጠው እየጠየቀ መሆኑን ገልጸዋል
ህዝቡ ማዳበሪያ ያለፍላጎቱ ተገዶ እንዲገዛ መደረጉ አስጸያፊ ነው ሲሉ አርሶአደሩ አክለው ተናግረዋል።
“በከተማው እጅግ ዘግናኝ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸማል” ያሉ አንድ ተወካይ፣ በዚህ አይነት ጉዞ ሌላ ችግር ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለመጭው ምርጫ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ በተለያዩ አካባቢዎች እየዞሩ ከተመረጡ የህዝብ ተወካዮች፣ ከኢህአዴግ ካድሬዎችና ከቀበሌ ባለስልጣናት
ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።
እስካሁን በተደረጉት ውይይቶች ህዝቡ ከፍተኛ የአስተዳዳር በደሎች እንደደረሱበት ሲገልጽ ቆይቷል። esate radio
No comments:
Post a Comment