‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ ፖሊሶች የቃሊቲ እስረኞች እቃ ተበረበረ::
#Ethiopia #WPRDF #UDJ #Humanrights #Kality #MinilikSalsawi
#Ethiopia #WPRDF #UDJ #Humanrights #Kality #MinilikSalsawi
የእስክንድር ነጋና የአንዱዓለም አራጌ ማስታወሻዎች ተወስደዋል::ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ የፌደራል ፖሊሶች እቃቸው በድንገት እንደተበረበረና እንደተወሰደ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ቃሊቲ እስር ቤትና አካባቢው በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ተከቦ እንደነበር የገለጹት ምንጮቹ ባልታወቀ ምክንያት የሁሉም እስረኞች እቃ በድንገት የተበረበረ ሲሆን በተለይም ፖለቲካ ነክ ጽሁፎች የሰፈሩባቸው ማስታወሻዎችና ሰነዶች መወሰዳቸውን ከእስረኞቹን ጠይቀው እንደተረዱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ብርበራም የታዋቂው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከ30 በላይ ገጽ የፖለቲካ ትንታኔ ጽሁፎች፣ እንዲሁም የአንዱ ዓለም አራጌ ማስታወሻዎች መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ ማስታወሻዎችንና ሌሎቹንም የእስረኞቹን ንብረቶች እያስፈረመ የወሰደ ሲሆን እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ እስር ቤቱ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment