ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ መንገድ መግባታቸውን የገለጸው የኬንያ ፖሊስ፣ 54ቱ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቤት ውስጥ ታጭቀው ተገኝተዋል ብሎአል።
ሰዎቹን ወደ ኬንያ ያመታው ግለሰብ መጥፋቱንም ፖሊስ ገልጿል። ኢትዮጵያውያንን ወደ ደቡብ አፍሪካ ማሻገር ትልቁ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ፖሊስ ገልጿል።
ወደ ደቡብ አፍሪካ እንጓዛለን በማለት ሙከራ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ በ ዝምባብዌ፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያና በሌሎችም አገራት ታስረው እንደሚገኙ ዘገባዎች ያመለክታሉ። sourse esat
No comments:
Post a Comment