ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን፣ በአብዛኛው አካባቢዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። አቦቦ በሚባለው አካባቢም
ግጭቱ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በጉራፈርዳ ያለው ግጭት አንጻራዊ በሆነ ሁኔታ መቀነሱን የሚናገረው የአካባቢው ወኪላችን፣ ከአካካቢው የሚሰደዱት ሰዎች ከመንግስት በኩል የሚሰጣቸው እርዳታ ባለመኖሩ አሁንም ለከፋ ችግር ተደርገዋል።
ወኪላችን እንደሚለው በአካባቢው በብዛት የተሰማሩት የቀድሞ የህወሃት አባላት መሬት በስፋት መያዛቸው አሁን ለተፈጠረው ቀውስ መንስኤ ሳይሆን አይቀርም።
በግጭቱ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናት እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም። sourse http://ethsat.com/
No comments:
Post a Comment