Saturday, August 10, 2013

የመጀመሪያው በሳል ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ትግል

ከያሬድ አይቼህ – ኦገስት 9፥2013
ህወሃት ደደብ ነው። ምንም የማይገባው ፡ ገደብ የማያቅ ፡ ግርድፍ ባዕዳዊ ድርጅት ነው። በአስተሳሰቡ ባዕድ ፡ በስነምግባሩ ባዕድ ፡ በግብረገቡ ባዕድ። ይሄን የህገ-አራዊት ድርጅት ፊት ለፊት የገጠመው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄ ነው። የንቅናቄው ብስለት ፡ አርቆ አሳቢነት ፡ አገራዊነት እና ሰብዓዊነት ድንቅ ነው ፤ ድንቅ!
ከ18 ወራት በፊት አካባቢ የጀመረው የድምጻችን-ይሰማ ንቅናቄን በመጠኑ ግራ በመጋባት እና በተደባለቀ ስሜት ስከታተል ቆይቻለሁ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንኖር ሰዎች የአሜሪካንን ፊሪሃ-ኢስላም (islamophobia) ፕሮፓጋንዳ ሌት ተቀን ስለምንጋተው ፡ እኔም ፈሪሃ-ኢስላም ተጠናውቶኝ ነበር። “ለመሆኑ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም አሸባሪነትን ያስተናግዱ ይሆን?” የሚለው ጥያቄ በአይምሮዬ ጀርባ ሲያንዣብብ ቆይቷል።
- See more at: http://addisvoice.com/2013/08/%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%aa%e1%8b%ab%e1%8b%8d-%e1%89%a0%e1%88%b3%e1%88%8d-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9b%e1%8b%8a-%e1%89%b5/#sthash.UVExhAj1.dpuf

No comments: