Wednesday, June 19, 2013

ኢትዮጲያ የማን ናት?

June 13, 2013
Aden Mesfin, from Norway
ከኤደን መስፍን(ኖረዌይ)
እንደሚታወቀው በአንድ ሃገር የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ክንውኖች የቀን ተቀን ለውጥ ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ(አስተዋጾ) ጉልህ ሚና አለው፡፡ እንዲሁም በሂደትቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጉዳዮችም ይሁኑ ወይም በተቃራኒው የሚከሰት ተፈጥሯዊም ሆነ በመልካም አስተዳድር ችግር ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች ከህብረተሰብ  ጫንቃ ላይ አይወርድም፡፡ ይህ ስለሚታወቅ ሃላፊነት  የሚሰማቸው፣ ለሃገርና ለሕዝብ ታማኝ  የሆኑ፣ በሕዝብ  ይሁንታ ስልጣን የያዙ  መንግስታት ያላቸው ሃገሮች በየትኛውም ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ሕዝባቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ በማድረግ በቤሔራዊ ስሜት የታነፀ በሃገሩ ጉዳይ የማያመነታ ህብረተሰብ ይገነባሉ፡፡ የእንደኛ አይነቶቹ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር የሌላቸው አምባገነን መሪዎች ግን እንኳን የሃገርህ ጉዳይ ያገባሀል ብለው ሊያሳትፉት ቀርቶ የሕዝብን የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፈጥሮዊ መብቱን ገፈው ሃገሪቱን የቁም እስር ቤት አርገዋታል፡፡
በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊ የሆነ የመብት ጥሰትን የተቃወመ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ ሃገር ሲቸበቸብ ኢትዮጲያ የኢትዮጲያዊያን ነች ብለው የተቃወሙትን፣ የእምነት ነፃነታቸውን አናስነካም ብለው በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁና በሌላም ሃገራው ጉዳይ ላይ እንደ ዜጋ ይመለከተናል ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ የተማረውን ክፍል ስም እያወጡ በየማጎሪያው በእስር በማሰቃየትና ገሚሱንም በማሳደድ ኢትዮጲያ የምንላትን የሁላችን  የሆነች  ታላቅ ሃገር በሞኖፖል በመቆጣጠር የአንድ ግለኛ ቡድን የግል ሃብት አረገዋታል፡፡
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ለሃገርና ለሕዝብ የተሻለ ሃሳብ አለን የሚሉትን የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችን ጨምሮ የሞያ ስነምግባራቸውን ጠብቀው አምባገነኑ ስርዓት በሕዝብና በሃገር ላይ የሚፈፅመውን ግፍና በደል በብእራቸው ያጋለጡ ጋዜጠኞችን በጅምላ ለሱ የሚመቸውን ስም እያወጣለቸው በየማጎሪያ ካምፑ የወረወራቸው እጅግ ብዙ የህሊና እስረኞች አሉ፡፡ ከህፃን ልጁ ተለይቶ በእስር የሚማቅቀው እስክንድር ነጋ፣  እውነት በመፃፏ ከነህመሟ በእስር የምትማቅቀው እርዮት አለሙ፣ በዘረኛው ቡድን ላይ የሰላ ሂስ በማቅረቡ በአሸባሪነት ተፈርጆ በእስር የሚሰቃየው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ እንዲሁም  በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳን ጨምሮ ብዙ ምርጥ የሃገር ልጆች በዚህ ዘረኛ ቡድን ግፍ እየተፈፀመባችው ይገኛሉ፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ በተለይ በሃገር ቤት ያለው የበደሉ ገፈት ቀማሽ የሆነው ወገን ለለውጥ ጥግ ድረስ ለትግል አልተዋቀረም፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ የሚተው አይደለም የልቁኑም ወያኔን ለመታገል ቆርጠው ከሚሰሩ የህዝብ ሃይሎችን በመቀላቀል ትግሉ የሚጠይቀንን ሁሉ የምንሆንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
ኢትዮጲያ የነማን፣ የማን እንደሆነች ማወቅ የሚቸግርበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ጥቂት ዘረኛ ቡድኖችና ሆድ አደሮች የነገሱባትና ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የቅንጦት ኑሮ የሚኖሩባት፣ ብዙሃኑ ለሃገርና ለዳር ድንበሩ መከበር ከጥንት ጀምሮ አጥንቱን ከስክሶ ደሙን አፍስሶ ባቆያት ሃገር ላይ የበይ ተመልካች ሆኖ በርሃብና በእርዛት በሚኖርባት ሃገር ናት፡፡
እናም ይህ ዘረኛ የወያኔ ስርዓት እንዲያበቃለትና ዘመን እንዳይሻገር እነሱ እንደሚሉን ጥቂቶች(ኢምንቶች) ሳንሆን እልፍ አእላፍ ሆነን ለነፃነታችን፣ ለሃገራችን አንድነትና ለወደቀው ክብራችን ብለን በአንድነት እንነሳ፡፡ ኢትዮጲያ የኛ የብዙሃን እንጂ የጥቂት ዘረኛ ቡድን መፈንጫ አትሁን!!!!!!!!!!
ኢትዮጲያን እግዚሀብሔር የባርክ!!!!

በኢትዮጵያዊያ የመሳፍንት ዘመን አጭር ታሪክ

በኢትዮጵያዊያ የመሳፍንት ዘመን አጭር ታሪክ

June 16, 2013

መምህር ገብረኪዳን ደስታ “ለVOA” ለሰጡት መልስ የግል አስተያየት

በተክሎ አባተ
ከኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ሳንገባ ለዚህ ጽሁፍ መነሻ እንዲያመች ትንሽ ቀንጨብ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በ1529 – 1543 ዓ.ም ኢማም አህመድ የተባለው የአፋር ተወላጅ በሐረር አካባቢ የሚገኙ ደጋፊዎቹን በማስተባበር በመላው ኢትዮጵያ የእስላም መንግሥት ለመመስረት ከፍተኛ ጦርነት አድርጓል። በጦርነቱ ምክንያት በእሰልሞናዊ ገዥዎችና በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ብዙ እልቂት ደረሰ። በዚህ የተነሳ የያሬድ መንፈሳዊ ኪነት እድገት ሳያሳይ በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ብቻ ተወስኖ ቀረ።
ነገ ርግን ከኢማም መሃመድ ጥፋት በኋላ የሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት የቀድሞ ግዛቶቹን አስመለሰ። ቢሆንም በተደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች የኃይል ክፍተት የተነሳ ከደቡብ እስከ ምስራቅ ድረሰ የኦሮሞዎች ወረራ ተስፋፋ። የኦሮሞ ወራሪዎች ገዳ በሚባል ስርዓት ሉባ በሚባሉ የጦር አበጋዞች አማካኝነት ጋሻና ጦር ይዘው የአዳልን የአካባቢ ነገሥታት እየወጉ፤ ነዋሪውን እያስለቀቁ በራሳቸው ቋንቋና ባሕል ለማዋሃድ ከፍተኛ ጦርነት አካሂደዋል።
እሮሞዎች ያደርጉት ጦርነት ራሳቸውን ችለው መንግሥት አይመስርቱ እንጂ በደቡብ መሀል አገር የሚገኙ እሮሞዎች፤ ገራጌዎች፤ ከምባታዎች፤ ሃዲያዎች፤ ሲዳማና ሌሎችም ብሄር-ብሄረስቦች ተቀላቅለው ግዛታቸውን ለማስፋት ሞክረው ነበር።
በጦርነቶች ምክንያት በአንድ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች እየፈለሱ ከሌሎች ጋር በመቀያየጥ አዲስ የአኗኗል ዘቤዎችን በመለማመድ በአሸናፊዎች ተጽኖ ሥር የመውደቅ እጣ ደርሶባቸዋል። በተለይ በምስራቅ አፋር፤ ሱማሌና እሮሞዎች ጐልቶ ይታይ ነበር።
በዘመነ መሳፍንት በኦሮሞ መሪዎች አማካኝነት ይደረጉ የነበሩ ጦርነቶች ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በሽዋ ከነበሩ መንግሥታት ጋር በመመሳሰል አጼ ሱሰንዮስ የተባሉ እሮሞዎችን ይዘው ከጐንደር ነገሥታት ጋር ተዋግተው ጐንደር መንግሥት መስርተው ነበር። በየጊዜው የሚደረጉ የሥልጣን ፉክክሮች የኃይል ሚዛናቸው እያየለ ሲመጣ ዛጉዌዎች የሃይማኖትንና የአገር አመራርን ለሰለሞናዊ ሰርወ-መንግሥት አስተላፉ። በዚህ ጊዜ በሰሜን በኩል አማራና ትግሬ የበላይነት እንዳላቸው በሌሎች ዘንድ ጥርጣሬን እንዳስከተለ ይገመታል።
ከላይ የተጠቀሰውን አጋጣሚ በመጠቀም ቱርክ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የአካባቢ የጐሳ መሪዎችን በጥቅማጥቅም እየደለለች በ1557 ምጽዋን ተቆጣጠረች። እንዲሁ ግብጽ የሱዳን ወደብ የነበረውን ዘይላን ያዘች። ከዛም እስከ ቀይ ባሕር ድረስ ለመስፋፋት ሞክራለች። በ19ኛው ከፍለ ዘመን ጣሊንና እንግሊዝም ቅኝ ግዛታቸውን ለማስፋፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስላደረጉ አገሪቱ በውጭና በእርስ በርስ ጦርነት ተወጠረች።
በዘመነ መሳፍንት የግዛት ዘመን የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት እየተዳከመ ሲመጣ የትግራይ ገዥ የነበሩ ራስ ሚካኤል ስሁል የተባሉ ኢዮአስ 1ኛን በ1769 ከሥልጣን አውርደው አስገደሏቸው። እንዲሁ አጼ ዮሃንስ 2ኛ አጼ ተክለሃይማኖት 2ኛን ሲሾሙ ለዘመነ መሳፍንት የመጀመሪያው ክስተት ሆነ።
የተካሄደው የእርስ በርስ የሥልጣን ሽኩቻ በተራዘመ ቁጥር ግብጽ አጋጣሚውን በመጠቀም 1874 ዓ.ም ሀረርን ተቆጣጥራ ነበር። በ1875 ዓ.ም በሰሜን በኩል ጣሊያኖች ከፍተኛ የመስፋፋት ወረራ አደረጉ። ይሁን እንጂ በአጼ ዮሃንስ አራተኛ የግዛት ዘመን ሥመ ጥሩው አሉላ አባ ነጋ ባደረጉት የተቀነባበረ ጦርነት በ1887 ዓ.ም ዶጋሌ ላይ ጣሊያን መሸነፏ አልቀረም። በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲሁ ጉራአ አካባቢ ግብጽ የላከቸው ጦር በኢትዮጵያ አልበገር ባይነት ድባቅ ተመታች።
በኢትዮጵያ የተማከለ መንግሥት ለመመስረትም ሆነ የበላይነትን ለማሳየት ብዙ ጊዜ የእርስ በርስ ጦርነቶች መካሄዳቸውን ከፍ ሲል አውስተናል። ይህ ሁኔታ ባለበት አጼ ቴዎድሮስ 2ኛ በጐንደር በኩል ሥማቸውና ኃይላቸው ጐልቶ ወጣ። ነገር ግን በአገሪቱ የተማከለ መንግሥት ለመመስረት ከፍተኛ ተጋድሎ በሚያደርጉበት ወቅት የቤተክርስቲያን ሹማምትም ሆኑ አንዳንዶች ሥልጣናቸውን ላለማስነጠቅ ውስጥ ውስጡን በአጼ ቴዎድሮስ ላይ መዶለት ጀመሩ። ከዚህ አድማ ባልተናነሰ ሁኔታ የየጁ ኦሮሞ የሽዋ፤ የጐጃም መሳፍንቶች በጐንደር በኩል የሥልጣን ተፎካካሪ የሆኑ አጼ ቴድሮስን ለመውጋት ተነሱባቸው።
የሰሜኑ የትግሬው በዝብዝ ካሣ (አጼ ዮሃንስ 4ኛ) ሥጣል ከቴዎድሮስ እጅ ነጥቀው ብቸኛ ንጉሥ ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራቸው የመሣሪያ እርዳታ አገኛለሁ በሚል ከኢንግሊዝ ጋር ተስማሙ። ይሁን እንጅ አጼ ቴዎድሮስ የውጭ ባዕድ ወራሪ ኃይል አገሪቱን እንዳይደፍራት ኃይላቸውን በማጠናከር ብዙ ጊዜ ተዋግተዋል።
ነገር ግን አገር በቀል ባንዳዎች ለእንግዝሊዝ ጦር መረጃ እያቀበሉ የአጼ ቴዎድሮስ ኃይል እንዲሳሳ ማድረጋቸው አልቀረም። ለዚህ ማስረጃ አጼ ዮሃንስ አራተኛን ከእንግሊዝ ጋር ባደረጉት ውል የናፒየርን ጦር ወደ መቅደላ መምራታቸው ነው። በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ የሚደርስባቸውን ተቃውሞ እየተጋፈጡ ከ1855 1868 በንግሥና ቆይተው መቅደላ ላይ ከኢንግሊዞች ጋር በተከፈተው ጦርነት ለጠላት እጅ መስጠትን እንደነውር ቆጥረው የራሳቸውን ሽጉጥ ጠጥተው ለአገራቸውና ለሕዝባቸው መስዋዕት መሆናቸውን ታሪክ መዝግቦታል።
ከአጼ ቴዎድሮስ በኋላ አጼ ዮሃንስ 4ኛ ኃይላቸው በማጠናከር ከተቀናቃኞቻቸው ጋር ከፍተኛ ውጊያ አድርገዋል። በእንግሊዝ መንግሥት ተባባሪነት የአጼ ዮሃንስ አራተኛ ኃይል ጐልቶ ሊወጣ ቻለ። ይሁን እንጂ የአካባቢ ገዥዎችን ከማስተባበር ባለፈ አገሪቱን በተማከለ መልክ ማስተዳደር አለመቻላቸውን ከታሪክ መረዳት አያዳግትም። በሰሜን ጀግናው አሉላ አባ ነጋ የጣሊያንን ወረራ እየተጋፈጡ ባለበት የአጼ ዮሃንስ ኃይል እምብዛም እንዳልታከለበት የብዙዎች ግምት ነው።
አጼ ዮሃንስ አገራቸውን ለባዕድ ወራሪ አሳልፈው ላለመስጠት መተማ ላይ ከድርቡሾች ጋር ሲዋጉ ሕይወታቸው ልፏል። አንገታቸው ተቆርጦ ካርቱም መሄዱ እውነት ነው። በዚህ ሁኔታ አጼ ዮሃንስ አራተኛ 1872–1889 ድረሰ ሥልጣን ላይ መቆየታቸው የማይታበል የታሪክ ሃቅ ነው።
አጼ ዮሃንስ አራተኛ ኢትዮጵያን በተማከለ መልክ ለማስተዳድር ጥረት በማድረጋቸው ለኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው። ነገር ግን በግዛት ዘመናቸው ሕዝብ አብሯቸው ተሰልፎ እያለ በእስልምና ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመሩ። አጼ ዮሃንስ አራተኛ የአስተዳደር ጉድለት ወይም ብቃት ስላልነበራቸው በእስልምና ተከታይ ሕዝብ በኩል ሊያገኙ ይችሉ የነበረው ድጋፍ አጡ። ጠቅለል ባለ መልኩ አጼ ዮሃንስ አራተኛ በታሪክ መልካም ሥም ቢኖራቸውም አጼ ቴውድሮስ በባዕድ ወራሪ እንዲጠቁ ማድረግ ባልተገባቸው ነበር። በዚህ የተነሳ ይመስላል ብዙ ጊዜ የአጼ ዮሃንስ መንግሥት በባዕዳን የተገነባ እንደነበር የተለያዩ የታሪክ ፀኃፊዎች ዘግበውታል።
በልማት በኩል ያደረጉት አስተዋጽዖ ጐልቶ አልታየም። የእስልምናን ሃይማኖት ጠቅለው ወደ ክርስትና ሃይማኖት ለማስፋፋት ከፍተኛ ሥራ ሰርተዋል። ቢሆንም ከጥቅሙ ጉዳቱ እያመዘነ የሃይማኖት ልዩነት በፈጠረው ክፍተት የሰው ሕይወትና ንብረት ከማለቁም ባሻገር የእስላምና የክርስቲያን አንድነት እንዳይጠነክር የአጼ ዮሃንስ አራተኛ አስተዳደር ምክንያት ሆኗል።
ባጠቃላይ በዛ ዓለም ባልሰለጠነት፤ አገሪቱ በእርስ በርስ የሥልጣን ሽኩቻ እየታመሰች ባለበት አገራቸውን ለድርቡሽ አሳልሆፎ ላለመስጠት ያደረጉት ጀግንነት ለመላ ኢትዮጵያ ዋስትና ነበር ማለት ይቻላል።
ከዝርዝር ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት በመጀመሪያ ደረጃ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ጊዜያቸውን ወስደው የአገር ታሪክ በመፃፋቸው ላንደቃቸው እወዳለሁ። ከዚህ በፊት የተፃፉም ሆነ ያልተፃፉ በታሪክነት እንዲቀመጡ ችሎታ ያላቸው የመፃፍ አገራዊ አደራ አለባቸው። እርግጥ ነው ሰው የማይገሰስ ሰብአዊ መብቱን በመጠቀም መፃፍና መናገር እንደሚችል አምናለሁ። ነገር ግን የአገርና የሕዝብ ታሪክ በዘፈቀደና ክልልን ያማከለ ከሆነ ለትውልዱም ሆነ ለአገር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ከመምህር ገብረ ኪዳን አንደበት ማድመጥ እንደተቻለው ችግራቸው ከአጼ ምኒሊክ ጋር የተያያዘ ነው። ይህን ካልኩ ዘንዳ ወደ መነሻየ ላምራ።
መምህር ገብረኪዳን ደስታ በቅርቡ ስለአጼ ዮሃንስ አራተኛ ገድል የሚያሳይ መጽሕፍ መፃፋቸው ይታወሳል። ይህን መነሻ በማድረግ የአሜሪካ ሬዲዮ አማርኛ ዝግጅት የትግራይ ቃላቀባይ አቶ ገብራይ ገብሩ የአጼ ዮሃንስን ገድል የሚያወሳ መጽሕፍ መፃፍ ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ማዳመጥ ችያለሁ።
የመምህር ገብረ ኪዳን ደስታ መልስ፟፦ሌሎች ስለአካባቢያቸው ሲጽፉ እኔም ስለአካባቢየ እጽፋለሁ፤ አጼ ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ጥሩ ሰርተዋል፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ታሪክ የተባለው ለአንድ ውስን ሰርዓ-ተማኅበር ብቻ በማጠንጠን አንድ አቅጣጫ ይዟል፤ ለማቃናት የሚተጋ ሰው አላጋጠመኝም፤ በአጼ ዮሃንስ ላይ የተሳሳተውን ዘገባ ለማስተካከል ነው አሉ። ጋዜጠኛው ገብራይ ገብሩ አክሎ ለዚህ ምን ማሰረጃ አለዎች የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው።
የደራሲ ገብረ ኪዳን መልስ ፦ ስለመረጃ ከትግራይ ሕዝብ በላይ ምንጭ የሚሆነኝ ሌላ ሕዝብ የለም የሚል ነበር።
መምህር ገብረ ኪዳን ማብራሪያቸውን ሰፋ በማድረግ አጼ ምኒሊክ የሽዋ ሰው ብቻ ስለነበሩ ሰሜኑን ክፍል እንደ ኢትዮጵያ አይመለከቱትም፤ ለኮሎኒያሊዝም ምክንያት ናቸው ወዘተ በማለት ደጋግመው ነግረውናል።
አዎ አጼ ምኒሊክ የሸዋ ሰው መሆናቸው አይካድም፤ በዚህ ሁላችን ልዩነት ያለን አይመስለኝም፤ እሽ እንስማማ። ችግሩ ግን የሽዋ ሰው ብቻ ስለነበሩ ሰሜኑን ክፍል እንደ ኢትዮጵያ አይመለከቱትም የሚለውን አምኖ ለመቀበል ህሊናየ አልደፈረም። አባቶቻችና የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱን ከሆነ አጼ ምኒሊክ የመላ ኢትዮጵያ አካል መሆናቸውን ነው ታሪክ የነገረን።
በዘመኑ መሳፍንታት ሲነሱ መጀመሪያ የአካባቢያቸውን ሕዝብ ይሁንታ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ነው። የአጼ ዮሃንስን፤ የአጼ ቴዎድሮስም የኃይል አደረጃጀት እንዲሁ በአካባቢ ላይ የተገነባ ነበር። የአጼ ምኒሊክም አደረጃጀት ከዚህ የተለይ አይደለም። በዚህ ዓይነት መነሻቸውን አውቀው እያሰፉ ሌላውን አካባቢ ማስተዳደር ችለዋል።
አጼ ምኒሊክ ከአጼ ዮሃንስ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አጼ ምኒሊክ አንድ ነገር ከማድረጋቸው በፍፊት አቅምና ችሎታቸውን የማመዛዝን ችሎታ ነበራቸው። በወቅቱ አጼ ዮሃንስ ከእንግሊዝ ባገኙት መሣሪያ የተጠናከሩ ስለነበር ለብቻ ከመዋጋት ይልቅ ኃይል ካለው ጋር በመሆኑ አገሪቱን ማስተዳደር ይቻላል በሚል አጼ ምኒሊክ ከትግሬ ከተወለዱት ከአጼ ዮሃንስ ጋር ወዳጅነት መፍጠር ብቻ ሳይሆ እስከ መጋባት ደርሰዋል። ታዲያ ከሸዋ እስከ ትግራይ ድርሰ ዘር ሳይለዩ በጋብቻ ከተሳሰሩ የሽዋ ብቻ ነበሩ ለማለት አያስደፍርም። ታሪኩ እንደታሪክ ይቀመጥ ከተባለ የጠባብነት ስሜት ያልነበራቸው ምኒሊክ ብቻ ነበሩ ማለት ይቻላል።
የኢትዮጵያን ሉዓዊነት ለማስከበር የተማከለ መንግሥት ለመፍጠር የተለያዩ አካባቢዎችን አንድ እያደረጉ እቅዳቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ እየተንቀሳቀሱ እያለ ከመሳፍንቶች የእርስ በርስ ጦርነት በከፋ መልኩ የጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን ለመቀራመት ወረራ ጀመረ። ይሁን እንጅ በአጼ ምኒሊክ ድፍረትና በእትጌ ጣይቱ ብልህነት በ1896 የአድዋን ድል ተጐናጸፉ። ነገር ግን የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግሥት በመላላቱ የተነሳ ቀረጥ ወይም ታክስ የሚከፍለው የሰው ቁጥር ቀነሰ። የገቢ ምንጭ በቀነሰበት ሁኔታ እስከ መጨረሻው ከጣሊያን ጋር ጦርነት ቢገጥሙ ውድቀት ሊደርስባቸው እንደሚችል በመገመት ለጊዜው ኤርትራን ከጣሊያን እጅ ማስወጣት አልቻሉም።
ለዚህ ዋናው ምክንያት የኢኮኖሚ አቅም ማነስና በሰሜ ኢትዮጵያ አገር በቀሎች ከጠላት ጋር በመወገናቸው ወደ ፊት ቢገሰግሱ ድል ሳይሆን የያዙትን እንደሚያጡ ከግምት በመሳገባት ነው።
የዚህ አይነት የጦርነት እስትራቴጅ በዚህ በ21 ክፍለ ዘመንም ቢሆን አንድ መንግሥት ለውጊያ ሲነሳ መጀመሪያ የጦር ኃይሉን የኢኮኖሚ አቅሙ በማገናዘብ ነው ። ታዲያ የአጼ ምኒሊክ ጥፋት ተምኑ ላይ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ይሁን እንጅ አጼ ምኒሊክ ቀስ በቀስ የመሳፍንት ገዥዎችን ወደ አንድ በማምጣት ለማዋሀድና አገሪቱ ከውጭ ወራሪ ጦርነት ተላቃ የቴክኖሎጅ እድገት እንድታሳይ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የተለያዩ የእምነት ተከታዮች የእርስ በርስ ውጊያን አስቀርተው ወደ አንድ እንዲመጡ አድርገዋል።
አጼ ምኒሊክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬው ምሁር ያላሳየውን የተራማጅነት ባሕሪ እንደነበራቸው አሳተው አልፈዋል። በአገሪቱ ሰላም የሰፈነ በአጼ ዮሃንስ ዘመን ሳይሆን በአጼ ምኒሊክ የግዛት ዘመን ስለመሆኑ ታሪክ ነጋሪ አያስፈልግም። ድሃው ሰርቶ የመኖር መብቱ ተከብሮ፤ ግብር እንኳን መክፈል ያልቻሉ እርዳታ እየተሰጣቸው በሰላም የኖሩበትን ዘመን ፈጠረዋል። የአግሪቱን የሥልጣኔ ጉዳና ለማፋጠን ገጠሬውን ከከቴሜው፤ የውጩን ከኢትዮጵያ ጋር ለማገናኘት የባቡር መስመር፤ የስልክ አገልግሎት እንዲስፋፋ የመጀመሪያ የእድገት በር ከፋች አጼ ምኒሊክ ናቸው።
በአጼ ዮሃንስ ዘመን ጣሊያን በቀይ ባሕር ሲስፋፋ ነበር። አጼ ምኒሊክ ግን የባድ ወራሪን መስፋፋት ዘመቻ ለመደምሰስ ባደረጉት ጦርነት አድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸው ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ አጼ ምኒልክ ብቻ ናቸው። የአገሪቱን የእርስ በርስ ጦርነት አስወግደው አዲስ አበባን ቆርቁረው ዛሬ ለአፍሪካ አንድነት ጽሕፈት ቤት በር የከፈቱ ምኒሊክ ብቻ ናቸው።
ኢትዮጵያን በሕግ የሚተዳደር ሕዝብ ፈጥረዋል። ዓለም ባልሰለጠነበት በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት አጼ ምኒሊክ ሥልጣ ከአንዱ ወሌላው በሰላም እንዲሸጋገር ለመጀመሪያ ጊዜ የዴምክራርሲን ይትባህል አሳይተው አልፈዋል።
ደራሲው ከአንደበታቸው ሲናገሩ እንደተደመጠው ከሆነ በጐጥ ዙሪያ የተሸበቡ መሆናቸውን አሳይቷል።
በጣም አዛዛኝ ሆኖ ያገኘሁት ደግሞ መላውን ኢትዮጵያ በማግለል ምስክሬና የታሪኩ ምንጭ የትግራይ ሕዝብ ብቻ ነው ማለታቸው የደራሲነታቸውን ማንነት በሚገባ አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህወሐትን የድል ቀን ትግራይ ውስጥ ሲያከብሩ እንኳ ከወርቅ ሕዝብ ተወለድኩ ያሉትን ቃል ያጠናከረ መጽሕፍ መስሎ ታይቶኛል።
ኢትዮጵያ ከመሳፍንት እስከ አሁን ድረሰ ሕዝቦች ተዋደው ተፋቅረው ዘር ሳይለዩ ተጋብተው ተዋልደው አገራችን አቆይተው አስረክበውናል። በመሆኑም ይህ ትውልድም ሆነ ቀጣዩ ትውልድ አንድ በሆነች አገሩ እንዲኮራ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር የታሪክ መጽሀፍ እንደሚፈልግ አያጠያይቅም።
በመጨረሻ፦መምህር ገብረኪዳን ደስታ በቃለመጥይቁ ላይ የተሳሳትኩት ካለ እታረማለሁ ማለታቸው ኢትዮጵያዊነትን ያሳያል። በመሆኑም መምህር ገብረኪዳን በታሪክነት ያቀረቡትን መጽሀፍ ለአገርና ለሕዝብ አፍራሽ መሆኑን ልብ እንዲሉት ተመልሰው እንዲያነቡትና የሚስተካከለውን በእርምት መልክ ቢያወጡት በሕዝብ ዘንድ ሊኖረዎት የሚገባው ተቀባይነት ቦታ ይኖረዋል። ነገር ግን ወግቶ ይማርህ ከሆነ በታሪክ ማስወቀሱ አይቀርም።
አንባቢያን በዚህ ዙሪያ የተሳሳትኩት ወይም የጐደለ ካለ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።
ሁሉም ቀናውን እንዲያሰብ የእግዚአብርሄር ረዴት ይደርብን።

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

June 16, 2013 ከኢየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…
አቶ ጌታቸው በቅርቡ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ወ/ስላሴ ከአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ በማድረግ እንደተበቀሏቸው ማወቅ ተችሏል። በጎንደር ተወልደው ያደጉትና በሰባዎቹ መጀመሪያ አመታት ሕወሐትን የተቀላቀሉት አቶ ጌታቸው በአብዛኛው አመራር « ጥሩ ሰው ነው፣ ላመነበት ነገር ወደኋላ የማያፈገፍግ..» ተብሎ እንደሚነገርላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። በሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ተተክተው በ1994ዓ.ም ወደስልጣን የመጡት ጌታቸው በተጨባጭ ሙስና ፈፅመዋል የሚል መረጃ እንደሌለ ያመለከቱት ምንጮቹ ነገር ግን በአብዛኛው ባለስልጣናት የሚፈፀመው መጠነ ሰፊ ዘረፋና ሙስና በተመለከተ በርካታ መረጃና ማስረጃ በጌታቸው እጅ እንደሚገኝ አያይዘው ገለፀዋል። በሌላም በኩል በ1994ዓ.ም በደህንነት ቢሮ የበታች ሹማምንት ሆነው በአቶ መለስ ከተመደቡት መካከል ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስና ወ/ስላሴ እንደሚገኙበት ያስታወሱት ምንጮቹ፣ አክለውም ሁለቱ የሕወሐት አባላት ከስር ሆነው ፈላጭ ቆራጭ አመራር ይሰጡ እንደነበረና በዚህ ተግባራቸው ከጌታቸው ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸውን አስታውቀዋል። ኢሳያስ ከአቶ መለስና ስብሃት ጋር ስጋ ዝምድና እንዳለው ማወቅ ተችሏል። በተለይም በዚህ ጣልቃ ገብ አሰራር ተማረው የቆዩት አቶ ጌታቸው ከቅርብ አመት ወዲህ ከአቶ መለስ ጋር ጭምር አለመግባባት ፈጥረው እንደነበረ ሲታወቅ፣ አቶ መለስ የጤና ችግር ተፈጥሮቦቻው እንጂ በዛው ወቅት ከስልጣን ሊያነሷቸው ከወሰኑት ባለስልጣናት አንዱ ጌታቸው እንደነበሩና ከመለስ ህልፈት በኋላ የደህንነቱ ሹም የታቀደባቸውን እንደደረሱበት ምንጮቹ አስታውቀዋል። የጠ/ሚ/ሩን ህልፈት ተከትሎም አቶ ጌታቸው ስልጣናቸውን በማደላደል ጎልተው መውጣቸውንና በወ/ስላሴ ላይ የወሰዱት እርምጃ ማስረጃ እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአቶ ጌታቸው ወንድም ዳንኤል አሰፋ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል ተደርጎ ባለፈው ጉባኤ መመረጡ ሲታወቅ፣ የዳንኤል ባለቤት የስብሃት ነጋ ዘመድ እንደሆነች ተጠቁሞዋል።
ከስልጣን የተነሳው ወ/ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን እንደሚታወቅ ያስታወሱት የቅርብ ምንጮቹ « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ሲሉ ያስረዳሉ። አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው ብለዋል። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር – እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አስታውሰዋል። ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አዜብ መስፍን በቅርቡ ቨርጂኒያ መጥተው እንደነበረ ምንጮች ገለፁ። ድምፃቸውን አጥፍተው የመጡት አዜብ በተጠቀሰው ከተማ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ የገዙት መኖሪያ ቪላ ውስጥ ለጥቂት ቀናት እንደቆዩና ወደአገር ቤት እንደተመለሱ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ከቪላው ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎች እየተጠናከሩ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ

June 17, 2013

“ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”

ጎልጉል የድረ-ገጽ ጋዜጣ
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
Allegations of Corruption Emerge Against Federal Government Examiners
Former Gambella Regional President, Mr. Omot Obang Olom
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል
ቀደም ሲል የጋምቤላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ከላይ የተጠቀሰውን የሙስና ወንጀል በማጋለጣቸው ጋምቤላ መኖር ሳይችሉ ቀርተው ራሳቸውን ሸሽገው ለመኖር ተገደው እንደነበር የሚያውቋቸው ለጎልጉል አስረድተዋል።
“አቶ ተስፋዬ ሙስናን በማጋለጣቸው በፍርሃቻ ራሳቸውን ደብቀው ሊኖሩ አይገባም” በማለት ኢህአዴግ ከለላ እንደሚሰጣቸው ቃል በገባላቸው መሰረት ከተሸሸጉበት የወጡት አቶ ተስፋዬ ሰንጋተራ ትንሳዔ ሆቴል ከጋምቤላ ልጆች ጋር መገናኘት ይጀምራሉ።
ባለፈው ሳምንት ከፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ከያዙ በኋላ ኮሚሽነሩ በድንገት ለለቅሶ ወደ ጎንደር በመሄዳቸው ቀጠሮው ለሳምንት ይራዘማል። ለሰኞ (ሰኔ10፤2005) አዲስ ቀጠሮ ይይዛሉ።
በስልክ ያነጋገርናቸው ትንሳዔ ሆቴል አካባቢ እንደነበሩና ለጉዳዩ ቅርበት እንዳላቸው የሚገልጹ የጋምቤላ ተወላጅ የስራ ሃላፊ እንዳሉት አቶ ኦሞት ኦባንግ ለአቶ ተስፋዬ ስልክ ደውለው ነበር። አቶ ተስፋዬ ህይወታቸው ከማለፉ ሁለት ቀን በፊት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦሞት በስልክ ተማጽንዖ አቅርበው ነበር።
አቶ ኦሞት “እውነት ነው ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀጠሮ የያዝከው?” በማለት ይጠይቃሉ
“አዎ! እውነት ነው” በማለት አቶ ተስፋዬ መልስ ይሰጣሉ።
አቶ ኦሞት መልሰው “እንግዲያውስ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመግባትህና ከማነጋገርህ በፊት ሁለታችን መገናኘት አለብን። የምንነጋገረው ነገር አለ” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። አቶ ተስፋዬ ስለ ስልክ ልውውጡ እንደነገሯቸው የተናገሩት እኚሁ ሰው፣ አቶ ኦሞት በስልክ ደጋግመው በመደወል ያቀረቡትን የ”እንነጋገር” ጥያቄ አቶ ተስፋዬ አልቀበልም ይላሉ።
ጋምቤላ ስራቸውን ለቀው ራሳቸውን ደብቀው የኖሩት በእርሳቸው ምክንያት መሆኑን፣ ፍትህ እንደሚፈልጉ፣ አሁን ለመነጋገር ጊዜው እንዳልሆነ፣ ዘርዝረው ለአቶ ኦሞት መናገራቸውን ያወሱት የጎልጉል ምንጭ፣ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው አቶ ኦሞት በንዴት ተዛልፈው ነበር።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው እንግዲህ አቶ ተስፋዬ ትንሳዔ ሆቴል ሰዎችን በመላላክና በመታዘዝ ከሚኖር አንድ የጋምቤላ ሰው /አቶ ተስፋዬ የሚረዱት በምግባር ጉዳይ የሚታማና ጸበኛ የሚባል ሰው ነው/ አብረው ተቀምጠው ምሳ እየበሉ ሳለ አቶ ተስፋዬ አረፋ ይደፍቃቸዋል። ወዲያው ከተቀመጡበት ተንሸራተው መሬት ይወድቃሉ። ቀጥሎም ሰውነታቸው ይዝልና ኮማ ውስጥ ይገባሉ። ከአፋቸው እየተዝለገለገ የሚወጣው ፈሳሽ በመጨመሩና የተለያየ ርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ ስላልቻሉ ሆስፒታል ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
አቶ ተስፋዬ ሆስፒታል ከመድረሳቸው በፊት እንደሞቱ የሚናገሩት የጎልጉል ምንጭ አሟሟታቸው ከመርዝ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ በሙስና ወንጀል ላይ ያሰባሱትን መረጃ ለተለያዩ አካላት የበተኑ ስለሆነ እሳቸውን በመግደል ማድበስበስ እንደማይቻል አስታውቀዋል። አቶ ተስፋዬ ሙስና ካጋለጡ በኋላ መሰወራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። በተያያዘ በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ውስጥ ከ70በመቶ በላይ የሆኑት የህወሓት የቀድሞ ታጋዮች የነበሩና የክልል አንድ ተወላጆች መሆናቸው የአቶ ተስፋዬን አሟሟት ይበልጥ ውስብስብ እንዳደረገው አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “የአቶ ተስፋዬ ሞት አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ” በማለት ስለ አቶ ተስፋዬ ሞትና አሟሟት መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
“አቶ ተስፋዬ ለእውነት ሲል ሞቷል። ኢህአዴግ ውስጥ በርካታ የወንጀል መረጃ ያላቸው ወገኖች አሉ። እንዲህ ያሉ ዜጎች በየትኛውም ዘመን አይረሱም። የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ስማቸውና ታሪካቸው ከጨዋነታቸው ጋር ተመልሶ ህያው ይሆናል። ሌቦችና ነፍሰገዳዮች ወደ ህግ ሲያመሩ፣ እንደ አቶ ተስፋዬ አይነቶቹ የመጪው ትውልድ ታላቅ ምሳሌ ሆነው እየተወደሱ ህያው ሆነው ይኖራሉ” የሚል አስተያየት የሰጡት አቶ ኦባንግ፤ አቶ ተስፋዬ ያሰባሰቧቸው የሙስናና ተመሳሳይ ወንጀሎች ማሳያ ሰነዶች እጃቸው ላይ ስላለ አቶ ተስፋዬን በመግደልና በማስገደል ወንጀል ማድበስበስ እንደማይቻል ተናግረዋል።
የአቶ ተስፋዬ የቀብር ስነስርዓት ጋምቤላ መፈጸሙን ለመረዳት ተችሏል። ቤተሰቦቻቸውን በማግኘት ሆስፒታሉ ስለ አሟሟታቸው የሰጠውን አስተያየት ጠይቀን ለመረዳት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

ኢትዮጵያ እና ዴሞክራሲ

ኢትዮጵያ እና ዴሞክራሲ

June 18, 2013 ዞን9 ብሎግ
ዴሞክራሲ ምንድን ናት? የዴሞክራሲ መናስ እንዴት ትወርዳለች? እንደምንስ ትፀናለች? የዲሞክራሲ ዋነኛ ጠላቶችስ እነማን ናቸው? የሚሉት ጥያቄዎች ለረጅም ዘመናት በየእለቱ አዲስ መልስ እየተሰጠባቸው እና አዲስ ጥያቄ እየፈጠሩ አንድ እና ወጥ መግለጫ ሳያገኙ ቀጥለዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ጥያቄዎች ጠቅለል አድርጎ ይገልፅልናል የምንለው የአሜሪካው 16ኛ ፕሬዘደንት፣ አብርሃም ሊንከን ታዋቂውን የጌትስበርግ ንግግራቸውን ያጠቃለሉበት “[…] that government of the people, by the people, for the people, shall not perish from the earth.” የተባለው ሀሳብ ነው፡፡ ከሕዝብ ለሕዝብ፣ በሕዝብ የሆነውን ስርዓትም ዘመናዊ ፀሃፍት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደሆነ እና የዴሞክራሲ ምንጯ ሕዝብ፤ ጠላቷም የሕዝብ ጠላት እንደሆኑ ይተነትናሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዴሞክራሲ አይሰራም፤ ቀልድ ነው፤ “Democracy can’t work. Mathematicians, peasants, and animals, that’s all there is, so democracy, a theory based on the assumption that mathematicians and peasants are equal, can never work.” ከሚሉት ከነሮበርት ሔንላይን እስከ “Democracy is the worst system, except for all the other systems” በማለት የዲሞክራሲን አስከፊነት ግን ምርጫ አልባነት እስከሚናገሩት ድረስ እናገኛለን፡፡ እንግዲህ ይህ በሀሳብ መለየት ነው እንጅ ዴሞክራሲማ እጅግ ተመራጩ ስርዓት ነው በሚል እሳቤ ነው የምንቀጥለው፡፡
ችግሩ የት ላይ ነው?
ዴሞክራሲን ለመግለጽ ሊቃውንት አንድ ቁርጥ ያለ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ምክንያት ሁሉም የራሱን ትርጉም በመስጠት ለአመቸው ተግባር ሲያውለው ይታያል፡፡ ከሀገር ሀገር፤ ከጊዜ ጊዜ አንዴ እየሰፋ፤ አንዴ እየጠበበ እጅግ የበዙ እና የተለያዩ ትርጉሞችን ይዞ በሩን አሁንም ለሌላ የትርጉም ጋጋታ ክፍት አድርጎ አዲስ ስያሜን ይጠብቃል – ዴሞክራሲ፡፡ ይሄን የበዛ የትርጉም ልዩነት የተመለከተው ጆርጅ ኦርዌል ‘Politics and the English Language’ በተባለው መጣጥፉ ‹‹ዴሞክራሲ ስምምነት ላይ የተደረሰበት ትርጉም ያጣ ቃል ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ትርጉም ለመስጠት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ከሁሉም አቅጣጫ ውግዘት ይደርስበታል፤ ምክንያቱም ሁሉም በውስጡ የራሱ ትርጉም አለውና ያ ትርጉም እንዲፈርስበት አይሻም… እንደ ዴሞክራሲ ያሉ ቃላት ለእያንዳንዱ ሰው የራሳቸው ትርጉም አላቸው›› በማለት ገና በ1930ዎቹ ዴሞክራሲ ትርጉም ያጣ፤ ሁሉም በየጓዳው እየመዘዘ የሚጠቀምበት ትርጉም አልባ ቃል እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ለዚህም ይመስላል የፖለቲካ ሳይንቲስቱ Robert Dahl በዴሞክራሲ ፋንታ ‘እውነተኛውን የዲሞክራሲ ትርጓሜ’ ወይም ‘Polyarchyን’ እንጠቀም ዘንድ የሚመክረን፡፡ ዴሞክራሲን እንዲህ ነው ብለን ብይን እንዳንሰጠው በተለያዩ ችሎቶች የተለያዩ ብይኖች ተሰጥተዋል እና ዴሞክራሲ ‘One of the most Misused and Abused term’ ይባል ዘንድ እውነት ሆኗል፡፡ ችግሩም የዴሞክራሲ ስመ ብዙነት፤ የዴሞክራሲ ትርጉመ የትየለሌሽነት ላይ ይወድቃል፡፡
The Ethiopian ‘D’ Syndrome
ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ዋለበትን ጊዜ ይህ ነው ብሎ ለመናገር የጠለቀ ጥናት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ በወጡት ዓለማቀፍ ህጎች እና መርሆች በመንተራስ በፀደቀው የ1955ቱ ሕገ መንግስት ላይ ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሚል ስያሜ የዜጎች መብቶች ተቀምጠው እናገኛለን፡፡ ያም ቢሆን የንጉሱ ስርዓት ራሱን ዴሞክራሲያዊ ብሎ ጠርቶ አያውቅም – ደግ አደረገ፤ ፈላጭ ቆራጭ ነበርና፡፡
የንጉሱ ስርዓት ማብቂያ ላይ ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ‹የመጀመሪያዎቹ› የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ብለው ከመጥራት ይልቅ ሕብረተሰባዊ፣ አብዮታዊ፣ ወ.ዘ.ተ የሚሉ ቃላትን ተመራጭ ያደርጉ ነበር፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆኑን የንጉሱን ስርዓት መገርሰስ ተከትሎ ብልጭ ብላ በነበረችው ‹የነፃነት ጮራ› በመጠቀም እስከ ቀይ ሽብር ማብቂያ ድረስ ለምልመው ከነበሩት ፓርቲዎች ውስጥ የዋነኛዎቹን ስያሜ ብንመለከት፤ የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)፣ አብዮታዊ ሰደድ፣ የወዛደር ሊግ (ወዝሊግ)፣ የኢትዮጵያ ጭቁኖች አብዮታዊ ትግል (ኢጭአት) እና ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሪቮሊሽናዊ ድርጅትን (ማሌሪድ)፤ እንዲሁም እነዚህ አምስት ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱትን የኢትዮጵያ ማርክሳዊ ሌኒናዊ ድርጅቶች ህብረት (ኢማሌዲህ) በአንድ ወገን ስናገኝ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲን (ኢህአፓ)  እናገኛለን፡፡
ከነዚህ ዋነኛ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱም ዴሞክራሲን የስም ማሸብረቂያ ሲያደርጋት አይታይም፤ አልደፈረም፡፡ ደርግ በአፈሙዝ በዙሪያው ያሉትን ፓርቲዎች አንድ ባንድ ካስወገደ በኋላ የወዛደሩን ፓርቲ  የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ኮሚሽን (ኢሰፓኮ) በኋላ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲን (ኢሰፓ) መሰረትኩ አለ፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስም ዴሞክራሲን ተዳፍሮ ለስም መጠሪያነት አላዋለም ነበር፡፡ ነገር ግን ወታደራዊው መንግስት በዙሪያው ነፍጥ ያነገቡ ሀይላት እየገፉ ሲመጡበት እና የምስራቁ ርዕዮተ ዓለም ሲዳከም ተመልክቶ ‹በአዎጅ ሀገር አስተዳድራለሁ› የሚለውን ቀረርቶ በማቆም፤ ለሕዝቡ ‹ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግስት› እነሆ አልኩ ሲል፤ በዛውም የሀገሪቱን ብሄራዊ መጠሪያ ዴሞክራሲ በተባለችው ምትሃተኛ ቃል አስጊጧት ነበር – ‹የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ›፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ግንባር ከጅምሩ ራሱን ዴሞክራሲያዊ ብሎ በመጥራት የፖለቲካውን ገበያ የተቀላቀለ ሲሆን፤ እርሱን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች ውስጥ ከሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) በቀር ሶስቱ ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፣ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ያችን ‹ወርቃማ ቃል› መለያቸው አድርገዋታል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም  በኢህአዴግ አጋርነት ቀሪዎቹን አምስት ክልሎች ከሚያስተዳድሩ ፓርቲዎች ውስጥ ከሀረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሀብሊ) በቀር አፋርን፣ ሶማሌን፣ ጋምቤላን እና ቤንሻንጉል ጉምዝን የሚያስተዳድሩት አጋር ፓርቲዎች ስያሜያቸውን በምትሃተኛዋ ዴሞክራሲ ያደመቁ ሁነው እናገኛቸዋልን፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችንም ‹ዴሞክራሲ› ለተባለው ቃል ያላቸው ፍቅር የበዛ ነው፡፡ ዴሞክራሲን በስያሜነት ያልተጠቀመ የተቃዋሚ ፓርቲ የህዝብን ይሁንታ አያገኝም የተባለ ያክል፤ የተቃዋሚው ሰፈር በዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የዴሞክራሲ ግንባር፣ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ዴሞክራሲያዊ ህብረት ወ.ዘ.ተ በሚሉ የዴሞክራሲ ቅጽል የተዋቡ ናቸው፡፡
ይሄን እይታችንን ወደ ሀገሪቱ መጠሪያነት ስንወስደው ደግሞ፤  የሀገራችን ብሄራዊ መጠሪያ ከዴሞክራሲ ጋር የተፋቀረ ሆኖ እናገኝዋለን፡፡ ወታደራዊው መንግስት አስራ ሶስት ዓመታትን ዘግይቶ ባወጣው ሕገ መንግስቱ ንቆ ትቶት የነበረውን ዴሞክራሲ ለስርዓቱ መጠሪያነት ‹የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ› በማለት አውሎታል፡፡ ወታደራዊውን መንግስት የተካው ኢሕአዴግ በበኩሉ የወታደራዊውን መንግስት ሕገ መንግስት ቀይሮ  ባወጣው አዲስ ሕገ መንግስት ‹የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን› እንደመጠሪያነት ተጠቅሞ በአፍሪካ ራሳቸውን ‹ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ› ብለው ከሚጠሩት ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከአልጀሪያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር በሶስተኝነት ተሰልፏል፡፡ እንግዲህ የሀገሪቱ መጠሪያ ዴሞክራሲያዊ ከተባለ ሩብ ምዕተ ዓመት አስቆጥራለች ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ያንድ ወጣት እድሜ ያስቆጠረው የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ብሄራዊ መጠሪያ እውን መሬት ላይ ያለችውን ኢትዮጵያን ይወክላል ወይ? ትንሹም ትልቁም ‹ዴሞክራሲ› የተሰኝችውን ቃል እየመዘዘ ስሙ ላይ ሲለጥፍ፤ እውን ራሱን ለዴሞክራሲ ፅንሰ ሀሳብ አስገዝቶ ነውን ነውን? ወይስ እንዲሁ ማታለያ ነች? ነው ጥያቄው፡፡
‹‹ዴሞክራሲ ሆይ፣ ዴሞክራሲ ሆይ የሚለኝ ሁሉ…››
አስማተኛው ወይም ሻማኑ ምትሃቱ እውን ይሆን ዘንድ፤ መናፍስቱ ስራቸውን ይጀምሩ ዘንድ በማይገባ ቃል ያነበንባል (‹በልሳን› ይናገራል እንበለው ይሆን?)፤ ይህም ማነብነብ ‘Abracadabra’ ይባላል፡፡ የቃሉ አመጣጥ ከቁምርዓነ ፅሁፎች (The writings of ‘Q’) አንዱ  በሆነውና በSerenus Sammonicus ከተፃፈው ፅሁፍ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሳሞኒከስ ስለዚህ ምስጢራዊ (Cabbalistic) ቃል የአጠቃቀም መመሪያ ያስቀመጠ ሲሆን፤ የማነብነቡ ሚስጥርም መናፍስቱን መጥራት እንጅ ምትሃቱን ማዝነብ አይደለም፤ የምትሃቱ ባለቤቶች መናፍስቶቹ ናቸው፡፡
እኛም ሀገር ዴሞክራሲ ወደ ሳሞኒከሱ ‹አብራካዳብራ› የተቃረበ ነው፡፡ የፖለቲካ አስማተኞቻችን የሳሞኒከስን መመሪያ ተከትለው በሚመስል መልኩ፤ ዴሞክራሲን በፓርቲ መጠሪያነት፤ ዴሞክራሲን በፓርቲ ፕሮግራም አድማቂነት፤ ዴሞክራሲን በሕዝብ ግንኙነት መሪ ቃልነት ይጠቀማሉ ፤ ሕዝቡም እንደመናፍስቱ ወደነሱ ይቀርባል፤ በዙሪያቸውም ይሰበሰባል፤ ያኔ አይኑን ያውሩታል በሕዝቡ ስም ይነግዳሉ፡፡ ይህም ማለት ፖለቲከኞቻችን ዴሞክራሲን እንደ ማር ገምቦ (Honeypot) ይገለገሉባታል እንደማለት ነው፡፡ ህዝቡ ማሩን ፍለጋ በማሩ ዙሪያ ይኮለኮላል፤ ማሩን ግን አያገኝም፡፡
የዘመናዊ ሕገ መንግስታት ፈር ቀዳጅ የሆነው የአሜሪካ ሕገ መንግስት አንድም ቦታ ዴሞክራሲ ወይም ዴሞክራሲያዊ የሚሉ ቃላትን አይጠቀምም፡፡ በተነፃፃሪ ባለፉት 25 ዓመታት ያየናት ኢትዮጵያ  ከሕገ መንግስታቶቿ እስከ ፓርቲ ፕሮግራሞች ድረስ ዴሚክራሲን ያልተጠቀመችበት ቦታ ማግኝት ከባድ ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን ኢትዮጵያ አብዝታ ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ ስላለች አሜሪካ ደግሞ በሕገ መንግስቷ አንድም ቦታ አላስተናገደችውምና፤ ኢትዮጵያ የተሻለች ዴሞክራሲ ናት ማለት በፍፁም አይደለም፡፡ ይልቁንም የህዝቡን ፈቃድ የሚያደርግ እንጅ፤ ዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲ የሚል ሁሉ ዴሞክራሲያዊ አይደለም፡፡
በተኩላው ‹ርዕዮተ ዓለም›  የተበላው፤ በጉ ዲሞክራሲ
በቅርብ ዓመታት ታሪካችን ውስጥ ያስተዋልነው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ የዴሞክራሲና የገላጭ ቅፅልን ጋብቻ ነው፡፡ ዴሞክራሲ ብቻውን መቆም አይችልም በሚል ሀሳብ ከፖለቲከኞች እስከ ምሁራን ድረስ የመረጡትን ወይ የሚተነትኑትን ዴሞክራሲ ለማስረዳት በቅፅል ያደምቁታል፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ሊብራል ዴሞክራሲ፣ ሶሻል ዴሞክራሲ፣ ሕዝባዊ ዴሞክራሲ፣ የድርድር ዴሞክራሲ ወ.ዘ.ተ እያሉ የሚቀጥሉ የዴሞክራሲ ክምር እናያለን፡፡ ዴሞክራሲ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ በገላጭ ቃል በማጀብ ለመግልፅ እየተሞከረ ነው ማለት ነው፤ ‹እኔ ከ እገሌ የምለየው በያዝኩት ልዩ ቅጽል› ነው ብሎ እንደመከራከር ማለት ነው፡፡
እንግዲህ ዴሞክራሲ በራሱ እንዳይቆም ሁሉም የራሱን ትርጉም በመስጠት ትርገም አልባ አድርጎታል ካልን ዘንድ፤ ቅፅል እየጨመሩ ማብራራቱ ባልከፋ ነበር፤ ነገር ግን ባለው ተሞክሮ በሀገራችን ዴሞክራሲ በቅጽል ሲታጀብ የሃሳቡ ባለቤት ግለሰብ ወይም ፓርቲ ቅፅሉን ለማግዘፍ ያደረገው እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ራሳቸውን ‹አብዮታዊ ዴሞክራት› ብለው ሲጠሩ ‹አብዮተኞች ነን› ማለታቸው ሆኖ እናገኝዋለን፤ ‹ሶሻል ዴሞክራት ነን› ሲሉ፤ ‹ረጅም የመንግስትን እጅ (Big Government) በኢኮኖሚው ውስጥ ማየት እንፈልጋለን› ማለታቸው ሆኖ ይታያል፤ ‹ሊብራል ዴሞክራቶች ነን› ሲሉ ደግሞ፤ ‹መንግስት እጁን ሰብስቦ ይቀመጥ› ማለታቸው ሆኖ እናገኝዋለን፡፡ በዚህ መሃል ዴሞክራሲ የተባለችውን ቃል ርዕዮተ ዓለም የተባለ አቧራ ሸፍኗት እናገኛታለን፡፡ እንግዲህ ዴሞክራሲን ከአቧራው መሃል አውጥቶ በዙፋኗ ማስቀመጥ ነው ተስፋ የሚደረገው የድኸነት መንገድ፡፡ ከአቧራው መሃል ማን ያወጣታል? ለሚለው ጥያቄ፤ ማን ሊያወጣት አይችልም?  ለሚለው ጥያቄ ዊንስተን ቸርችል “Democracy is no harlot to be picked up in the street by a man with a tommy gun” ያለውን ሀሳብ እንደመልስ ብንወስድስ?

