Thursday, June 19, 2014

በእነማይ ወረዳ የመኢአድ አባላት እየተዋከቡ ነው።


ሰኔ ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅጎጃም ዞን  በነማይወረዳደንጎሊማቀበሌ የሚኖሩት አቶሞሳአዳነቅዳሜሰኔ 7 ቀን በኢህአዴግ ታጣቂዎች ከተገደሉ በሁዋላ ሌሎችም አባሎች እየተዋከቡ መሆኑን የወረዳው የመኢአድ ተወካይ መቶ አለቃ ደመላሽ ጌትነት ተናግረዋል።
ግለሰቡ ገበያ ውሎ ሲመለስ አዲሱ ጫኔ እና ብርሃኑ ታምሩ የተባሉ ካድሬዎች መንገድ ላይ አስቁመው በዱላ ደብድበው እንደገደሉት የሟቹ ወገን የሆኑትና በህይወትና በሞት መካከል ባለ ጊዜ ደርሰው ቃሉን የተቀበሉት አቶ ይልቃል የሻነው ተናግረዋል።
አቶ ይልቃል እርሳቸውንም ለመግደል ሙከራ በመደረጉ አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ገልጸዋል። ፖሊስ ምንም የተጨበጠ መልስ እንዳለስጣቸውም አክለዋል
አቶይበልጣልወንድሜነህ የተባሉ በደብረጥሞና ቀበሌ የሚኖሩት ሌላው የመኢአድ አባል ደግሞ  መሣሪያ ደብቀሃል በሚል ቤታቸው ተከቦ እንደሚገኝ ግለሰቡ ግን ማምለጣቸውን መቶ አለቃ ደመላሽ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።              sourse esat

No comments: