ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ክ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ኤርትራ ተሰደዋል::
ባሳለፍነው ሃምሌ ወር ክ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ኤርትራ ተሰደዋል::
ከ5500 በላይ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸን እና ቤተሰቦቻቸውን አስከትለው ድንበር አቋርጠው ወደ ጎረቤት ኤርትራ መግባታቸውን አስመራ የሚገኙ ምንጮች ለDurame በስልክ አስታውቀዋል::
በአማካኝ በየቀኑ 180 የሚሆኑ እድሜያቸው ከ30 አመት በታች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ኤርትራ ይገባሉ:: እንደምንጮቹ ዘገባ ከሆነ አብዛኛዎቹ ስደተኞች የሚመጡት ከምእራብ እና ደቡብ ትግራይ ሲሆን እንዲሁም ከጎንደር ናቸው::
በመቀሌ የኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረው የ23 አመቱ ግርማይ ሃብቴ እንዳለው የወያኔ መንግስት ህዝቡን እየጨቆነ እንደሆነ እና ልንታገልው ይገባል ሲል ተናግሯል:: ሁሉም ነገር አለኝ.....በኢትዮጵያ ግን ተስፋዬ የጨለመ ነው:: ኢትዮጵያ ትልቅ እስር ቤት ሆናብኝ ነበር ብሏል::በየአመቱ ወደ 350.00ኦ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሃገሪቷን ለቀው ይሰደዳሉ :: በአፍሪካ ከፍተኛ የስደተኞች ላኪ አገር ኢትዮጵያ ሆናለች::
source Minilik Salsawi
No comments:
Post a Comment