Saturday, October 11, 2014

አምባሳደር ሚኒልክ የስራ መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ


መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄነቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፅ/ቤት ባለሙሉ ስልጣን በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታሁን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ማግኘታቸውን ተከትሎ  ሃላፈነታቸውን መልቀቃቸውን  ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል።
የኢህአዴግ ዋና ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው አምባሳደር ሚኒልክ ፣ ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ በመቆየታቸው ” ታጋይ ሚኒልክ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል።
አምባሳደሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንድ ብሔር በተወጣጡ ዲፕሎማቶች መከበባቸው፤ ይህም በፈጠረባቸው  ጭንቀት በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደ የከፍተኛ ዲፕሎማቶች ስብሰባ ላይ በተካፈሉ ጊዜ ለሚቀርቧቸው ጓደኞቻቸው መናገራቸው ከባለስልጣናት ጀሮ መድረሱ ስጋት ላይ ጥሎአቸው ቆይቷል።
አምባሳደሩ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ካገኙ በሁዋላ ፣ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። አምባሳደሩ መልቀቂያቸው ተቀባይነትያገኘ በመሆኑ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ስልጣናቸውን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጉዳዩ ዙሪያ አምባሳደር ሚኒሊክን  በስልክ አነጋግረናቸው መልሳችሁ ደውሉ ካሉ በሁዋላ፣ መልሰን ስንደውል ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።    sourse esate radio

No comments: