Tuesday, September 2, 2014

ስልጠናው በማህበረ ቅዱሳን ላይም አነጣጥሯል * ‹‹በፓትሪያሪክ ምርጫ ላይ እጃቸውን ያስቡት ተቃዋሚዎች ናቸው››


  • 751
     
    Share
• ‹‹በፓትሪያሪክ ምርጫ ላይ እጃቸውን ያስቡት ተቃዋሚዎች ናቸው››
• ‹‹ገዳማት አልታረሱም›› ሰነዱ
ለኢህአዴግ ጽ/ቤትና በትምህርት ሚኒስትር ተዘጋጅቶ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ማህበረ ቅዱሳን ላይ ማነጣጠሩን ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት ማህበሩ የኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት የማይወክልና አክራሪ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ለስልጠና የተዘጋጀው ሰነድም በክርስትና ኃይማኖት ሽፋን እንደሚሰሩ ያትታል፡፡
ሰነዱ እነዚህ ‹‹አክራዎች›› ያነሱታል ያላቸው ጥያቄዎች በተለይም መንግስት በሲኖዶሱ ጣልቃ ይገባል፣ በክርስትና አማኞች ላይ ጫና ይደረጋል፣ እንዲሁም ገዳማት እየታረሱ ነው ብለው አንስተዋቸዋል የሚላቸው ጥያቄዎች ሀሰት መሆናቸውን ይዘረዝራል፡፡
ሰነዱ በገጽ 39 ‹‹መንግስት በክርስትና እምነት አባቶች ምርጫ ላይ እጁን አስገብቷል የሚባለው ፈጽሞ መሰረተ ቢስ ነው፡፡ በኃይማኖት አባቶች ምርጫ በቀጥታ እጃቸውን አስገብተው ለራሳቸው የሚመች ፓትሪያርክ ለማስመደብ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አፍራሽ ተቃዋዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡›› ሲል ይገልጻል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ገጽ 40 ላይ ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እጅ ያሉ ገዳማት ያሉባቸው መሬቶች ታረሱ የሚባለው በተለይ ደግሞ ከወልቃት ስኳር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሳው የሀሰት ወሬ›› መሆኑን ሰነዱ ይገልጻል፡፡
ሰነዱን እንደሚከተለው አያይዘነዋል!
mahbere kidusan 1
mahbere kidusan 2
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ
-- Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.--

No comments: