Thursday, October 23, 2014

የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀልና በሽብር የሚጠረጥራቸውን ሰዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በቀላሉ ለመያዝና ንብረቶቻቸውን ለመውረስ የሚያስችለው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡


ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የጠረጠሩትን ዜጎች በመያዝ ለፈላጊው ሀገር አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ትብብር መሰረት መረጃው በሚፈለገው ሀገር አግባብነት ባለው ተቋም ህጋዊ መጠየቂያ
ደብዳቤ መሰረት ለተጠያቂው ሀገር በመላክ ይከናወናል ይላል፡፡ ስምምነቱ በተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳይ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ፣ ቃል የመቀበል፣ የሚያዙ ሰዎችን ወይንም ምስክሮች ለትብብር ጠያቂው ሀገር የፍርድ አካላት የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ፣ የፍርድ ሰነዶችን ለተጠርጣሪዎች የማድረስ፣
የንብረት ብርበራ ማድረግና መያዝ፣ የወንጀል ፍሬነገሮችን በመለየት የሚያዙበት፣ የሚታገዱበትና የሚወረሱበት ሁኔታ የማመቻቸት፣ የተጠርጣሪ ግለሰቦች ግንኙነት የመጥለፍ፣ በወንጀል ሒደት ውስጥ ሰርጎ በመግባት የወንጀል መረጃዎችን የማሰባሰብና በጊዜያዊነት ለወንጀል ስራ የተያዙ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት
ትብብሮችን ያጠቃልላል፡፡ ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ ዲሴምበር 4/2013 በሱዳን ካርቱም ከተማ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋር ትብብር በፈጸሙት ስምምነት መሰረት ይህ አዋጅ መቅረቡ ታውቋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ አራት ክፍሎች፣ 26 አንቀጾች ያካተተ ሲሆን ፓርላማው ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ኮምቴ የመራው ሲሆን በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሚቃወሙትን ሃይሎች ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ የሻዕቢያ ቅጥረኛ የሚሉ ታፔላዎችን በመለጠፍና በሽብር ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት በጎረቤት ሀገራት በጥገኝነት እንዳይኖሩ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እያሳደደ፣ አንዳንዶቹንም እያሰረ መሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እያስከተለበት
እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሱዳን ለተቃዋሚዎች የመንቀሳቀሻ ቦታ እንዳትሰጣቸው ለማድረግ የአገሪቱን ሰፊ መሬት አሳልፎ መስጠቱን ተችዎች ይገልጻሉ። የምእራብ አርማጭሆ የአንድነት ፓርቲ ተወካይ አቶ አንጋው ተገኝ  የሱዳን ታጣቂዎች በድንበር አካባቢ የሚፈጽሙት ወንጀል እየባዛ ነው በማለት ተናግረዋል           sourse esat

No comments: