ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከበው ካደሩ በሁዋላ የተወሰኑ ወጣቶችን እየለቀሙ በማሰር የተቃውሞ ሰልፉን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው።
የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል ዋና አዘጋጅ በላይ ማናየ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ሃላፊ እና የብሄራዊ ምክር ቤት ጸሃፊ ወጣት ሳሙኤል አበበ፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል ፍቅረማርያም አስማማው በደህንነቶች ታፍነው ተወስደዋል።
አካባቢው አሁንም በፖሊሶች እንደተከበበ ነው። አጠቃላይ የቀኑን ውሎ በተመለከተ የሰማያዊ ፓርቲን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ዮናታን ተስፋየን አነጋግረነዋል ።
ውድ ተመልካቾቻችን የሚፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶችን በተመለከተ እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። sourse esat radio
No comments:
Post a Comment