Saturday, June 28, 2014

የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ተከለከለ! – አብርሃ ደስታ


June 27th, 2014  sourse abugda

ህወሓቶች የመቐለ ህዝብ ዓፈናውን በሰለማዊ ሰልፍ እንዳያሰማ ለማፈን ያህል የነገው የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከልክሏል። በደብዳቤ እንዲያሳውቁን በጠየቅነው መሰረት የደብዳቤው ይዘት ምን መሆን እንዳለበት ለስድስት ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ እነሆ ቀኑና ይዘቱ አዛብተው ሰጥተውናል። ስህተት አለው ስንላቸው፤ ዝም ብላቹ ያዙ እሱም በስንት መከራ ነው ብለውናል። ባጭሩ የተቀመጠው ምክንያት ክልላዊና ከተማዊ ዝግጅት ስላለን አይመችም፤ በቂ የፀጥታ ኃይልም የለንም የሚል ነው። ግን ነገ ምንም ዝግጅት እንደሌለ አረጋግጠናል። በቂ የፖሊስ ኃይል እንዳለም የታወቀ ነው። ንፁሃን ዜጎች ለመደብደብና ለማሳሰር ፖሊስ ያላጡ ለሰለማዊ ሰልፍ ኃይል የለንም እያሉን ነው። ደሞኮ ለሚፈጠር ችግር ሓላፊነት ትወስዳላቹ ብለው አስፈርመውናል። ሌላ ደግሞ የፎርም ችግር እንዳለ ፅሑፉ ያትታል። የምን ፎርም መሆኑ አይታወቅም። ለማንኛውም ሰልፉ ለመከልከል ፈልገው በደብዳቤው የሚፃፍ ምክንያት ማጣታቸው ነው የሚያሳየው። ደብዳቤው ለህዝብ እንበትነዋለን ስላልናቸው ‘ሌላ ግዜ የምንፈቅድ መሆኑን እናሳውቃለን’ ይላል ደብዳቤው። ባጠቃላይ ግን ህወሓት የመቐለ ህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እንዲጋለጥ አልፈገምና ከልክሎታል። ጨቋኝ ስርዓት የህዝብ ድጋፍ የለውም። የህዝብ ድጋፍ እንደሌለው እንዲታወቅ ግን አይፈልግም። ሰልፉ ሌላ ግዜም ቢሆን ይደረጋል። ለነገ ግን የመቐለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብቱ መነፈጉ ግልፅ ሆኗል።
It is so!!!10395836_670827396331538_8719857189520019750_n

No comments: