Ethiopian National Transitional Council
P.O.Box 9929
Alexandria, VA 22304
Tel: 1-571-335-4637
Tel: +44-7958-487-420
Email: contact@etntc.org
Website: www.etntc.org
October 2, 2013
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን ትግል እንደግፋለን!
በአሁኑ ሰአት ሀገር ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ትግሉን በሙሉ ሀይል በመግፋት ላይ መሆናቸውን ሁላችንም
እይተከታተልን ነው። ወያኔ-ኢሃዴግም ያለ የሌለ ሀይሉን እየተጠቀመ ያቺ አይቀሬ የሆነቸውን ቀን ለማዘግየትና የስልጣን
እድሜውን ለማራዘም አፈናውን፤ ግድያውንና እስሩን በስፋት ተያይዞታል።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ከሳምንት በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ እንዲሰናከል አባላቶችን በማሰርና
በመደብደብ፤ መንገዶች በመዝጋትና ሰልፈኛውን በማዋከብ ሲያደርግ የነበረውን ድርጊት በተመሳሳይ በአንድነት ፓርቲና
በ33ቱ ፓርቲዎች ላይ ባሳለፍንው ሳምንት ዸግሞታል። ይህ ድርጊት በወያኔ የሚሽከረከረው የአምባገነኑ ስርአት በ99.6%
ሕዝብ መርጦኛል ያለውን አሰልቺ ፕሮፖጋንዳው የተጋለጠበት፤ መረጠኝ የሚለውንም ህዝብ ምን ያህል እንደሚፈራ
ያሳየበትና የወያኔ ስርአት ፍጹም የአፓርታይድ አገዛዝ መሆኑን ለኢትዮጵያኖችና ለአለም አቀፍ ህብረተሰቡ ግልድ ባለ መልኩ
ያስመሰከረበት ድርጊት ነው። በመነሻነት ድምጻችን ይሰማና የሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነቃቃና በድፍረት
ለመብቱ እንዲነሳ ያሳዩት ፈጣንና ቆራጥ አመራር በተከታታይ ለተደረጉ እንቅስቃሴዎች መሰረት በመሆናቸው ልናወድሳቸው
ይገባል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ለነዚህ ቆራጥ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይም ለሰማያዊ ፓርቲና የአንድነት ድርጅት
አመራርና አባላቶች፤ እንዲሁም በየእስር ቤት ተወርውረው ለሚጊኙት የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ደራሽ ጀግኖች የድርጅት
መሪዎችና ጋዜጠኞች፤ ያለንን ከፍተኛ አድናቆት ከመግለጽ ባሻገር፤ ይህንን ግፈኛ ስርአት በህዝባዊ አመጽ መታገልና ማስወገድ
የድርጅታችን መርህ ከመሆኑ አኳያ ሙሉ ድጋፋችንን የምንሰጥ መሆኑን እናረጋግጣለን። በአለም አቀፍ ህበረተሰቡ ዘንድ
የህሊና እስረኞች መሆናቸው የተረጋጋጠላቸውና የተለያየ ሽልማት በማግኘት ላይ ያሉትን ብርቅዬ ወገኖቻችንን አወድሳችኋል
በሚል ድንቁርናና እብሪት በተሞላበት ሁኔታ፤ በወያኔ ሳንባ የሚተነፍሱት አፈቀላጤ አቶ ሽመልስ ከማል የሰጡትን አይን
ያወጣ ማስፈራራት እናወግዛለን።
በተለያዩ አቅጣጫዎች እየታዩ ያሉ መነቃቃትና የነጻነት ትግሎች ወደ ህዝባዊ ማእበል ሲለወጡ የወያኔ/ ኢሕአድግ ስርአት
የማብረድም ሆነ የመጨፍለቅ አቅም እንደማይኖረው እራሱም ጠንቅቆ ያውቀዋል ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ከስርአቱ
ውድቀት በኋላ ስርአቱን የሚተካ ሃይል ቅድመ ዝግጅት፤ እቅድና ስምምነት ባልተደርገበት ሽግግር አሁን በግብጽ በሶርያና
በሌሎች የአለም ሀገራት የምናየው ችግር ውስጥ እንዳትገባ፤ አገርና ህዝቡ ለከፍተኛ አደጋና ቀውስ እንዳይጋለጥ፤ ድርጅታችን
ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደት ላይ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል። ይህንን በተመለከተ ባለፈው ጁላይ ወር ላይ
ከተለያዩ ድርጅቶች፤ የሀይማኖት ተቋማት፤ ምሁራንና ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት የምክክር ጉባኤ አካሂዶ የሽግግር
ሂደት ቅድመ ዝግጅት ሂደት እንዲጠናከር የሚያግዝ ኮሚቴ አቋቁሟል። ቀጣይ እንቅስቃሴዎችና እርምጃዎችን አስመልክቶ
ተከታታይ መግለጫዎች የምናወጣ መሆኑን እየገለጽን የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ወገናችን አደጋውን በመገንዘብና ተሳትፎ
በማድረግ በጋራ በአገራችንን አስተማማኝ ለውጥ እንድናመጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የምናደርገው ዕንቅስቃሴ ህዝብን
መሰረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ በመሆኑ ስርአቱን ስታገለግሉ የነበራችሁና የከዳችሁ ሽግግር ምክር ቤቱን በመቀላቀል
ታሪካችሁን እንድታድሱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ለዘላቂና አስተማማኝ ለውጥ እንሳተፍ እንደራጅ!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር
No comments:
Post a Comment