ቦስተን መስከረም 17/2007 (ሴፕቴምበር 27፣ 2014 ዓ.ም) የደመራ በዓል በካምብሪድጅ ከተማ 808 Memorial Dr. አጠገብ በሚገኘው ፓርክ በቦስተን እና አካባቢዋ ነዋሪ በሆኑ የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕምናን ዘንድ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተከበረ።
በበዓሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን አባቶች፤ ዲያቆናት እና መዘምራን በቦታው በመገኘት በዓሉን በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ስርዓት አክብረዋል።
በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል ላይ የቤተ ክርስቲያኖቹ አባቶች ስለ በዓሉ ታላቅነት እና የበዓሉን ታሪካዊ እና ሐይማኖታዊ አመጣጥ በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን፤ መዘምራኖችም በዓሉን የተመለከቱ መንፈሳዊ መዝሙሮችን በመዘመር ለበዓሉ ትልቅ ድምቀት ሰጥተውታል።
የቦስተን እና አካባቢዋ ምዕመናን በዓሉን አስመልክቶ የጧፍ ማብራት ስነ ስርዓት በማድረግ እና መንፈሳዊ ዜማዎችን ከመዘምራን ጋር በማዜም ተጠናቋል። (ፎቶግራፎችን ይዘናል ይመልከቱ)
በዚሁ አጋጣሚ የአቡጊዳ ዝግጅት ከፍልም ለመላው የቦስተን እና አካባቢዋ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎ፤ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች “እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደርሳችሁ” እያለ መልካም ምኞቱን እየገለጸ፤ ባለፈው ዓመት የመስቀል በዓል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ባህልና ትምህርት ድርጅት /ዩኔስኮ/ መመዝገቡንም በዚሁ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን።
No comments:
Post a Comment