Friday, August 30, 2013

ሽብርተኛው ወያኔ/ኢህአደግ በሀይማኖቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደረገውን እኩይ ሴራ እናወግዛለን!

Ethiopian National Transitional Council
P.O.Box 9929
Alexandria, VA 22304
Tel: 1-571-335-4637
Tel: +44-7958-487-420
Email: contact@etntc.org
Website: www.etntc.org
ነሐሴ 23 2005 23 2005
ሽብርተኛው ወያኔ/ኢህአደግ በሀይማኖቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደረገውን እኩይ ሴራ
እናወግዛለን!
ባሳለፍናቸው ወራት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች እየደረሱባቸው ያሉ አፈናዎችንና እስሮችን በመቋቋም ህዝቡ
ለመብቱ እንዲቆም እያደረጉ ያሉትን የማነቃቃትና የማንቀሳቀስ ስራ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ሳይገድሉ
እየተገደሉ ያለመታከት ከአንድ አመት በላይ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄያቸው ምላሽ በመሻት ድምዳቸውን
በማሰማታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት ያለውን አድናቆትና አክብሮት ይገልጻል። እንቅስቃሴዎቹም
የሽግግር ምክርቤት ከሚከተለው የህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ጋር ተዛማጅ በመሆናቸው ሙሉ ድጋፋችንን መግለጽ
እንወዳለን ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከየአቅጣጫው የሚያደርግበት ግፊት ያስበረገገው የወያኔ-ኢህአዴግ ስርአት፤ በስፋት ሲሰራበት የኖረውን
አንዱን ሀይማኖት ከሌላው የማጋጨት ጥረት በአሁኑ ሰአት ወደ ከፋና የመጨረሻ ደረጃ ላይ አድርሶታል። በነሓሴ 26 ቀን
2005 ዓ.ም. ህዝቡን በተለይም የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችንን ባለው መዋቅርና በተለያዩ መንገዶች በማስፈራራትና
በማስገደድ አደባባይ ወጥተው በሰላም ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡትን የሙስሊም ወገኖቻችንን እንዲያወግዙ ማቀዱ እጅግ
አሳዝኖናል። በተለይም ይህ ሰልፍ የተጠራው ሰማያዊ ፓርቲ ከሳምንታት በፊት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በጠራው ቀንና
ቦታ መደርጉ፤ የወያኔ አላማ ምን እንደሆነ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም።
እኩይ ተግባሩን በሚያስፈጽሙለት ካድሬዎቹ አማካይነት በሰልፉ ላይ የተቀነባበረና አላስፈላጊ ግጭቶችን በማነሳሳት
ተቃዋሚዎችን በማሸበርና በማፈን ማለቂያ የሌለው የወያኔ የተለመደው አሰልቺ ድራማ ሲሆን፤ ዋና አላማውም በሙስሊም
ወገኖቻችን ላይ በአሩሲ ኮፈሌ ያደረገውን አረመነያዊ ጭፍጨፋ፤ ባአዲስ አበባ የተደረገውን ድብደባና አስር፤ በተለያዩ
የተቃወሚ ድርጅት አባላት ላይ እየተደረገ ያለውን እስርና እንግልት የህግ ሽፋን በመስጠት ህዝባዊ ድጋፍ እንዳለው
ለኢትዮጵያ ህዛብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰቡ ለማሳየት የሚያደርገው መፍጨርጨር ነው።
ታድያ ሽብርተኛው ማነው? ጥያቄውን በሰላም የሚያቀርብ ህዝብ ወይስ ለሺህ ዘመናት ተፋቅሮና ተከባብሮ የኖረን ህዝብ
ለማጫረስ የጦር ሜዳውን የሚያመቻች የሽፍቶች ስብስብ?
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፤ ምንም እንኳን ወያኔ ይህ ሴራ ይሳካለታል ብለን ባናስብም፤ የሁኔታውን መሰሪነት
ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ፍጹም አረመኔ ቡድን እየሄደበት ያለውን አደጋ በማውገዝና ስርአቱን ማስወገድ አማራጭ
የሌለው መፍትሄ መሆኑን በመገንዘብ ከጥቃቅን ጥቅማ ጥቅሞችና የብዥታ ግርዶሽ በመውጣት እያንዳንዳችን ይበቃል
በሚል መርህ ታሪካዊ ድርሻችንን እንወጣ።
ስርአቱን ለማስወገድ እንደራጅ!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር

No comments: