ከ ዘመን ዘመን ለመኖር ለመግዛት ግዛት ለማስፋት በዘር
ጠርቶ ምንድነው
በድንበር መስፋት
ህዝቡን ጠልቶ
ምንድን ነው ከቶ መደንፋት
የማይገፉውን
መግፋት እኒህም
የኔዎቹ አጠገቤ
ያሉ
ሰርክ
የማገኛቸው ያልገባኝን
ጉዳይ ሁሌ ሳዋያቸው
ምንም ሳይዛነፍ ‹‹እንጃ›› ነው መልሳቸው፤ ‹‹ ከ‹እንጃ› ምሶሶና ከ‹እንጃ ባላ፣ ማገር በ‹እንጃ› ባይ አናፂ በታነፀች አገር ከ‹እንጃ› ማለት በቀር ለጥያቄ ሁሉ ምላሽም አልነበር?›› ብየ እጠይቃለሁ
ብየ እጨነቃለሁ ከጥያቄ ጋን ውስጥ ጥያቄ
እጠልቃለሁ፤ የምሬን
እኮ ነው፤
ከ‹እንጃ› ባይ አገሬ
ከ‹እንጃ› የተሻለ የአገር ምላሽ ባገኝ
‹ለምን?› አስረግዞ ‹ለምን?› የወለደው
የሚያንገበግበኝ ምላሽ ያጣሁለት
ጥያቄ
ነበረኝ፤›› ብዬ እተክዛለሁ ከጥያቄዬ ላይ ጥያቄ
እመዛለሁ፤ ‹‹ማንን
ነው ማዋየው ወይ የማማክረው የልቤ
ጥያቄ ልቤን ተረተረው፤ እያልኩ
አስባለሁ ድንገት
እነጉዳለሁ
ከጥያቄዬ ጋር እወጣ እወርዳለሁ፤
ቢጨንቀኝ
ጊዜ እንጂ፤ እሳት
ሆኖ ወርቅ መምስል ምንድን ነው እንደ
ዕባብ ማስብ
የማይመስል
ሃረግ መሳብ
ብሶት
ያጓለመስው 23 አመት
ቁ ስሉን ሲወራ
የንጥቄያ የዝርፌያ
አውራ በ‹‹እንጃ›› አገር ተፈጥሮ
በ‹‹እንጃ›› ምላሽ አድጎ
‹‹እንጃ›› ሲል ለኖረ ከ‹‹እንጃ›› ማለት በቀር
ከ‹‹እንጃ›› የተሻለ ኢትዩጵያ
ያንቺ መከራ መልስም አልነበረ
ሀቅ ይኸውላችሁ፤ በዚች አገሬና - በዚች አገራችሁ ‹‹ምን ይበጀን ይሆን›› ለሚል ጥያቄዬ
ለሚል ጥያቄያችሁ ‹‹እንጃ›› ነው ምላሹ ‹‹እንጃልህ፣እንጃልሽ›› ወይም ‹‹እንጃላችሁ››፡፡
No comments:
Post a Comment