አንድነት ፓርቲ “ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው!”

June 15, 2013
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
ከአአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች፤ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ለብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች የተጋለጠች አገር ናት፡፡ በአንፃራዊነት ሲታይም ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ብትሆንም ዜጎቿ በርሃብ የሚሰቃዩባት፤ ከሞት ጋር ተጋፍጠው ስደትን የሚመርጡባት፤ በሙስና ተግጣ ያለቀች፣ መልካም አስተዳደር የናፈቃት የምታስቆጭ ሀገርም ናት፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ከራሱ ስልጣን ይልቅ የህዝብን ጥቅም የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ አግኝታ አታውቅም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ሉዓላዊነቱን ለማንምና ለምንም ሰጥቶ አያውቅም፣ ወደፊትም ሊሰጥ አይችልም፡፡ ይህም ስለሆነ ሀገራችን ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ ዓመታት ቆይታለች፡፡
ከዚህ በፊትም አቶማን ቱርኮች፣ ግብፆች፣ ድርቡሾች፣ ጣሊያኖችና ሶማሊያ ባደረጉት የሉዓላዊነት መድፈር የጨቋኞችን ክፉ ድርጊት ወደ ጎን በማለት፣ ‹‹ጨቋኝ ገዢዎች እንጂ ሀገሬ አይደለችም›› በሚል እሳቤ ደሙን አፍስሷል፡፡ አጥንቱን ከስክሷል፡፡ ለባለፉት ሃያ ሁለት አመታት ግን ብሔርንና ጎሳን መሰረት ባደረገው ከፋፋይ ሥርዓት ኢትዮጵያዊ አንድነትን በማደብዘዝና የጋራ ህብረ ቀለምና እሴቶችን ወደ ቡድን ህብረ ቀለምና እሴት በመቀየር፣ ተከብሮና ታፍሮ የኖረ ሉዓላዊነታችንን ከግራና ከቀኝ እንዲቆረስ በማድረጉ ከቀደሙት አገዛዞች ለየት ያደርገዋል፡፡
በተጨማሪም ይሄን ሥርዓት ከሌሎች የቀደሙ አምባገነን ሥርዓቶች ለየት የሚያደርገው ‹‹ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ሥልጣን መጠቀሚያ ማዋል›› የሚለው ተግባሩ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የአንድ መንግሥት ግዴታዎች የሆኑት ተግባራት መንገድ፣ መብራት፣ ውሃ፣ ቤት የመሳሰሉት መዳረሻቸው የፖለቲካ ሥልጣንን ማራዘም ነው፡፡ እነዚህንም ስለሞከረ አመስግኑኝ፣ ዘምሩልኝ የሚል መንግሥት የኢህአዴግ መንግሥት ብቻ ነው፡፡ በመሰረቱ መንግሥት አይመሰገንም፡፡ በሰለጠኑት እና እድለኛ በሆኑት ሀገሮች ህዝቡ መንግሥቱን እንዳመሰገነ የሚቆጠረው የምርጫ ካርዱን ሲሰጠው ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ያለው የመንግሥት ግዴታ ነው፡፡
ፓርቲያችን አጥብቆ እንደሚያምነው ለፖለቲካ ፍጆታ የማይውል ንፁህ ልማት እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ለፖለቲካ መጠቀሚያ የማይውል የመሠረተ ልማት ግንባታ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ትላልቅ ግድቦችን መገንባት፣ ለመስኖና ለተለያዩ ጉዳዮች መጠቀም እንደ ኢትዮጵያ በርካታ ህዝብ ላለው ሀገር አስፈላጊነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ኢህአዴግ እንዳዲስ ያነሳው በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ መስራትና የማልማት አስፈላጊነት ለዘመናት ሲነሳ የነበረ ጉዳይ ነው፡፡
አንድነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም ተፈጥሮአዊና መብት እንዳለውና ይሄ የኢትዮጵያውያን መብት ለማንም ተላልፎ የሚሰጥ እንዳልሆነ በጽኑ ያምናል፡፡ በአባይ ላይ በፍትሓዊነት የመጠቀም መብት ከፓርቲዎች ወይም ገዢ ከሆነው ፓርቲ ለህዝቡ የሚሰጥ ሳይሆን የህዝቡና የህዝቡ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው ችግሩ የሚመነጨው ገዥው ፓርቲ አባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመስራት መነሳቱ ሳይሆን የአባይን ጉዳይ የኢህአዴግ ጉዳይ ማድረጉ፣ የአባይን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ ራዕይ ማድረጉና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ቦንድ እየገዛ ያለውን ህዝብ የግድቡ ባለቤት ማድረግ አለመቻሉ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን ግድቡ በጊዜያዊነት አቅጣጫ እንዲቀይር የተደረገበትን ቀን ከግንቦት ሃያ በዓላቸው ጋር ሆን ብለው ለማገጣጠም መፈለጋቸው ነው፡፡ ግድቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ግድብ ይሁን የኢህአዴግ በውል አልለዩትም፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የፖለቲካ መጠቀሚያ ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአባይ ላይ ግድብ ከመሰራቱ በፊት ማለቅ የሚገባቸው የዲፕሎማሲ ስራዎችና ሌሎች ጉዳዮች በውል ታይተዋል ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳትም ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ግድቡ ላይ ከእያንዳንዱ ኪስ የተወሰደ ገንዘብ አለና ነው፡፡
ስለዚህ ገዢው ፓርቲ ሁሉን ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ በማዋል ሥልጣንን ማስረዘም በሚል መርህ ተቀይዶ የዘነጋቸው ብዙ ሀገራዊ ተግባራት እንደነበሩና እንዳሉ ለመገመት ይቻላል፡፡ ከነዚህም ዋነኛው በቂ የዲፕሎማሲ ስራ አለመስራት፤ ከዓባይ ተጋሪ ሀገሮች ጋር በቂና አስተማማኝ ውይይት አድርጎ ስምምነት አለመድረስ፤ በዚህ ረገድ ሀገሪቱ የጦርነት ስጋር ቢገጥማት ለመቋቋም በቂ ዝግጅት አለማድረግ፤ የገንዘብ ቁጥጥርና ሙስና የመሳሳሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ሌላው አብይ ጉዳይ ሁሉም ነገር እኔ አውቀዋለሁ በሚል ትእቢት ኢህአዴግ ብሔራዊ መግባባት (National Consensus) እንዲፈጠር ምንም አይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ አለመፈለጉ ነው፡፡ ይልቁንም ገዢው አካል ብሔራዊ መግባባት እንዳይፈጠር በመስራት የሚታወቅት ነው፡፡ ሀገራዊ ጉዳይ ያነሱ ፖለቲካኞችንና ጋዜጠኞችንና ባዘጋጀው የማጥቂያ ህግ ‹‹ሽብርተኛ›› በማለት የሚፈርጅ፣ ለመነጋገርና ለመግባባት ዝግጁነት የሌለው፣ በልማት ስም ጭቆና የሚያካሂድ፣ ይቀናቀነኛል የሚላቸውን ኃይሎች ሁሉ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለባቸው ብሎ የሚያስብ አምባገነን ሥርዓት ነው፡፡ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ብሔራዊ መግባባትን የሚፈታተን በማጥቃት ላይ ብቻ የተመሰረተ አገዛዝ ነው፡፡ ስለዚህ አጣብቂኝ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ እንኳን ሀገራዊ አጀንዳ ካላቸው ተቃዋሚዎች ጋር የመመካከር ሃሳብ የለውም፡፡ ይሄም የሆነው ከሀገር ይልቅ ስልጣንንና ለስልጣን ብቻ ከማሰብ የሚመነጭ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ የታቀደው ትልቅ ፕሮጀክት ያለ ሀገራዊ መግባባት እንዴት ሊሳካ ይችላል?
ከተመረጡ አንድ ዓመት የሚሆናቸው የግብፁ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ያቀረቡት ሃሳብ ቅቡልም ሆነ የማይረባ ከተቃዋሚዎች ጋር ተነጋግረዋል፤ የሱዳን መንግሥት የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት የተሻለ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር እየጣረ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በግትርነት ማሰርና መፈረጁን በመቀጠል የሀገራዊ መግባባት አደጋ እየሆነ ይገኛል፡፡ በሀገራችን ያሉ ችግሮችን ተነጋግሮ ለመፍታት ፈቃደኛም፣ ቁርጠኛም አይደለም ስለዚህ ራሱ መንግሥት ተጠያቂ የሚሆንበት ጉዳይ ብዙ ነው፡፡
በመዚህም መሠረት የአንድነት አቋም የሚከተለው ነው፡-
1. የግብጽና የኢትዮጵያ መንግሥት ከፀብ አጫሪ ድርጊት በመቆጠብ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ከሚያበላሹ ፕሮፓጋንዳዎችን ከመንዛት እንዲታቀቡና ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጠረጴዛ ዙሪያ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩ እናሳስባለን፤
2. አባይን መጠቀም የኢትዮጵያ ተፈጥሮዊ መብት መሆኑ እንዲታወቅ፣
3. ሁለቱ ሀገሮች የአባይን ጉዳይ የውስጥ ፖለቲካቸው ማብረጃ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣
4. ሀገራዊ መግባባት አሁኑኑ እንዲፈጠር መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣
5. የአባይ ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ መሆኑ እንዲያበቃ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 6 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ለዶ/ር መራራ”ነፃነት በጨቋኞች መልካም ፈቃድ የሚሰጥ ሳይሆን በተጨቆኑ ህዝቦች ትግል የሚገኝ ዉጤት ነዉ!”

