ሃያ ሁለት ዓመት ሙሉ በጎጥ፣ በሀይማኖትና በጥቅማ ጥቅም ከፋፍሎ ከህዝብ ፍላጎት ዉጭ በመግዛት ላይ የሚገኘዉ የህወሀት መራሹ መንግሥት አጭበርብሮ የመግዛት ስልቱ በህዝብ ስለተነቃበትና ተቃዉሞዉ ሁሉን አቀፍ በመሆኑ አጥፍቶ የመጥፋት ዘመቻዉን አጠናክሮ ቀጥሏል::
ይህ ጸረ ህዝብና ጸረ ሀገር የሆነዉ ቅጥረኛ ቡድን ህገወጥ ተግባሩን በሚቃወሙ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ በአጠቃላይና በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እየፈጸመ ያለዉ የወቅቱ የጅምላ ጭፍጨፋ አገሩንና ህዝቡን ለሚወድ ዜጋ የሚያስተላልፈዉ መልዕክት ቀላል አይደለም:: ስለሆነም በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ አገር የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በመካከላችን ያለዉን ማንኛዉንም አነስተኛ ልዩነት አቻችለንና የግልና የድርጅት ጀብደኝነት ትተን በሀገርና በህዝብ አድን አስቸኳይ ተግባር በጋራ እንድንሰማራ ጥሪአችንን እናቀርባለን::
ይህንን ሥርአት የሚመሩና በስርአቱ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂት ደጋፊዎቻቸዉ የተጀመረዉ ሁሉ አቀፍ ትግል ተጠናክሮ ከቀጠለ የሚያመጣባቸዉን መዘዝ ጠንቅቀዉ ሰለሚያዉቁ ያለ የሌለለ ሀይላቸዉን ተጠቅመዉ ትግሉን ማዳፈን ካልሆነም አጥፍተዉ ለመጥፋት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ስለማይኖር ከወዲሁ አዉቀን ትግሉን በስሜት፣ በእልህና በተናጥል ሳይሆን በጥበብ፣ በትዕግስትና በጋራ ማካሄድ ይኖርብናል ::
የነጻነት ትግሉ ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል የሚል እምነት አለን:: በመሆኑም የህዝብ አልገዛም ባይነት በመላዉ ኢትዮጵያ ፍርሀትን ሰብሮ መዉጣቱ ሰሞኑን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት በመራዉ ህዝባዊ ንቅናቄ „የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት“ አረጋግጧል:: ይህንን የቆራጥነት ጅማሮ ፓርቲዉ አመራር በመስጠት ህዝቡ ደግሞ ነጻነት በትግል እንጂ በልመና እንደማይገኝ አዉቆ ድጋፉን መቀጠል አለበት:: እኛ ከሀገርና ከህዝብ ርቀን የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን የገንዘብና የድፕሎማሲ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸዉ መቆማችንን የምናረጋግጥበት ወቅት ቢኖር አሁን ነዉ ::
ከሃያ ሁለት ዓመት ተሞክሮአችን እንደምንረዳዉ ሥርዓቱም ሆነ መንግሥት እንደ ሸክላ ላይጠገን የነከተ፤ እንደ ደረቅ እንጨት ላይታረቅ የገረረ መሆኑን ተገንዝበን ይህንን ሥርአት ከማስወገድ በቀር ሌላ አማራጭ እንደለለ መገንዘብ ይኖርብናል:: ይህ በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቅ መሆኑን ጠንቅቆ የሚያዉቅ ወንጀለኛ መንግሥት ያለ የለለ ሀይሉን ተጠቅሞ በሀገር፣ በህዝብና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል እያንዳንዳችን ከፍርሀትና መደናገጥ ነጻ ሆነን በዘዴ ትግሉን መቀጠል ይኖርብናል::
በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት፣ የደህንነትና በሆዱ ተገዝቶ ወገኑን ለሚያስፈጅ የወያኔ ካድሬዎች በሙሉ ለጥፋት አገልግሎታችሁ የሚከፈለዉ ገንዘብ መከራና ስቃዩን ከምታበሉትና ለሞት ከምትዳርጉት ደሀ ዜጋ የሚመዘበር መሆኑን ተገንዝባችሁ ሰልፋችሁን ከህዝብ ጋር እንድታደርጉ ጥሪአችንን እናቀርብላችኋለን:: ከገንዘብ በላቀ ደግሞ ይህ አሸባሪ መንግሥት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ሃይል አባላት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ህዝብ እንዳልተፈጠራችሁ የባእድ ቅጥረኛ ሰራዊት ቆጥሮ ከትዉልድ ቄያችሁ ዉጭ የሰሜኑን ተወላጅ ወደ ደቡብ፤ የምሥራቁን ወደ ምዕራብ፤ የደቡቡን ወደ ሰሜን እያዘመተህ በቋንቋ እንኳን ተግባብተህ የህዝቡን በደል እንዳትረዳና እንዳትራራለት አድርጎ በዜጋህ ላይ የአውሬ ተግባር እንድትፈጽም እየተደረክ መሆኑን መዘንጋት የለብህም::
