Friday, August 16, 2013
ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ
የሰላማዊው ሰልፎ ዋና አላማ ሃገራችንን ኢትዮጵያ ለሐሃያ ሁለት አመታት በዘረኛውና ከፋፋዮ ወያኔ ገዢ መንግስት ያደረሰባትን የዘር ማጥፋት፣ ከትውልድ ቄያቸው በግዳጅ ማፈናቀል ፣የሐይማኖት ነጻነት አለመኖር ህዝቦቿም ወደ ማይወጡት ችግር ውስጥ በማስገባት ለስደትና ለመከራ በመዳረግ ከዛም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋና ግድያ እንዴሁም በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚያደርሰውን እስር፤ ድብደባ ፤ እንግልት በመቃወምና የኖርዌ መንግስት ከአምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ጋር የምታደርገውን ግኑኝነትና የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።
በፕሮግራሞ ላይም ከኖርዌይ ፖለቲከኞች የተለያዩ ፓርቲዎች ተጋበዥ ሲሆን ሓገራቸው በአሁን ሰአት የምርጫ ጊዜ ስለሆነ ጥቂቶቹ ሊገኙ ስላልቻሉ በቴሎፎን ድጋፋቸውን ገልጸዋል ከመሐከላቸውም ከቬንስትረ ፓርቲ ወኪላቸውን በመላክ በኢትዮጵያ መንግስት ያላቸውን ተቃውሞና ለሰላማዊ ሰልፈኛው ድጋፋቸውን በላኩት መልእክተኛ አስነብበዋል በመጨረሻም ከዲቬሎፕመት ፈንድ ተወካይ የመጣው ባለስልጣን አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ መልእክታችንን ተቀብለዋል።
በመዝጊያውም የተለያዩ መፈክሮች ከተሰሙ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ እንደ ሐገራችን መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኛውን በድብደባና የገባበት ገብቶ ለመያዝ በማሳዳድ ሳይሆን በዲሞክራሲ መብታችን የፈለግነውን ተናግረንና ተቃውመን በሰላም ተጠናቋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይም ከተሰሙት መፈክሮች በጥቂቱ,TPLF is evil, There is apartheid in Ethiopia, Don't remove indigenous people from their livelihood, We need freedom of religion., Regime change is needed in Ethiopia now, We need freedom of speech, ድምጻችን ይሰማ እኛ ሙስሊም ክሪስቲያን ኢትዮጵያኑች አንድ ነን አንለያይም , ሞት ለወያኔ በሚሉ መፈክሮች ያሸበረቀና ሌሎችንም መፈክሮች ያካተተ ነበር። ሰላማዊ ሰልፉም በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ kl 13; 00 ተጀምሮ በ 14፡30 ተጠናቋል ቸር ያሰማን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር
እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ
16.08.2013
No comments:
Post a Comment