Thursday, September 18, 2014

በጥቅምና በፖለቲካ እንጭጭነት የታወረ ጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ አደጋ አለው !!! መፍትሔውስ? – ምንሊክ ሳልሳዊ



- ያልበሰሉ ካድሬዎች ድክመቶቻቸውን ይዘው ሃገሪቱን የማትወጣበት ከባድ አደጋ ውስጥ ከተዋታል።
- የኢትዮጵያ ህዝቦች የጋራ መስዋትነት በመክፈል ታሪካዊ ድሎችን የምንቀዳጅበት ጊዜ ነው።
- ወሳኙ የትግል ጊዜ እና የወያኔ በር በርግደን ነጻነታችንን የምናረጋግጥበት ቁልፉ በጃችን ነው።
- አንዱ አንዱን ሲኮረኩም የወያኔን እድሜ እያስረዘምን በህዝብ ሰቆቃ እየቀለድን መሆኑን አንዘንጋ።
- ግለሰቦች ላይ በማተኮር የህዝቦችን የነጻነት እና የለውጥ ፍላጎት በትግል ሽፋን ማደፍረስ ይቁም።
ከሁለቱም ወገናቸው የተሳሉ ስሜታዊ እና በጥቅም የታወሩ የፖለቲካው ብስለቱ ያሌላቸው እንደመሰላቸው የሚጓዙ እና ላም ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም የሚዳዳቸው የተጋረዱ እውር ካድሬዎች (ጩቤዎች) ሃገሪቱን እና ያለውን እውነታ በማድበስበስ ህዝብን እያጭበረበሩ በመኖር ላይ መሆናቸውን ስንመለከት አገራችን ከተዘፈቀችበት አደጋ ወደሌላ የማትወጣበት ከባድ አደጋ እያመራች መሆኑ መገንዘብ አያዳግትም::
በገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በኩል የምናየው ያልበሰሉ ካድሬዎች መበራከት አገሪቷን አደጋ ውስጥ እየከተታት መሆኑን ሲታወቅ በስልጣናቸው መከታ በመሆን እና በታገሉት የመስዋትነት ልክ ትእቢት በመሞላት ከመንግስት እና ከህግ በላይ የሚያላዝኑ ባለስልጣናትን መሸሸጊአ በማድረግ የጀመሩት የጥቅም ዘረፋ እንዳይጓደልባቸው በጭፍን የፓርቲ ካድሬነት የሚገሰግሱ ሳያውቁት የሆዳቸውን መሙላት ተከትለው የሚያጨበጭቡ በርካታ ዜጎችን ሃይ የሚል መንግስት መጥፋቱ አሁንም በድጋሚ ያለንበት የአደጋ ቀጠና እየሰፋ መምጣቱን ያመለክታል::
ልማትን ተገን አድርገው ሃገርን ወደ ገደል የከተቱ የገዢው ፓርቲ አባላት የአመራር እጦት እና የአስተዳደር ብልሹነት በገዢዎቹ ውስጥ መከሰቱን እና የጭፍንነት በሽታ መስፋፋቱን የማይካድ ገሃዳዊ ሃቅ ነው::በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሂደት በሚዛናዊ መልክ መመልከት ያቃታቸው የህዝብን ብሶት እና ድምጽ መስማት የተሳናቸው አመራሮች/ባለስልጣናት የፈጠሩት የካድሬዎች ትንንሽ ቡድን ሃገሪቱዋን ወደማትወጣበት አዘቅት ስለከተታት ማጣፊአው አጥሯቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ላይ ይገኛሉ::እነዚህ ፓርቲያቸውን እና መንግስታቸውን ገፈታትለው ህዝብን አስቀድመው ወደ ጉድጓድ የጨመሩትን የሃገር ደህንነት እና እድገት ማሞካሸት እና ማድነቅ ብቻ የሚመስላቸው ነገን የማይመለከቱ አካላት የሚቆጣጠራቸው በመጥፋቱ የተቦረቦረች ሃገርን ወደ ዝግምተኛ ባዶነት ቀይረዋታል::
ተቆጣጣሪ በማጣታቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከየፕሮጀክቱ በመዝረፍ የራሳቸውን የዘራፊ ማፊያ ቡድን በመገንባት ህዝብን እያስለቀሱ በአገሪቱ ስንት መንግስት እና ስንት ህግ አለ እስከሚባል ድረስ ትዝብት እና ጥላቸ ውስጥ የወደቁ ካድሬዎች ድክመቶቻቸውን ይዘው ሃገሪቱን ካለችበት የፈንጂ ወረዳ ወደባሰ የፈንጂ ወርዳ ከተዋታል ዛሬ ነገ ሳይባል የጋራ ትግል ሊታሰብበት ይገባል::
መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው ፤ በፖለቲካ ተንኮል በሙስና የተቀፈደዱ ባለስልጣናትን እንደ አምላካቸው አድርገው የሚያዩት እና በፖለቲካ ሴራ የተተመጠሙ የፖለቲካ መሪዎችን እንደ ነብስ አባታቸው የሚያመልኩ የፖለቲካ እንጭጮች እና ጭፍኖችን ያቀፈውን ስር አት ይሁን ወገን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰሰ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዜግነት ድርሻችንን በመወጣት ወደ ትግሉ ጎራ በመትመም የተገጨውን የትግል ቁልፍ ይዘን የወያኔን በሮች በርግደን በመግባት ታሪካዊ ድሎችን መቀዳጀት የራሳችን ድርሻ ሲሆን ነጻነታችንን ራስአችን ካላረጋገጥን ማም በስጦታ መልክ እቤታችን እንደማያመጣልን ማወቅ ግዴታችን ነው። በደሉ ከፀና፣ አፈናው ግድያው እስራቱ ግፉ ከቀጠለ፣ አንድነቱ ፍቅሩ መተሳሰቡና መተባበሩ ተሸርሽሮ ከተናደ፤ሁሉም ለነፃነቱ መታገል የሚናፍቅበት ነገር ግን የሚያዳግትበት ጊዜ መምጣቱ ስለማይቀር፤ይህ ቀን ሳይመጣ፤ እኛም ከምድረገጽ ሳንጠፈ፤እድሉን ተጠቅመን ሀይላችንን አስተባብረን ሁላችንም ነፃ ልንወጣ ይገባናል!!!
እርስ በእርስ ከመኮራኮም እና በሴራ ፖለቲካ ትጀቡነን አንዱ አንዱ እየወነጀለ የትግልን ስልት እና መንገዱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በዝርጠጣ እና በወሬ ድል እንደማይመጣ ለመናገር እድፍራለሁ። ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በጋራ በፍቅር በመከባበር በአንድነት በመቻቻል እጅ ለ እጅ ተያይዘን አምባገነንነትን በማደባየት የተዘጉትን በሮች በመበርገድ ራሳችንን ሕዝቦች መሆናችንን በማረጋገጥ የድል ስኬታንን እና ብስራታችንን ማብሰር አለብን።አንድነት ሃይል ነው!!!  sourse abogda

No comments: