Sunday, 04 August 2013 06:49
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በቅርቡ በወያኔ ላይ በከፈተው ድንገተኛ የማጥቃት እንቅስቃሴው 65 የሥርዓቱ ታማኝ ታጣቂ ሐይሎችን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው።
አርበኛው የጦርነት ፍልሚያውን ግብግብ ከወያኔው ታጣቂ ሃይሎች ጋር የተካፈለው በጎንደር ደባርቅ ወረዳ የሥፍራው ልዩ ስያሜ በደዊ በመባል በሚታወቀው ሥፍራ ላይ ነው።
ከአርበኛው ሐይል ጋር በዕለቱ በተጠቀሰው ሥፍራ ተገኝተው ውጊያውን የተካፈሉ የወያኔ ታጣቂ ሐይላት የፈጥኖ ደራሽ አባላት ሲሆኑ በአውደ-ውጊያው መጨረሻም 28 አባሎቻቸውን በሞት ያጡት የወያኔ ታጣቂዎች ተጨማሪ ሌሎች 37 የፈጥኖ ደራሽ አባሎቻቸውም ላይ ከፈተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
አርበኛው በደባርቅ የበድዊው ጦርነት 28 የወያኔ ፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎችን ግድሎ ተጨማሪ 37 ታጣቂዎችን ሊያቆስል የቻለው በጸና የሕዝባዊ ዓላማ ፅናት ፣ በሕብረተሰቡ ጠንካራ የድጋፍ መሰረት ላይ በመሆኑም በውጊያው ከቀላል እስክ ከባድ የሚባሉትን አያሌ ተተኳሽ የጦር መሳሪያዎችንም ከጠላት እጅ ማርኳል።
ጦርነቱ የተካሄደበት አካባቢ ክረምቱ እየጠነከረ የመጣ ሲሆን ይህን የአየር ለውጥ ክስተት ጫና ተቋቁመው ከአርበኛው ጋር መጋፈጥ ተስኗቸው ለሞትና ለቁስለኝነት በተዳረጉ የፈጥኖ ደራሽ ታጣቂዎች ብቃት ዙሪያም ሕዝቡ እየተሳለቀ ነው።
በአንፃሩም ሐምሌ 25-2005 ዓ.ም ዕለተ ሐሙስ አርበኛው የወቅቱን የአየር ፀባይ ለውጥ ተቋቁሞ የደባርቅ ወረዳ የበደዊን ቀበሌ ውጊያ በበላይነት ድል ማጠናቀቁ ውጤቱ ለሕዝቡ እንዳኮራቸውም በደባርቅ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment