esat radio
ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ 17 ጋዜጠኞች ከስራ መባረራቸው ተገልጾላቸዋል።
ጋዜጠኞች የተባረሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይታወቅም፣ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ተቃውሞ እንዲሁም ባህርዳር ላይ ተደርጎ ከነበረው የስፖርት ዝግጅት የቀጥታ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሳይሆን አይቀርም።
ቀድም ብሎ ውስጣዊ ግምገማዎች ሲካሄዱ እንደነበር የኢሳት የመረጃ ምንጮች ጠቁመው፣ 6 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ቀደም ብለው እንዲታገዱ መደረጉን አስታውሰዋል።
በውስጥ ትርምስ ውስጥ የሚገኘው ኦህዴድ፣ በክልሉ የሚታየውን አለመረጋጋት ለማብረድ ላይ ታች ቢልም እስካሁን አልተሳካለትም።
በሚቀጥሉት ተከታታይ ሳምንታት አንዳንድ የዞን እና የወረዳ ባለስልጣናት እንደሚባረሩ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል።
No comments:
Post a Comment