- አደም ጀማል
- ሌንጮ ጂልቻ
- ሀቢብ ዋቤ
- ጋቻኖ ቱሴ
- ሙሀመድ ደበል ኡሴ
- ጀማል/አርሾ አርሲ/
- ሙሀመድ ኢደኦ
- አማን ቡሊ
- ሙሀመድ ሀሰን
- ረሺድ ቡርቃ
- አቡሽ ኢብራሂም
- ማሙሽ ኢብራሂም እና
- ቱኬ በሶ
የተባሉትን ወጣቶች መንግስት ያለ አንዳች ርህራሄ በጭካኔ ገድሏቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ለመጨረስ የከፈተው ዘመቻ አካል በመሆኑ የወጣቶች ንቅናቄ (ቄሮ) ድርጊቱን በአፅንኦት ያወግዘዋል፡፡
የወያኔ መንግስት እየወሰደ ያለው የግድያ እርምጃ የአገዛዝ ዘመኑ እያከተመለት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በምእራብ ወለጋ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ የወያኔ የደህንነት ሀይሎች ኢፋ ይገዙ የተባለውን ወጣት የኦነግ አባል ነህ በማለት የገደለው ሲሆን በሌሎች 9 ወጣቶች ላይ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት እንደሚገደሉ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎባቸዋል፡፡ እነሱም፡-
- ወጣት ደሱ አለማየሁ
- ወጣት ፍቃዱ ቱፋ
- ወጣት ወንድሙ ጉዳ
- ወጣት አራርሶ ቀጀላ
- ወጣት ገመቺስ በንቲ
- ወጣት ቢቂላ እስራኤል
- ወጣት ሁሴን መሀመድ
- ወጣት አባያ ባይሳ እና
- ወጣት ቶሎሳ አለማየሁ
የተባሉት ሲሆኑ በእነዚህ ወጣቶች ላይ የወያኔ መንግስት የግድያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት አስከፊ ድርጊቱን እየፈፀመባቸው ይገኛል፡፡ የወያኔ መንግስት እየፈፀመ ያለውን ግድያ፣ እስራት፣ ከትምህርት ገበታ ማፈናቀል እና ኢፍትሀዊ ውሳኔውን ለመጋፈጥ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ መነሳት እንዳለበት ለነፃነት የሚታገለው ወጣት ሀይል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የወያኔ መንግስት ከመቼውም ጊዜ የከፋ ጫና በኦሮሞ ወጣቶች ላይ እያደረሰ መሆኑ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት መጎናፀፊያው ወቅት እየቀረበ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እጅ ለእጅ ተያይዞ መብቱን መጠየቅ ያለበት አሁን ነው፡፡ የወጣቶች ንቅናቄ(ቄሮ) የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን አስከፊ እርምጃ በማውገዝ ማንኛውንም መስዋእትነት ከፍሎ የህዝቡን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ ይገልፃል፡፡
ትግሉ ይቀጥላል!!! ድል ለኦሮሞ ህዝብ!!!
የወጣቶች ንቅናቄ(ቄሮ)
ነሀሴ/2013
No comments:
Post a Comment