Friday, September 5, 2014

ኢህአዴግ የአዲስ አበባን አባሎቹንና ህዝቡን ለማሳመን እየጣረ ነው


ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በተለያዩ ሊጎች ወይም ፎረሞች ለሰበሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና
ባልጠበቀው አቅጣጫ እየሄደበት መሆኑን ተከትሎ ሰዎችን ከመከፋፈል ጀምሮ እስከ ማባረር መድረሱን ምንጮች ገልጹ።
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የመሰብሰቢያ ቦታዎች በሚደረጉት ስልጠናዎች ላይ ለገዢው ፓርቲ ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን የሚያቀርቡ ወጣቶች እና
የፖለቲካ ንቃት አላቸው የሚባሉ ነዋሪዎች ፣ ከቀሪ ተሰብሳቢዎች እንዲለዩ ሲደረግ አንዳንዶች ደግሞ ከእንግዲህ ወደ ስልጠናው እንዳትመጡ ተብለው ተባረዋል።
በመላ አገሪቱ የተፈጠረው የስኳር እና ዘይት እጥረት፣ የኑሮ ውድነት፣ የሃይማኖት ጉዳይ በቀዳሚነት ተሰብሳቢዎቹ ሲያነሱዋቸው ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል ይገኛሉ።
በአጼ ሚኒሊክ ዘመን ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን በስብሰባው ላይ የተገኙት እናቶች ሳይቀር እንዲማሩ መደረጉን ስብሰባውን የተካፈሉ ሰዎች ገልጸዋል።
ኢሳት ያነጋገራቸው አንዳንድ ነዋሪዎች የሌግ አባል ናችሁ ተብለው መመረጣቸውን ለኢሳት ተናግረዋል።esat  radio

No comments: