Thursday, August 15, 2013

ከቁጫ እስከ ኦሮሞ - ማንነትና የማንነት ፖሎቲካ እንደምታና መዘዞቹ ዩሱፍ ያሲን


የአሜሪካ ድምፅና የዶቼቬሌ አማርኛ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የቁጫ ሕዝብ የራሱን ማንነት የመወሰን
ጉዳይ አስመልክቶ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎች መታሰራቸው ዜና በቅርቡ ተዘግቦ ሰምተናል። 40
የሚሆኑ የአካባቢ ሽማገሌዎች እነዚህ የተሳሩ ሰዎችን ለማስፈታት አዲስ አባባ ድረሰ መምጣታቸውንም
ተዘግቧል። የቮይስ ኦፍ አሜሪካ ባልደረባ ጋዘጤኛ ሰሎሞን ክፍሌ ባመዛኙ በማንነት ዙርያና ሳቢያ
የተነሳውን ውዝግብ ርእሰ ጉዳይ ላይ የሽማገሌዎች ወኪል ከተባሉት ጋርም ቃለ ምልልስ
አስደምጦናል።
ቁጫ በደበቡ ኦሞ በጋሞጎፋ ዞን በደቡብ በዲታና ዴራማሎ፣ ከደቡብ-ምዕራብ በዛላ፣በምዕራብ
ከደምባ-ፋ፣ በሰሜን-ምዕራብ በዳውሮ ዞንና ከሰሜን ከወላይታ ዞን የምትዋሰን አንዲት የደቡብ
ኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ወረዳ ናት። ዋና ከተማውም ሰላምበር ትባላለች፣ ይህንን
የዘገበው ዊኪፒዲያ ነው።
ቃል-ምልልስ የተደረጉት የቁጫ ሕዝብ ወኪል ”የቁጫ ሕዝብ ጋሞ አይደለም፣የቁጫ ሕዝብ ወላይታ
አይደለም፣ የቁጫ ሕዝብ ቁጫ ነው ፣ቋንቋውም ቁጨኛ ነው” ነበር ፍርጠም ብለው
ያስረገጡት።በቅርቡ በሶማሌ ክልልም በመሥራቅና በምዕራብ አሚ የሰፈረው የዱቤ ሕዝብ ወኪልም
እንዲሁ "እኛ የዱቤ ብሔረሰብ ሶማሌ አይደለንም፣ ራሳችን የቻልን ሕዝብ" ነን ብሎዋል።የእነሱም
ወኪልም አሁንም በዚያው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ላይ ቀርበው ነው ይህንኑ ያረጋገጡት።ከዚህ
በፊትም የሥልጤ ብሔረሰብ ”ሥልጤ፣ ሥልጤ እንጂ ጉራጌ አይደለም” የሚል የማንነት ጥያቄ
አነስቷል ተብሎ ሪፈረንደም ተፈቅዶለት አብላጫው ”ሥልጤ፣ሥልጤ እንጂ ጉራጌ አይደልም”
ድምዳሚ በድምፁ አፅድቆ እስከዚያ ድረስ በቀሪዎቹ ኢትዮጵያውያን ዘንዳ በዘልማድ ከሚታወቅበት
"ጉራጌ" መታወቂያ መለያ የራሱን ማንነት መርጦ ፀደቀለት።ከዚያ በፊት በተለያዩ የኢትዮጵያ
አካባቢዎች አልፎ አልፎ በማንነት ዙሪያ የተነሱ ወይም ለማዕከላዊ መንግሥት ጥያቄ የቀረበበት በርካታ
በማንነት ዙሪያና ሳቢያ የተነሱ ጉዳዮች እናውቃለን።ይህንኑ ማንነት ማጠንጠኛ አድርጎ በወረዳ፣በዞንና
አልፎ ተርፎ በክልሎች መካከል የአከላለል ውዝግቦች ሲያናታርኩና ሲያወዛግቡ ተመልክተናል።አሁንም
አልፎ ተርፎ ስያገዳድሉም ሰምተናል።
የአሜሪካ ድምፅ የቁጫም ሆነ የዱቤ የማንነት ጥያቄ ዜና እምብዛም የብዙዎቻችንን ትኩረት
አልሳበም።የሥልጤ ውሳኔ-ሕዝም ሆነ ውጤቱ ክርክር አላቀጣጠለም ኢትዮጵያውያኑ ዘንድ።ባንፃሩ
ወጣቱ የፖሎቲካ አናሊስት ጆውሃር መሃመድ ከሁለት ሌሎች የኦሮሞ ብሔርተኛ አክቲቪስቶች ጋር
በአለጀዚራም ሰለ ኦሮሞ ማንነት ጥያቄ ዙሪያ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ብዙ አቧራ
አስነስቷል።አነታርኳል።አናቁሯል ማለት ይቀላል።
አሁንም በቅርቡ በሚኖሶታ በተደረገው የኦሮሞ የሙስሊም ኮሚኒቲ ስብስብ ላይ ይህንኑ ወጣት ምሁር
የኦሮሞ ሕዝብ የመብት ትግል ከኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ትግል ጋር አስተሳስሮ በማቆላለፉ አባባሉ
አንዳንዶቹ እንዳሉት ለኦሮሞ ብሔርተኛ ትግል "መጥለፍ" በመመኮሩ የብዙዎችን ትኩረት
ስቧዋል።አሁንም ብዙ አቧራ አስነስቷል።ብዙ ውይይትም አቀጣጥሎዋል። ባጭሩ ፣ በብዙ የዲያስፖራ
ኢትዮጵያውያን ማሕበራዊ መገናኛ ኔትዎርኮች ዘንድ ዓቢይ መነጋገሪያ ርእሰና ሰሞነኛ አጄንዳ ሆኖ

No comments: