ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ አባላት አሸባሪዎች ገብተዋል በማለት የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ፍተሻ እንዳስመረራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የተጠናከረ ፍተሻ ሰኞ እለት ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት በቦሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች፣ አሸባሪዎች ገብተዋልና አጋልጡ በሚል መኪኖች ሲፈተሹ መዋላቸውን፣ መንገደኞች እየቆሙ መፈተሻቸውን እንዲሁም የቤት ለቤት አሰሳ መደረጉን ለሰአታት ታግተው የቆዩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የአካባቢው ሰዎች መንግስት ሆን ብሎ ሽብር በመንዛት ስራችን እንዳንሰራ እያደረገን ነው፣ የሚፈነዳ ነገር ካለም መንግስት ራሱ የሚያፈነዳው ይሆናል ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል esate RIDO
No comments:
Post a Comment