June 15, 2013
ከአዳነ ምስጉን
በቅርቡ ከ 8 አመት በኋላ በሰማያዊ ፓርቲ አነሳሽነት በከተማችን በአዱ -ገነት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል።Dr. Merera Gudina Ethiopian politician
መንግስት ተብዬዉ ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ የፈቀደዉ ፈልጎት አይደለም ተገዶ እንጂ!
መንግስት የህዝቡንና የፓርቲውን አመራሮች ቁርጠኝነት ስለተገነዘበ ሰልፉን ፈቅዷል።አለቀ-ደቀቀ!
ሆኖም በቅርቡ በፌስ ቡክ ላይ ዶ/ር መራራ ጉዲና “ቆይ ለእኛ እንቢ የተባለዉ ሰልፍ እንዴት ለሠማያዊ ፓርቲ ተፈቀደ?” ሲሉ ተደምጠዋል።
እኔ ዶ/ር መራራን የመሳደብ ሞራሉም ሆነ ድፍረቱ የለኝም። በትምህርትም፣ በእድሜም ሆነ በልምድ እጅግ ይበልጡኛል። ነገር ግን የትንሽነቴን ሁለት አስተያየቶቼን ልስጣቸዉ።
1ኛ-እየፈሩ ትግል የትም አያደርስም። ይልቁንስ ምስኪኑን ወገኔን ያስጨርሱታል። ስለሆነም ቆራጥ ይሁኑ እንደ ሠማያዊ ፓርቲ አመራሮች።
2ኛ-አብሮ ስለመስራት ያስቡ። ሠማያዊ ፓርቲ እንዴት ተፈቀደለት ብለዉ ከሚጨናነቁ ከ90 ቀን በኋላ ለሚኖረዉ ሰልፍ ተዘጋጁ፣ ተነጋገሩ!
በመጨረሻም ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳለዉ “ነፃነት በጨቋኞች መልካም ፈቃድ የሚሰጥ ሳይሆን በተጨቆኑ ህዝቦች ትግል የሚገኝ ዉጤት ነዉ!” እግዛብሔር ድፍረቱን ይስጥዎት አሜን።

ይድረስ ለአለምነህ ዋሴ፣ የአሜሪካ « ሰይጣን» በአገራችን?

June 18, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያዬ ወጥቼ ጥቂት እንደተጓዝኩ ሁለት አሜሪካዊያን ወጣቶች ከፊት ለፊቴ ሲመጡ ተመለከትኩ። እጅ ለእጅ ተያይዘዋል…በጥንቃቄ ምስላቸውን ለማስቀረት ሞከርኩ።… ( ወንድ ከወንድ- ሴት ከሴት፣ እጅ – ለእጅ መያያዝና መተቃቀፍ ግብረ-ሰዶማዊነትን ያመለክታል በአሜሪካ)… ታዲያ ምንድነው?.. ትለኝ ይሆናል፤… ይህ «ሰይጣናዊ» የነአሜሪካ «ቁሻሻ» በአገራችን መስፋፋቱ አሳስቦኝ ነው። የ11 እና 10 አመት ታዳጊ ሕፃናት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ ት/ቤት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 6 አስተማሪዎች እየተፈራረቁ «ሰይጣናዊ» ድርጊት ሲፈፅሙ እንደከረሙ መስማት አያስጨንቅም?… ለትምህርት የላከው ልጅህ ያውም በአስተማሪዎች እንዲህ አይነቱ ርካሽ ተግባር ሲፈፀምበት ምን ይሰማኻል?… «14ሺህ ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጲያ አሉ» ተብሎ በአንድ ወቅት የተነገረውን ስትሰማ ምን አልክ?…ምነው ቤቲ ላይ በረታህ?… እርግጥ ነው ቤቲ የሰራችው ከአገራችን ባህል ጋር የሚጣረስ ነው!! ይህ አያከራክርም። ግን ቤቲ አረብ አገር እንደሚሰቃዩት እህቶቻችን እጣ ቢገጥማት… ይህን ያክል ትጮህላት ነበር?… በቅርቡ አረብ አገር ቁልቁል ተዘቅዝቃ ደም እየተፋች ስትገረፍ የነበረችው (ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ለጥፎት ነበር) እህታችን ሰቆቃ የሚሳየውን ቪዲዮ አይተኸዋል?… እንኳን ልታየው ከቁም ነገር ከተኸዋል?… ከ10 አመት በፊት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በአዲስ አበባ ያለውን ሁኔታ ሲገልፁ «ሶስት መቶ ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ አሉ» ብለው ነበር። ማን የፈጠረው ችግር ነው?… ቤቲ የዚሁ አካል አይደለችም?… ሌሎቹ አደባባይ ስላልወጡ ነው?… ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ፥ የምታገለግለው ስርአት ይህን ሁሉ ችግር እንደፈጠረ ጠፍቶህ አይደለም። በስደት ስለሚያልቁትና ስለሚሰቃዩት እህትና ወንድሞቻችን አንድም ቀን ትንፍሽ ሳትል… ቤቲ ላይ ዘመትክባት። ሃቁ ግን የኢኮኖሚ ድቀት የፈጠረው ነው!!… ስለ «ሰይጣናዊው» አደገኛ የባህል ወረርሽኝ ትንፍሽ አላልክም። ለምን?… ወገኖቼ የቱ ያስጨንቃል?…

ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንና የዘረኛው ወያኔ ሹመኞች

June 19, 2013

በሰው ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ የክርስቲያን ሥራ እየሰራሁ ነው ማለት አይቻለም።
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።
በ09/06/2013 በዕለተ እሑድ ለንደን በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርና ሹማምንቶች የሚቀጥለውን ማስታወቂያ ለሕዝቡ አስተላልፈዋል።
  1. በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሦስት ወራት መዘጋቷን፤
  2. ለብጥብጡና ለችግሩ መንስዔ የሆነው ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ በሚገኘው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ባለመመራቷ መሆኑን፤
  3. ቤተ ክርስቲያኗ ላለፉት 7 ዓመታት ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ ብቻዋን ስትንከራተት ከቆየች በኋላ አሁን ተመልሳ መቀላቀሏን። (ማስታወቂያው ከተነገረ በኋላ እንደ ተለመደው ሕዝቡ የሚጠበቅበትን ጭብጨባና እልልታ እንዲያሰማ ተደረገ)
  4. ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ችግር መንስዔ የሆነው ጉዳይ እልባት ሊያገኝ የቻለው ከቅዱስ ሲኖዶስ ተልከው በመጡት በሊቃነ ጳጳሳቱ መሆኑንና የሰጡት መፍትሔም ቤተ ክርስቲያኗ በአቡነ እንጦስና በመጋቢ ተወልደ በሚመራው የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ሥር እንድትደዳደር መመሪያ ሰጥተው ወደ ኢትዮጵያ መለሳቸው ነው በማለት አብራርተዋል።
በመጨረሻም ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሃገረ ስብከቱ ሥር እስከሆነች ድረስ ማንኛቸውም ምእመን በቤተ ክርስቲያኗ የመገልገል መብት ስላለው ቤተ ክርስቲያኗ ባስቸኳይ ተከፍታ አገልግሎቷን እንድትሰጥ ሕዝቡ ማመልከቻ (Petition) ላይ እንዲፈርም የተደረገ ሲሆን በገብረኤል ቤተ ክርስቲያንም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደተፈጸመ ለማወቅ ተችሏል።
ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡
  1. ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሃገረ እንግሊዝ ከተመሠረተች ከ40 ዓመታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ አታውቅም፤ አሁን የተፈጠረውም ችግር በቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ትሁን አትሁን ከሚለው ጥያቄ ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም።በእርግጥ ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ሆና ብትቆይም ቤተ ክርስቲያኗ በውጪ ሃገር የምትገኝ በመሆኗ እና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተፈጠረው ችግርና መከፋፈል የተነሳ ከአንድም ሁለትና ሦስት ጊዜ በአባ ጳውሎስ አማካኝነት ከኢትዮጵያ ተልከው በመጡ እንደ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ፤ አቡነ ኢሳያስና በመጨረሻም በአቡነ ሙሴ አማካኝነት ተደጋጋሚ ችግር ስለደረሰባት የተፈጸመባት ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ሳታቋርጥ አስተዳደሯንና ንብረቷን በተመለከተ ግን ቃለ ዓዋዲውን መሠረት በማድረግ  በUK የቻሪቲ ሕግ መሠረት ራሷን ችላ ስትተዳደር ቆይታለች። ይህንን አቋሟን ልለውጥ፤ ወይም ላሻሽል ብሎ የተነሳ ክርክርም ሆነ ጸብ የለም።
  2. ከዚሁ ጋር ቤተ ክርስቲያኗ አሁን በህይወት የሌሉት አባ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያኗም ላይ ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱትን በደልና ግፍ ከግምት ውስጥ በማስገባት ስማቸውን ቅዱስ ብሎ ላለመጥራትና አመራራቸውንም ላለመቀበል የጠራ አቋም በመያዝ በዛ አቋም መሠረት ስትመራ
ከ7 ዓመት በፊት አቡነ እንጦስ ቤተ ክርስቲያኗን መንበሬ እንዳደርግ በአባ ጳውሎስ ተሹሜአለሁ ብለው በመጡበት ወቅት የቤተ ክርስቲያኗን አቋም ተቀብለው እንዲያገለግሉ ሲጠየቁ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም አልቀበልም በማለታቸውና የአባ ጳውሎስንም ሥም ካልጠራሁ ላገለግል አልችልም በማለታቸው ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ሳይመጡ ቀርተዋል። “ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጥላ ለ7 ዓመት ስትንከራተት ነበር” በማለት በስላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አማካኝነት ለሕዝቡ የተላለፈው መልዕክት ከአቡነ እንጦስ ተነጥላ በሚል ቢታረም ምናልባት ከእውነት ጋር ሊገናኝ ይችል ይሆናል እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ የተነጠለችበት ወቅትና ጊዜ የለም።
  1.  ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አቋሟንና አሰራሯን በማጥራት  አገልግሎቷ ሰፍቶና ተጠናክሮ ዕድገቷ በመፋጠኑ የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ለመግዛት ጥረት በተጀመረበት ወቅት በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ቂምን የቋጠሩት አባ ጳውሎስ ሕዝበ ክርስቲያኑ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገዛ ለማሰናከል ለAnglican Church ደብዳቤ በመጻፍ የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ለስደተኛው ኢትዮጵያዊ እንዳይሸጥ ተቃውሞ አቀረቡ። ያም ሆኖ ግን ሰው ሳይሆን ፈጻሚው እግዚአብሔር ነውና የአባ ጳውሎስ የጭካኔና የተንኮል ተግባር ከሽፎ በታላቅ ርብርቦሽ የቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ ከነ መኖሪያ ቤቱ ሊገዛ ችሏል።
በዚህ አሳዛኝ ተግባር እንኳ ሕዝበ ክርስቲያኑ በአባ ጳውሎስ ላይ እሮሮውን አሰማ እንጂ ኢትዮጵያ ካለው ቅዱስ ሲኖዶስ እንለይ፤ ወይም እንገንጠል የሚል ጥያቄ አላነሳም፤ ከዛም በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ፀብና ክርክር አንስቶ አያውቅም።
በአሁኑ ወቅት ግን ስላሴ ቤተ ክርስቲያንን በር እረጋጣችሁ ብለው ካህናትን የሚያባርሩትና የሚያግዱት፤ ምእመናንን ስላሴ አትሂዱ በማለት ሲያስፈራሩና ሲያስጠነቅቁ የነበሩት፤ በኢትዮጵያ ባለው ሲኖዶስ ላይ መግለጫና ማስጠንቀቂያ ሲያዘንቡ የነበሩት አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ደጋፊዎች ነን ብለው በመነሳት ሌላው ሕዝብ ኢትዮጵያ ያለውን ሲኖዶስ ተቃዋሚ አድርገው በማቅረብ የችግሩ መነሻም ሆነ ነድረሻ የሲኖዶስ ጉዳይ ነው የሚል አዲስ የቲያትር ደርሰው በተዋናኝነት ሲቀርቡ  ይህ ጉዳይ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ እንደሆነ የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አባላትና ሹማምንቶች በሚገባ እያወቁ ሕዝብን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በሚወስድ መልኩ ማቅረባቸው በእጅጉ ያሳዝናል፤ ያስተዛዝባል።
  1. ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በያዘችው የጠራ አቋም በመጽናት ያለማንም የፓለቲካና የመንግሥት ጣልቃ ገብነት በነፃነት በመመራት ቀጥሎ የተመለከቱትን ተግባራት ታከናውን ነበር እንጂ ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለይታ ስንትከራተት የኖረች አይደለችም።
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ህጻናት፤ ጎልማሶችና አሮጊትና ሽማግሌዎች በመንግሥት ወታደርና የደህንነት ኃይል በግፍ ሲጨፈጨፉ አባ ጳውሎስ ግፍ የተፈጸመበትን ሕዝብ ትተው ለአገዛዝ ሥርዓቱ በመወገን መንፈሳዊነታቸውን ትተው ከፓሊተከኞቹ ብሰው በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን ለሞቱት ሰዎች ጸሎት እንዳይደረግላቸው ሲያግዱ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ግን ክርስቲያናዊ ያልሆነውን የአባ ጳውሎስን ማገጃ በመጣስ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች ሙሉ ጸሎት አካሂዳለች።  (ይህም በመፈጸሙ ለሞቱት ኢትዮጵያኖች ጸሎት መደረግ የለበትም የሚሉ ካህናት ከቤተ ክርስቲያኗ ተነጥለው ነው ዛሬ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሥርተው የሚገኙት)
  • ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሕግ የበላይነት፤ ፍትሕና ነጻነት በሰፈነበት ሀገር የምትገኝ በመሆኗ በኢትዮጵያም ውስጥ ሆነ በሌላው ዓለም በክርስቲያኖችና በመላው ሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፤ ግፍና በደል ሁሉ እንደ ቤተ ክርስቲያን በነፃነት በመቃወምና በማወገዝ የድርሻዋን ስትወጣ ኖራለች፡፤
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ገዳማት ሲጠቁና ሲቃጠሉ ቤተ ክርስቲያኗ ማንኛቸውም መንግሥትና የፓለቲካ ተቋም ጫና ሳይገድባት የተቃውሞ ድምጿን ከፍ አድርጋ አሰምታለች፤ አቅም በፈቀደም ለተጎዱትና ለተጎሳቆሉት ገዳሞችና ቤተ ክርስቲያናት ያለመንግሥት ተጽዕኖና ጣልቃ ገብነት በነጻነት እርዳታና ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች፤
  • በቅርቡ ዋልድባ ገዳም ለሸንኮራ አገዳ ተክል ተብሎ ታሪካዊ ቦታዎች ሲፈርሱ መቃብራት ሲታረሱ፤ መነኮሳት ሲበደሉና ሲሳደዱ ከሲኖዶስ ጀምሮ ወደ ታች ያለው በመንግሥት ተጽዕኖ አፉ ተለጉሞ፤ እግሩና እጁ ታስሮ ሲቀመጥ ሌላው ቀርቶ በዚህ በምንኖርበት በነፃነት ሃገር የሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ ራሳቸውን ከመንግሥት መዋቅር ጋር በማያያዝ በሃይማኖታቸውና በቤተ ክርስቲያናቸው ላይ የሚደርሰውን ጥቃቅ በጸጋ ለመቀበል ሲገደዱ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግን በዓለም ተዋዊ በሆነው በእንግሊዝ ፓርላማ ፊት በመውጣት የተቃውሞ ድምጿን አሰምታለች።
በዚህ መሠረት ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ሁሉ የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለሕዝብ ከገለጸው ማስታወቂያ ውስጥ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ወር መዘጋት ካልሆነ በስተቀር የተቀረው በሙሉ ሃሰትና ሕዝብን አሳስቶ በፓለቲካ መሣሪያነት ለመጠቀም ሆነ ብሎ የተቀነባበረ የቅስቀሳና የፕሮፓጋንዳ ተግባር ብቻ መሆኑን ልትገነዘቡት ይገባል።
በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠርውን ችገር ለመፍታት ወይም ለማስታረቅ ከኢትዮጵ መጡ የተባሉት ሊቃነ ጳጳሳት ስብስበው ያነጋገሩትና የሥላሴ፤ የገብረኤልና የጸራጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላትን እና ከለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አባ ግርማንና ደጋፊዎቻቸውን ብቻ ሲሆን ያደረጓቸው ሁሉም ስብሰባዎቻቸው ደግሞ ምእመኑ ተሰብስቦ
  • የሊቃነ ጳጳሳቱን ትምሕርትና መግለጫ ያዳመጠበት፤
  • ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር እንድትሆንና አስተዳደሯም ሆነ ሃብትና ንብረቷ በሃገረ ስብከቱ ስር ሆኖ አቡነ እንጦስ መንበራቸው በቤተ ክርስቲያኗ እንዲሆን ካህናቱ ተስማምተው መፈራረማቸውን፤ ሲገልጹ እልልታና ጭብጨባውን የለገሰበት፤
  •  አባ ግርማ ከበደ የማይወክሉትን ሕዝብ እወክላለሁ፤ የሌለውን የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አለ በማለት የስላሴንና የገብረኤልን አብያተ ክርስቲያናት አባላት የውሸት ይቅርታ የሚጠይቁበትን ዲስኩር በመስማት፤ እልልታና ጭብጨባውን ያሰማበት ብቻ ነበር እንጂ ሃሳብና አስተያየቱን የሚሰጥበት ወይም ውሳኔ የሚያስተላልፍበት አልነበረም።
ሊቃነ ጳጳሳቱ አባ ግርማ በሕዝበ ውሳኔ ከሥልጣናቸው መውረዳቸውንና የተቀሩት ሁለት የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ካህናት ማሟያ ተመርጦላቸው አብረው እንዲሰሩ ቢጠየቁ አሻፈረኝ በማለታቸው የቤተ ክርስቲያኗ አባላት የሰበካ መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ከካህናት፤ ከምእመናንና ከሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የተውጣጣ አዲስ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ መርጠው መሰየማቸውን ተገቢው ገለጻ በተደረገላቸው ወቅት የሰጡት ጠንካራ ምላሽ “ከቤተ ክርስቲያን ሕግ አኳያ ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ከቤተ ክርስቲያኑ ውጪ የተደረገው ምርጫ ሁሉ ምንም ዓይነት ሕጋዊነት የለውም” የሚል ነበር።
ይህንን ቃል ካረጋገጡና ካስረዱ በኋላ ግን ሊቃነ ጳጳሳቱ ራሳቸው ከአባ ግርማና ደጋፊዎቻቸው በስተቀር የተቀረው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን  ቤተ ክርስቲያን አባላት ባልተገኙበት ከቤተ ክርስቲያኗ ውጪ ጉባኤ በማካሄድ ይባስ ብለው ለደረሰው ችግር ሁሉ ዋናው መንስዔና የችግሩ ሁሉ ዋና ተጠያቂ አባ ግርማንና ሌሎች የአባ ግርማን ሥልጣን ያጠናክራሉ ያሏቸውን ሰዎች ሥራቸውን በለቀቁት የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ምትክ በመሾም ቤተ ክርስቲያኗን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው ለሀገረ ስብከቱ እንዲያስረክቡ መመሪያ ሰጥተል።
ይህንን ሹመትና ድልድላቸውን ለማጠናከርና የአባ ግርማና ደጋፊዎቻቸውን ተግባር የተቃና ለማድረግ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሁንም አብዛኛው የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ባልተገኙበት በገዛ ፍቃዳቸው ሥራቸውን ለለቀቁት ምእመናን የሰባካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የቤተ ክርስቲያኗን ምሥል የያዘ ፎቶ ግራፍና ምሥክር ወረቀት ሸልመዋል።
ከላይ የተጠቀሰውን ድርጊት ነው የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሊቃነ ጳጳሳቱ ተልዕኮ ስኬትና የማርያም ቤተ ክርስቲያንም ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመፍታት ዜና አድርጎ ያቀረበው።
የማርያም ቤተ ክርስቲያን ችግር ቢፈታና ቤተ ክርስቲያኗ ተከፍታ አገልግሎቷን ብትጀምር ከሁሉም በላይ የቤተ ክርስቲያኗን አባላት የሚያስደስት በመሆኑ ማስታወቂያው እውነትነት ቢኖረው ምንም ባላነጋገረ። ነገር ግን ማርያም በተዘጋችና አባላቷም ባዘኑና በተንገላቱ የቤተ ክርስቲያኗን ችግር መጠቀሚያ አድርጎ የራስን ዓላማና ምኞት ማሳኪያ አድርጎ ለመጠቀም መሞከር በቁስል ላይ ጨው እንደመነስነስ ይቆጠራል።
ሌላው ሊቃነ ጳጳሳቱ ከላይ የተዘረዘርውን ተግባር ሲያከናውኑ፡
  1. አባ ግርማ ከበደና የእሳቸው ተከታይ የሆኑትን ጥቂት ካህናትና ምእመናንን ከማየትና ከመቅረብ በስተቀር  ከዛ ውጪ ያለውን አብዛኛውን የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን አባላት ስብስቡልንና ችግሩ ምን እንደሆነ ከሁለቱም ወገን እንስማ የሚል ጥያቄ ቀርቶ ዝንባሌም አሳይተው አያውቁም፤
  2. ለሕዝቡ የስብሰባ ጥሪ በሚደረግበት ወቅት የተጣላ ባልና ሚስትን ለማስታረቅ ባልና ሚስቱን ትቶ ጎረቤቱን ሁሉ ሰብስቦ ከማነጋገር ጋር በተመሳሰለ ሁኔታ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት በሚል የሚጠሩት የሌሎች አብያተ ክርስቲያናት አባላትን በመሆኑ፤ ችግሩን ለማወቅም ሆነ ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል አንዳችም ሁኔታ አልተፈጠረም ነበር።
  3. ሊቃነ ጳጳሳቱ ባደረጓቸው ጉባኤዎች ሁሉ የነሱንም ሆነ የካህናቱን ውሳኔና መግለጫ እያሰሙ ሕዝቡ ጉዳዩ ይግባውም አይግባው መብቱና ድርሻው እልልታ ማሰማትና በእጁ ማጨብጨብ ብቻ ስለሆነ በየትኛውም ስብሰባ ላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ የተወያየበት ወይም ጠይቆ የተረዳበት አንዳችም ጊዜ አልነበረም እንዲኖርም አላደረጉም።
ይህ ሁሉ የሚደረገው አሰራሩም ሆነ እውነታው ሳይታወቅ ቀርቶ ሳይሆን ከኢትዮጵያ የመጡት ሁለት ሊቃነ ጳጳሳትና ለንደን የሚገኙት የሃገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳስ ዓላማቸው ቤተ ክርስቲያኗ ከችግሯ ተላቅቃ መልሳ በሁለት እግሯ ሳትቆምና ሳትጠናከር አስተዳደሯንም ሆነ ሃብትና ንብረቷን የ”ሰሜን ምዕራብ አውሮፓ” ተብሎ በተቋቋመው ሃገረ ስብከት ስር ማዋል አለብን የሚለውን ዕቅድ ማራመድ ስላለባቸው ብቻ ነው።
ይህንን ለማስፈጸም የሚቻለው ደግም ቤተ ክርስቲያኗ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር እስከምትውል ድረስ በአሁኑ ወቅት በዋና መሣሪያነት ሊጠቅሙ የሚችሉትን አባ ግርማንና ጥቂት ተከታዮቻቸውን በማጠናከር እነሱን ግንባር ቀደም ተፋላሚ አድርጎ ከነሱ ኋላ ሆኖ በመሥራት ነው።
እዚህ ላይ ከኢትዮጵያ የመጡት ሊቃነ ጳጳሳት አባ ግርማ ከበደ እንዴት ለችግሩ መንስዔና ተጠያቂ እንደሆኑ፤ እሳቸው በአስተዳደር ሥልጣን ላይ እያሉም ችግሩ ሊፈታ እንደማይችል በተጨባጭ ማስረጃ ሲገለጽላቸው ጉዳዩን አምነው በመቀበል መፍትሔውም አባ ግርማንና መሰሎቻቸውን ከቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ማንሳት እንደሆነ በሚገባ ተረድተው ከወሰኑ በኋላ መልሰው ሲገመግሙት ግን የሃገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የበላይ ተቆጣጣሪ አድርጎ ለማስቀመጥ አስተማማኝ መንገድ መስሎ ስላልታያቸው አባ ግርማንና ተከታዮቻቸውን ሥልጣን አጠናክሮ በማቆም በዛ መሸጋገሪያነት ቤተ ክርስቲያኗን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ይቻላል በሚለው ስልት በመለወጥ ምንም ዓይነት ሕጋዊነት የሌለው ሹመትና የስራ ድልድል አድርገው ችግሩ ጭራሽ ወደ ባሰና ወደ ከፋ ደረጃ የሚሸጋገርበትን የችግር ቦይ ቀደው ሊሄዱ ችለዋል።
የስላሴና የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን አባላት በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነታቸው ከዛም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይነታቸውና በአንዲት የስደት ሀገር የሚገኙ በመሆናቸው ግዙፍ በሆነ አንድነት፤ በወንድምነት፤ በእህትነት፤ በአባትና ልጅነት የሚተያዩ ናቸው እንጂ የፓለቲካና የጎሳ ዘይቤ የተጠናወታቸው ጥቂት አመራሮች በፈጠሯት ጥፍጥሬ በምታክል የአቋም ልዩነት በጠላትነት ሊተያዩ የሚችሉ አይደሉም።
ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡ በማርያም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ችግር መነሻው ውሸት ነው፤ ውሸቱንም የጀመረው አስተዳደሩና አስተዳዳሪው ናቸው፤ ውሸቱ እያደገ በሄደ ቁጥር ችግሩም እየሰፋ ሄደ፤ ውሸቱ ሕዝቡን ሲያጥለቀልቀው ችግሩም ሕዝቡን አጥለቅልቆታል።
ከጅምሩ ገና ውሸቷ ማቆጥቆጥ ስትጀምር በአንድነት ቆመን ብንዋጋና ብንጨፈልቃት አድጋና ተጠናክራ በክርስቲያኖች መካከል ግንብ ሰርታ ሕዝብን የመከፋፈል አቅም ባላገኘች ነበር። ዛሬም በስላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የተጀመረው  ውሸት የሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የሥልጣን መቆናጠጫ መሰላል ለማመቻቸት እንጂ ለሥላሴም ሆነ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የሚፈይደው ነገር ኖሮ አይደለም።
ይልቁንም ይህንን የመሰለ ችግር በማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲደርስ የሌላው ቤተ ርክስቲያን አባላት በማዘንና በመቆጨት እግዚአብሔር መፍትሔውን እንዲያመጣ በጸሎትና በልመና መርዳት እንጂ ምን ዓይነት መግለጫና ማብራሪያ በፈረማችሁት ማመልከቻ (Petition) ላይ ተጨምሮ እንደሚተላለፍ መተማመኛ ሳይኖርና አንዴ የተፈረመውን አስተዳደሩ ለሌላም ጊዜ እንዳማይጠቀምበት ማረጋገጫ በሌለበት በየዋህነት ብቻ ማመልከቻ (Petition) ላይ መፈረም አንዱን ክርስቲያን በሌላው ላይ በማስነሳትና እርስ በእርስ በማጋጨት ከፍተኛ ጸብና ጥላቻን ቀስቅሶ  ያንዱ ቤተ ክርስቲያን ችግር እንደ ተስቦ ወደ ሌላው ቤተ ክርስቲያን በመዛመት ከፍተኛ መዘዝን ቀስቅሶ ያልታሰበና ያልተገመተ ችግርን ለሚያመጣ ተግባር መሣሪያ እንዳትሆኑ መጠንቀቅ ይገባችኋል።
በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የሚችለው እግዚአብሔር  እና የምንኖርበት ሃገር ሕግ ብቻ ነው።
ብልጣ ብልጦችና የውሸት ቋቶች ሃይማኖታችሁን፤ የዋህነታችሁንና ሰው አማኝነታችሁን ተጠቅመው እሬቱን በማር ለውሰው፤ ሃሰቱን የውሸት ቀለም ቀብተው እያቀረቡላችሁ ሳታውቁ በገዛ ጥርሳችሁ ምላሳችሁን እንዳትነክሱ ከማርያም ቤተ ክርስቲያን ችግር በመማር እንደ እርግብ የዋህ ብትሆኑም እንደ እባብ ብልህ መሆን ይጠበቅባችኋል።
ከላይ የተጠቀሰው መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚመለከት ሲሆን የሥለሴ ቤተ ክርስቲያን እና የገብረኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሮችና ሹማምንቶች በተመለከተ በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት አንዱን ወገን በመደገፍ ሌላውን ወገን ለመጉዳትና የቤተ ክርስቲያኗን ችግር ወደ ባሰ ደረጃ ለማድረስ የሚደረጉ ተግባራት ሁሉ እስካላቆሙ ድረሥ ይህንን ተግባር በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም በሚወሰደው እርምጃና በዚህም ሳቢያ ለሚደርሰው ማንኛቸውም ነገር ተጠያቂ መሆናቸውን ከወዲሁ ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን!

የኢትዮጵያውያን የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን በአትላንታ ተቋቋመ፣ ዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን ምስረታ

የኢትዮጵያውያን የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን በአትላንታ ተቋቋመ፣ ዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን ምስረታ

June 19, 2013 Alemtsehay Breast Cancer Foundation (ABCF)
info@abcfonline.org * abcfonline.org
facebook.com/ABCancerFoundation

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15፣ ቀን 2013 ዓም በአትላንታ ከተማ “የዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን” (Alemtsehay Breast Cancer Foundation) መመሥረቱን ወ/ሮ ፊፊ ደርሶ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አስተዋውቀዋል። የፋውንዴሽኑም የመጀመርያ ስብስባ የተደረገው በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማዕከል ነበር። በስብሰባው የተገኙት ተሳታፊዎች በአትላንታና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ስለፋውንዴሽኑ መመስረት እጅግ መደሰታቸውንና ሙሉ በሙሉም ድጋፋቸውን የሚለግሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከተሰበሰቡት መካከል 3ቱ ከካንሰር ህመም የዳኑ (survivors) መሆናቸውን ሲናገሩ፣ “ድርጅቱ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ተናጋሪነት የተጋበዙት ወ/ሮ ለምለም ጸጋው ከዋሽንግተን ዲሲ ነበሩ።Fifi Derso, announced the creation of Alemtsehay Breast Cancer Foundation (ABCF) in Atlanta.
ፋውንዴሽኑ የሚቀጥሉትን አገልግለቶች ለመሥጠት አቅዷል፤
1. በአሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደ እድሜያቸው የሚደረገውን የጡት ምርመራ በራሳቸውና በሃኪሞች እንዲመረመሩ ማስገንዘብ፣ በሽታውም ይዟቸው በህክምናም ላይ ካሉ የመንፈስም ሆነ የገንዘብ ድጎማ እርዳታ መለገሥ፥
2. በአሜሪካ ለሚገኙ በጡት ካንሰር ለተያዙ ኢትዮጵያውያንና ቤተሰቦቻቸው ደጋፊ ማህበር (support group) ማቋቋም፥
3. በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ሴቶች ስለበሽታው ምንነትና ምን ማድረግ እንድሚችሉ፥ ህክምናም ሆነ ትምህርት ስለበሽታው ሴቶችም ሆኑ ወንዶች እንዲያገኙ፣ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ ሃኪም ቤቶችና የጤና ጣቢያዎች በመተባበር መሥራት፥
4. በአሜሪካ አገር ካንሰርን ለማጥፋት ለሚረባረቡ ድርጅቶች ስለኢትዮጵያውያን ሴቶች ለምርመራም ይሁን ህክምና ለማግኘት ያለባቸውን ችግር አስረድቶ ድጋፍ እንዲሰጡ መጣር፥
5. ስለጡት ካንሰር ጥናት የሚያደርጉትን ተቋማት በአሜሪካ የሚኖሩ በጡት ካንሰር የተያዙ ኢትዮጵያኖችን ቁጥር ለይተው እንዲመዘግቡ መገፋፋት።