በተለይም የሀገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት በህገመንግሥቱ የተሰጠህ ሀላፊነት የሀገርን አንድነት፣ የህዝብ ደህንነት፣ ሀብትና ንብረቱን እንድታስጠብቅለት እንጂ የጥቂት የማፍያ ቡድኖች የቤት አሸከርና የወንጀል ፈጸሚያ መሣሪያቸዉ እንድትሆን አይደለም :: ስለሆነም ጊዜዉ ሳይረፍድብህ እጅህ በተጨማሪ
Hypo Vereinsbank, Konto:104532187, BLZ:70020270 , Verwendungszweck :Pro Ethiopia Tele:-ይህ ጸረ ህዝብና ጸረ ሀገር የሆነዉ ቅጥረኛ ቡድን ህገወጥ ተግባሩን በሚቃወሙ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ በአጠቃላይና በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ እየፈጸመ ያለዉ የወቅቱ የጅምላ ጭፍጨፋ አገሩንና ህዝቡን ለሚወድ ዜጋ የሚያስተላልፈዉ መልዕክት ቀላል አይደለም:: ስለሆነም በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ አገር የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በመካከላችን ያለዉን ማንኛዉንም አነስተኛ ልዩነት አቻችለንና የግልና የድርጅት ጀብደኝነት ትተን በሀገርና በህዝብ አድን አስቸኳይ ተግባር በጋራ እንድንሰማራ ጥሪአችንን እናቀርባለን::
ይህንን ሥርአት የሚመሩና በስርአቱ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂት ደጋፊዎቻቸዉ የተጀመረዉ ሁሉ አቀፍ ትግል ተጠናክሮ ከቀጠለ የሚያመጣባቸዉን መዘዝ ጠንቅቀዉ ሰለሚያዉቁ ያለ የሌለለ ሀይላቸዉን ተጠቅመዉ ትግሉን ማዳፈን ካልሆነም አጥፍተዉ ለመጥፋት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ስለማይኖር ከወዲሁ አዉቀን ትግሉን በስሜት፣ በእልህና በተናጥል ሳይሆን በጥበብ፣ በትዕግስትና በጋራ ማካሄድ ይኖርብናል ::
የነጻነት ትግሉ ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል የሚል እምነት አለን:: በመሆኑም የህዝብ አልገዛም ባይነት በመላዉ ኢትዮጵያ ፍርሀትን ሰብሮ መዉጣቱ ሰሞኑን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት በመራዉ ህዝባዊ ንቅናቄ „የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት“ አረጋግጧል:: ይህንን የቆራጥነት ጅማሮ ፓርቲዉ አመራር በመስጠት ህዝቡ ደግሞ ነጻነት በትግል እንጂ በልመና እንደማይገኝ አዉቆ ድጋፉን መቀጠል አለበት:: እኛ ከሀገርና ከህዝብ ርቀን የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን የገንዘብና የድፕሎማሲ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸዉ መቆማችንን የምናረጋግጥበት ወቅት ቢኖር አሁን ነዉ ::
ከሃያ ሁለት ዓመት ተሞክሮአችን እንደምንረዳዉ ሥርዓቱም ሆነ መንግሥት እንደ ሸክላ ላይጠገን የነከተ፤ እንደ ደረቅ እንጨት ላይታረቅ የገረረ መሆኑን ተገንዝበን ይህንን ሥርአት ከማስወገድ በቀር ሌላ አማራጭ እንደለለ መገንዘብ ይኖርብናል:: ይህ በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቅ መሆኑን ጠንቅቆ የሚያዉቅ ወንጀለኛ መንግሥት ያለ የለለ ሀይሉን ተጠቅሞ በሀገር፣ በህዝብና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል እያንዳንዳችን ከፍርሀትና መደናገጥ ነጻ ሆነን በዘዴ ትግሉን መቀጠል ይኖርብናል::
በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት፣ የደህንነትና በሆዱ ተገዝቶ ወገኑን ለሚያስፈጅ የወያኔ ካድሬዎች በሙሉ ለጥፋት አገልግሎታችሁ የሚከፈለዉ ገንዘብ መከራና ስቃዩን ከምታበሉትና ለሞት ከምትዳርጉት ደሀ ዜጋ የሚመዘበር መሆኑን ተገንዝባችሁ ሰልፋችሁን ከህዝብ ጋር እንድታደርጉ ጥሪአችንን እናቀርብላችኋለን:: ከገንዘብ በላቀ ደግሞ ይህ አሸባሪ መንግሥት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ሃይል አባላት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ህዝብ እንዳልተፈጠራችሁ የባእድ ቅጥረኛ ሰራዊት ቆጥሮ ከትዉልድ ቄያችሁ ዉጭ የሰሜኑን ተወላጅ ወደ ደቡብ፤ የምሥራቁን ወደ ምዕራብ፤ የደቡቡን ወደ ሰሜን እያዘመተህ በቋንቋ እንኳን ተግባብተህ የህዝቡን በደል እንዳትረዳና እንዳትራራለት አድርጎ በዜጋህ ላይ የአውሬ ተግባር እንድትፈጽም እየተደረክ መሆኑን መዘንጋት የለብህም::
በተለይም የሀገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት በህገመንግሥቱ የተሰጠህ ሀላፊነት የሀገርን አንድነት፣ የህዝብ ደህንነት፣ ሀብትና ንብረቱን እንድታስጠብቅለት እንጂ የጥቂት የማፍያ ቡድኖች የቤት አሸከርና የወንጀል ፈጸሚያ መሣሪያቸዉ እንድትሆን አይደለም :: ስለሆነም ጊዜዉ ሳይረፍድብህ እጅህ በተጨማሪ
የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ እየተካሄደ ያለዉን ግድያና የአፈና ዘመቻ አጥብቀን እንቃወማለን:: መንግሥት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱንም እናወግዛለን:: ንጹሃን ዜጎችን የሚያሸብሩ፣ ህገወጥ እርምጃ እንዲወስዱና እንዲገደሉ ትእዛ ሰጪዎች፣ ትእዛዝ አስፈጻሚና ፈጻሚዎች ለፍርድ መቅረባቸዉ የማይቀር ሀቅ መሆኑን እንዲያቁት ይገባል:: ታዝዤና ተገድጄ ነዉ ብሎ ማምለጥም አይቻልም:: ስለሆነም በነጻነት ትግሉ ከተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅቶችና ከሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በመሰለፍ ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ ለማምጣት የሰላማዊ ትግሉ አካል መሆን የግድ ይላል:: ይህ ሕዝብ እየተገደለና እየሞተ ወያኔም እየገደለና እያገዳደለን ዝንተአለም አይኖርም:: ፈሪ ጨካኝ ነዉና በአሁኑ የወያኔ መንፈራገጥ ግራ ሳንጋባና ሳንደናገጥ በሥልት የተጀመረዉን ሰላማዊ ትግል አቀናጅተን መቀጠል ይኖርብናል:: የድጋፍ ድርጅታችን የወያኔ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ የሲቪክ ማህበራትን፣ ነጻ ሚዲያዎችንና የህወሀትን ተንኮልና ደባ የሚያጋልጡ ሀቀኛ ዜጎችን ለማፈን ያወጣዉን ጸረ ሙስና አዋጅ በመቃወም የአንድነት ፓርቲ የጀመረዉን ህዝባዊ ንቅናቄ ሙሉበሙሉ እንደግፋለን ለተግባራዊነቱም የድርሻችንን በመወጣት ላይ እንገኛለን።
ዉሸትና ቅጥፈት የማይታክተዉ የወያኔ እህአዴግ መንግሥት ሰሞኑን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት“ በሚል መርህ የጀመረዉ ህዝባዊ ንቅናቄ አስደንግጦት በድርጅቱ ላይ እያካሄደ ያለዉን የዉሸት ፕሮፓጋንዳ አጥብቀን እናወግዛለን። በዚሁ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ የጀመረዉ ህዝባዊ ንቅናቄ እዉን እንዲሆን ተፈላጊዉን ድጋፍ በማበርከት የድጋፍ ማኅበራችን ከጎኑ መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን።
በማጠቃለያም በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ለረጅም ጊዜ የኖረዉን አንድነትና የደም ትስስር ለመናድና ትርምስ ለመፍጠር የወያኔ መንግሥት ሰሞኑን እያሰራጨ ያለዉን የበሬ ወለደ ቅጥፍት በአገር ውስጥም ሆነ በዉጭ የምንኖር አገር ወዳድ እትዮጵያዉያን ማጋለጥና መዋጋት ይኖርብናል።
ነጻነት ያለትግልና መስዋዕትነት አይገኝም
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተከብሮ ለዘለአለም ትኑር
አንድነት ደጋፊ ማኅበር በሙኒክ Hypo Vereinsbank, Konto:104532187, BLZ:70020270 , Verwendungszweck :Pro Ethiopia Tele:-
No comments:
Post a Comment