በዶ/ር ታደሰ ብሩ
1. መግቢያ
“ሰላም ምንድነው?” በሚል ርዕስ ለፃፍኩት መጣጥፍ ከደረሱኝ በርካታ አስተያየቶች ውስጥ “በነካ እጅህ ልማት ምን ማለት እንደሆነ ብትገልጽልን” የሚለው ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል።
ከአሰልቺ የወያኔ ካድሬዎች ክርክሮች አንዱ “ልማታችን፣ ልማታችን” መሆኑ የማውቀውና በራሴም ላይ ከተራ ማሰልቸት በላይ የመብት ጥሰቶች ያደረሰብኝ ጉዳይ ነው። ወያኔ በአገራችን ላይ ላሰፈነው አገዛዝ ተቀባይነት (ligitimacy) ዋነኛ መከራከሪያው “ለኢትዮጵያ ልማትን ያመጣሁ፤ አሁንም በማምጣት ላይ ያለሁ መንግሥት ነኝ። ለወደፊቱም ኢትዮጵያን ለማልማት ከኔ የተሻለ የለም” የሚል ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ (1) ከዚህ በፊት በአገሪቱ ውስጥ ልማት የሚባል ነበር አልነበረም፤ (2) እኔ ልማትን እያመጣሁ ነው፤ ሌላውን ቻሉት፤ እና (3) ለወደፊቱም ከኔ የተሻለ ኢትዮጵያን ማልማት የሚችል የሌለ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሲባል እኔ ለረዥም ጊዜ በስልጣን መቆየት አለብኝ የሚል መልዕክት አለው።
በዚህ ጽሁፍ እነዚህን ሶስቱም መከራከራዎች ውሸት መሆናቸውን ለማስረዳት እሞክራለሁ። ከሁሉ አስቀድሞ ግን “ልማት” በተሰኘው ጽንሰ ሀሳብ ላይ የጋራ ግንዛቤ እንያዝ።
2.የልማት ትርጉም
በዛሬቷ ኢትዮጵያ መብራት ሲቋረጥ፤ ውሀ ሲጠፋ፤ ጤፍ ሲወደድ፤ መንደሮች ሲፈርሱ፤ የመኪና አደጋ ሲበዛ፤ ገበሬዎች ሲፈናቀሉ ሰበቡ ልማት ነው። ማናቸውም ችግር “እድገት ያመጣው ነው፤ ቻሉት” እየተባለ ይታለፋል። ለረሀብ፣ ለጥማት፣ ለበሽታ እና መሰል መጥፎ ነገሮች ልማት ምክንያት ሆኖ ሲቀርብ፤ “መብቴ ይከበርልኝ ብሎ መጠየቅ “በፀረ-ልማትነት” ሲያስከስስ “ለመሆኑ ልማት ምንድነው?” የሚል የጅል አልያም የልጅ የሚመስል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን። ………..
No comments:
Post a Comment