Wednesday, September 4, 2013

Print Friendly Version of this pagePrint Get a PDF version of this webpagePDF የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት እና ዴሞክራሲ ግብረሐይል በስዊትዘርላንድ

የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት እና ዴሞክራሲ ግብረሐይል በስዊትዘርላንድ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እና ዴሞክራሲ ግብረሃይል በስዊትዘርላንድ በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለመወያየት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ኦክቶበር 12 . 2013 . ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በዙሪክ ከተማ ማዘጋጀቱን ያበስራል።Ethiopian Human Right & Democracy Task Force in Switzerland
በእለቱ ንግግር የሚያደርጉ ተጋባዥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የሚሳተፉ ሲሆን እርስዎም በዚሁ እለት በስብሰባው ላይ በመሳተፍ በሀገርዎ ጉዳይ ላይ እንዲመክሩ ተጋብዘዋል። የውይይቱ ርእስ ኢትዮጵያ ዛሬ የሚል ሲሆን በውይይቱ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች ይዳሰሳሉ፤ እንዲሁም በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ በግፍና በገፍ በመሰደድ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ከሞት እና ከህይወት ጋር ግብግብ ስለተያያዙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ይወያያል መፍትሄም ያመላክታል።
 እርስዎም በስብሰባው ለመሳተፍ ቀጠሮዎን ከኛ ጋር ያድርጉ
ቀን   – 2.10.2013  (ኦክቶበር 12 , 2013)
ሰዓትበፈረንጆች አቆጣጠር ከጠዋቱ 10.00 ጀምሮ
አድራሻኪርች ጌማይንዴ Kirchgemeinde Aussersihl, Stauffacherstrasse 8, 8004 Zürich
ወደ አዳራሹ ለመምጣት ከዋናው የዙሪክ ባቡር ጣቢያ ትራም 14 ቁጥርን በመያዝ 3ኛው ፌርማታ ስታፋውከር ሲወርዱ ያገኙታል( From Haupt Bahnhof ..Tram 14 and tram 3 stop Stauffacher)
ለተጨማሪ መረጃ 076 500 6288 ፤ 076 261 2995 ፤ 076 394 0027 ፤076 446 7862 ፤076 209 5118 ፤076 249 9428 ይደውሉ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

No comments: