este radio
ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-37 ኢትዮጵያውያን በህወገጥ መልኩ የዝንባብዌን ድንበር በማቋረጣቸው መያዛቸውን ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል።
ኢትዮጵያውያኑ ባዞዎች በተሞላው የሊምፖፖ ወንዝ አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸውን አገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዳቸውም ገልጿል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በእየአመቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚጎርፉ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፍትህ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ኢትዮጵያኑ አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ከሚያደርጉቸዋም ምክንያቶች መካከል በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ።
ተያዙ ስለተባሉ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰጠው መግለጫ የለም
No comments:
Post a Comment